Posts

ከተለያዩ የገቢ አርዕሰቶች ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን በሲዳማ ዞን የአለታ ጩኮ ወረዳ ገቢዎች ባለሥልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ መንግስቱ መለስ እንደገለፁት የተገኘው ገቢ በዓመት ውስጥ ሊሰበሰብ ከታቀደው የ3ዐ ሚሊዮን ብር አካል ክንውኑም 1ዐ7 ብልጫ እንደሚኖረው አስታውቋል፡፡ ገቢው ከአመና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ1 ሚሊዮን ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡ የመስሪያ ቤቱ ሠራተኞችን በገቢ አሰባሰብ ስምሪት በ24 ሰዓት በፈረቃ በማድረግና ህገ ወጥ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊ መስመር ማስገባት መቻሉ አቶ መንግስቱ ተናግረዋል፡፡ ለገቢው መጨመር አስተዋፅኦ እንደነበረው በወረዳው የግብር ከፋይና ምዝገባ ክትትል የንግዱ ማህበረሰብ ግብር በወቅቱ በመክፈል ሀላፊነቱን እንዲወጣ ትልቅ አገዛ እንዳደረገላቸው ገልፀዋል፡፡ አንዳንድ  ግብር ከፋዮች በሰጡት አስተያየት መንግስት ያቀዳቸውን ውጥኖች ማሳካት ግብርን በወቅቱ መክፈል የገባነው ቃል እንወጣለን ሲሉ መናገራቸውን የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል፡፡

ጥራት ያለው ትምህርት ለልማት ያለው ፋይዳ ጉልህ በመሆኑ ሁሉመ ባለድርሻ አካላት መረባረብ እንደሚጠበቅባቸው በሲዳማ ዞን የአለታ ጩኮ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በወረዳው የሚገኙ የትምህርት ባለድርሻ አካላት በወረዳው ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ሞዴል በሆነው በማንጉዶ ትምህርት ቤት በመገኘት ሰሞኑን የተሞክሮ ልውውጥ አድርገዋል፡፡ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሽመልስ አየለ እንደገለፁት ጥራት ያለው ትምህርት ለልማት ያለው ፋይዳ የላቀ መሆኑን በመገንዘብ ጥራቱን ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው ከትምህርት ባለ ድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ሥራ መስራታቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚሁ በተሰራው ሰፊ ስራ በወረዳው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የትምህርትን ጥራት ለማምጣት የእርስ በርስ የሥራ ፉክክር መንፈስ በመላበስ እንዲሰሩ በተደረገው መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ ከወረዳው ከሚገኙ ከ43 ትምህርት ቤቶች መካከል  የመንጉዶ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተያዘው በአንደኛ ሩብ አመት በትምህርት ሥራ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ሞዴል ትምህርት ቤት መሆኑን አብራርተዋል፡፡ የማንጉዶ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ዱሬሳ ዮኖራ በበኩላቸው ትምህርት ቤቱ በአሁኑ ጊዜ 1ኛና ሞዴል ሊሆን የቻለው መንግስት የቀረፀውን ስድስቱን የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጆችን ከትምህርት ባለ ድርሻ አካላት ጋር ተግባራዊ በማድረጋቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከሲዳማ ዞን ትምህርት መምሪያ የትምህርት ጥራት ዋና የሰራ ሂደት አስተባባሪ አቶ እሸቱ ቃሬ እንደተናገሩት የትምህርት ቤቶች የልምድ ልውውጥ የትምህርትን ጥራት በማስጠበቁ ረገድ የላቀ ሚና አለው፡፡ ልምድ ልውውጡ ወቅት ለ12 ወላጅ አጥ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እዳይስተጓጎሉ ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ከተገኘው ገንዘብ የተለያዩ አልባሳት ተበርክተውላቸዋል ፡፡ የበንሳ ቅርንጫፈ እንደዘገበው፡፡ http://www.smm.gov.et/

