ስራ ኣጥነት እና የወጣቶች እሮሮ በሲዳማ
በኪንክኖ ኪአ በሲዳማ ዞን በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች በሥራ አጥነት የሚሰቃዩ ወጣቶች ቁጥር ከጊዜ ቀደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ፡፡ ሥራ ያጡ ወጣቶችም በተለያዩ ወረዳዎች ሠላማዊ ሠልፍና ተቃዉሞ እያሰሙ መሆናቸዉ ታዉቀዋል፡፡ ሰሞኑን በአርቤጎና ወረዳ በተካሄደዉ ተቃዉሞ ሰልፍ ሳቢያም ከ15 በላይ ወጣቶች መተሰራቸዉ ተሰመቶአል፡ በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ ሙያና ት/ት ዘርፎች ተከታትለዉ ከተመረቁ በኀላ የሥራ እድል በማጣት በርካታ ወጣቶች በከፍተኛ ችግር ላይ መዉደቃቸዉ በሰፊዉ ይነገራል፡፡ የከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ት ካጠናቀቁ በኀላ በተለያዩ ኮሌጆች፡ የሙያ ማሠልጠኛ ተቐማትና ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸዉን የተከታተሉ ወጣቶች ቁጥር በርከት እያሌ መምጣቱ የሚነገር ሲሆን ከዚሁ ቁጥር ጋር የሚመጣጠን የሥራ እድል በመንግሥት ባለመመቻቸቱ ከፍተኛ የሆነ የሥራ አጥነት ችግር በዞኑ ተንሰራፍተዋል፡፡ ወጣቶቹ በት/ት የቀሰሙትን እዉቀት ተጠቅመዉ ሕብረተሰቡን ለማገልገልና የራሳቸዉን ሕይወት ለማሻሻል ከፍተኛ ተነሳሽነትና አቅምያላቸዉ ቢሆንም ት/ታቸዉን አጠናቀዉ ከ5 እና ከዚያ በላይ ዓመታትን የለሥራ በማሳለፋቸዉ ሰቢያ ሊለማ የሚችል እዉቀት፤አቅምና ጉልበት በጥቅም ላይ ሣይዉል እንደሚባክን ተጠቁመዋል፡፡ የሥራ አጥ ወጣቶች የኑሮ መሠረት በአጭሩ አብዛኞቹ የሥራ አጥ ወጣት ምሁራን የተገኙት ከገጠሩ ማህበረሰባችን ከፍል ነዉ፡፡ ትምህርታቸዉን ለመከታተልም ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ወጪ አድርገዉ፤ አብዛኞቹ ደግሞ በግል ት/ት ተቐማት በራሳቸዉ አቅም ትምህርታቸዉን የተከታተሉ ናቸዉ፡፡ እንደሚታወቀዉ አብዛኛዉ የሲዳማ ማህበረሰብ የገጠር ነዋሪ በመሆኑ የኢኮኖሚ መሠረቱ ግብርና ከመሆኑም በተጨማሪ የገቢ ምንጫቸዉና አቅምቸዉ ይኼ ነዉ የሚባል አይደለም፡፡ ይህም ሆኖ እነ