በሀዋሳ ከተማ ከ253 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የልማት ፕሮግራም እየተካሄደ ነው

Image
ሃዋሳ ታህሳስ 04/2005 በሀዋሳ ከተማ መንግስታዊ ያልሆኑ 74 ድርጅቶች ከ253 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ በጀት ህብረተሰቡን ያሳተፉ የልማት ፕሮግራሞች እያካሄዱ መሆናቸውን የከተማው ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ገለጸ፡፡ የመምሪያው ምክትል ሃላፊ አቶ አሻሬ ኡጋ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በከተማው ስምንት ክፍለ ከተሞች የሚካሄደው የልማት ፕሮግራም ለሚቀጥሉት ሶስት አመታት የሚቆዩ ናቸው፡፡ ከልማት ፕሮግራሞቹ መካከል የጤና፣ የትምህርት፣ የከተማ ግብርና፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የህጻናት ድጋፍና ክብካቤ፣የገቢ ማስገኛ ፣አቅም ግንባታን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ዘርፎች መሆናቸውን አስታውቀዋል የከተማውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማፋጠን መንግስት የሚያደረገውን ጥረት ለማገዝ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ህብረተሰቡን በማሳተፍ የሚካሄዱት የልማት ፕሮግራሞች ሲጠናቀቁ ከ200ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡ የድርጅቶቹን የስራ አንቅስቃሴና አፈጻጸም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ክትትልና ቁጥጥር እያደረጉ መሆናቸውንም አመልከተዋል፡፡ እየተጠናቀቀ ባለው የአውሮፓውያኑ 2012 የስራ ዘመን ድርጅቶቹ በመደቡት ከ84 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የከተማው ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደረጉ ተመሳሳይ የልማት ፕሮግራሞች ማካሄዳቸውን የመምሪያው ምክትል ሃላፊ ገልጸዋል፡፡ http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=3941&K=1

ስራ ኣጥነት እና የወጣቶች እሮሮ በሲዳማ

Image
  በኪንክኖ ኪአ በሲዳማ ዞን በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች በሥራ አጥነት የሚሰቃዩ ወጣቶች ቁጥር ከጊዜ ቀደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ፡፡ ሥራ ያጡ ወጣቶችም በተለያዩ ወረዳዎች ሠላማዊ ሠልፍና ተቃዉሞ እያሰሙ መሆናቸዉ ታዉቀዋል፡፡ ሰሞኑን በአርቤጎና ወረዳ በተካሄደዉ ተቃዉሞ ሰልፍ ሳቢያም ከ15 በላይ ወጣቶች መተሰራቸዉ ተሰመቶአል፡ በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ ሙያና ት/ት ዘርፎች ተከታትለዉ ከተመረቁ በኀላ የሥራ እድል በማጣት በርካታ ወጣቶች በከፍተኛ ችግር ላይ መዉደቃቸዉ በሰፊዉ ይነገራል፡፡ የከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ት ካጠናቀቁ በኀላ በተለያዩ ኮሌጆች፡ የሙያ ማሠልጠኛ ተቐማትና ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸዉን የተከታተሉ ወጣቶች ቁጥር በርከት እያሌ መምጣቱ የሚነገር ሲሆን ከዚሁ ቁጥር ጋር የሚመጣጠን የሥራ እድል በመንግሥት ባለመመቻቸቱ ከፍተኛ የሆነ የሥራ አጥነት ችግር በዞኑ ተንሰራፍተዋል፡፡     ወጣቶቹ በት/ት የቀሰሙትን እዉቀት ተጠቅመዉ ሕብረተሰቡን ለማገልገልና የራሳቸዉን ሕይወት ለማሻሻል ከፍተኛ ተነሳሽነትና አቅምያላቸዉ ቢሆንም ት/ታቸዉን አጠናቀዉ ከ5 እና ከዚያ በላይ ዓመታትን የለሥራ በማሳለፋቸዉ ሰቢያ ሊለማ የሚችል እዉቀት፤አቅምና ጉልበት በጥቅም ላይ ሣይዉል እንደሚባክን ተጠቁመዋል፡፡   የሥራ አጥ ወጣቶች የኑሮ መሠረት በአጭሩ አብዛኞቹ የሥራ አጥ ወጣት ምሁራን የተገኙት ከገጠሩ ማህበረሰባችን ከፍል ነዉ፡፡ ትምህርታቸዉን ለመከታተልም ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ወጪ አድርገዉ፤ አብዛኞቹ ደግሞ በግል ት/ት ተቐማት በራሳቸዉ አቅም ትምህርታቸዉን የተከታተሉ ናቸዉ፡፡ እንደሚታወቀዉ አብዛኛዉ የሲዳማ ማህበረሰብ የገጠር ነዋሪ በመሆኑ የኢኮኖሚ መሠረቱ ግብርና ከመሆኑም በተጨማሪ የገቢ ምንጫቸዉና አቅምቸዉ ይኼ ነዉ የሚባል አይደለም፡፡ ይህም ሆኖ እነ

የሀዋሳን መስህቦች ከጎበኙ ቱሪስቶች ከ16 ነጥብ 8ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ፡፡

Image
አዋሳ ታህሳስ 3/2005 በሀዋሳ ከተማና አካባቢውን የሚገኙ የመስህብ ቦታዎችን ባለፉት ሶስት ወራት ከጐበኙ የሀገር ውስጥና የውጪ ቱሪስቶች ከ16 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የከተማው አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝምና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳይ መምሪያ አስታወቀ፡፡ በመምሪያው የቱሪዝምና ፓርኮች የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አዲሴ አኔቶ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በሀዋሳ ከተማና አካባቢው የሚገኙ የመስህብ ቦታዎች ባለፉት ሦስት ወራት በ47 ሺህ 728 የሀገር ውስጥና 10 ሺህ 139 የውጪ አገር ቱሪስቶች ተጐብኝተዋል፡፡ ቱሪስቶቹ የጎበኟቸው የመስህብ ቦታዎች የሀዋሳ ሀይቅንና በውስጡ ያሉት ብርቅዬ የአእዋፍ ዝርያዎች፣ ጉማሬዎች ፣ በከተማው ዙሪያ የሚገኙት የአላሙራና የታቦር ተራራዎች፣ የጥቁር ውሃ ደን ፣ የቡርቂቲ ፍል ውሃ ፣ የሲዳማ ባህላዊ ጎጆዎችንና የተለያዩ ብሄረሰቦች የባህል አልባሳት ፣ አመጋገብና የሙዚቃ መሳሪዎች ጨምሮ ሌሎች ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶች ነው፡፡ የተገኘው ገቢም ሆነ የቱሪስቶች ቁጥር ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር አምስት በመቶ ብልጫ እንዳለው ገልፀዋል፡፡ ገቢውም ሆነ የቱሪስቶች ቁጥር ሊጨምር የቻለው የቱሪዝም ሀብቱን በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በማስተዋወቅ ጎብኚዎችን ለመሳብ በተደረገው ጥረት መሆኑን የስራ ሂደቱ አስተባባሪ አመልከተዋል፡፡ የሀዋሳ ከተማ የአየር ንብረት ተሳማሚነት፣ የመስተንግዶና የመሰረተ ልማት መስፋፋትን ጨምሮ ለመዝናናትና ለኑሮ ባለው ምቹነት አካበቢውን ለመጎብኘት የሚመጡ የሀገር ውስጥና የውጪ ቱሪስቶች ቁጥር በየአመቱ እየጨመረ እንዲሄድ አስተዋጽኦ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡ የጐብኝዎች ቁጥር መጨመርን ተከትሎም የሚገኘው ገቢ በዚያው መጠን እያደገ መሆኑን አስተባበሪው