Posts

Why such Daunting Silences The Sidama Sons and Daughters?

December 08 2012 (Kukkisa, Our reporter from Sidama Capital Hawassa) Ohi!! the Sidama nation of north East Africa, From where may I start my lament? From where may I begin my argument? How can I reveal the hidden face of all evils and their architects? How can I unravel behind the scene secrets? How can I show you the poisonous policies? Perpetrated against your nation, the biggest story for an ongoing discussion? Or with what language on earth may I speak? The depth, magnitude and the extent of your ongoing grievances? Over a century old neglected pleas? And about the situation you’re obliged to live under, That is causing you untold disaster? How can I say and who can I speak to? In the land of lawlessness where brutalities rule over innocents!! From where may I start my laments? You fathers of the Sidama kids, unable to provide, to your families’ burning needs, As your lone attempt fail to succeed, Extremely confused, not knowing what to do, and where and to who to turn to, when you

33ቱ ፓርቲዎች የምክትል ጠ/ሚኒስትሮቹን ሹመት ተቃወመ

Written by  ሠላም ገረመው    ኢራፓ “ስርአቱ ይስተካከል እንጂ ሹመቱን አልቃወምም” ብሏል በቅርቡ በአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በፓርላማ ቀርቦ የፀደቀው የሁለት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች ሹመት ህገመንግስቱን የሚፃረር ነው ሲሉ በአዳማ ከተማ ፔቲሽን ተፈራርመው ለምርጫ ቦርድ ጥያቄዎቻቸውን ያቀረቡ 33 ፓርቲዎች ተቃወሙ፡፡ ኢራፓ በበኩሉ የኢህአዴግ ስርዓት ይስተካከል እንጂ ከህገመንግስት ውጭ ቢሆንም ለአገር እስከጠቀመ ድረስ ሹመቱን አልቃወምም ብሏል፡፡ የአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ሁለት ባለስልጣናትን በምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ማዕረግ ለፓርላማ አቅርበው ማፀደቃቸው ህገመንግስቱን የጣሰ ተግባር ነው ብለዋል - ፓርቲዎቹ፡፡ ባለፉት ጊዜያትም በጥድፊያና ከህገመንግስቱ ጋር በሚፃረር መልኩ የወጡት የፀረሙስና የመያዶች የፕሬስና የፀረ ሽብር አዋጆች ሁኔታው ቀጣይ እንጂ አዲስ ነገር አለመሆኑን ያሳያል ብለዋል - በመግለጫቸው፡፡ “የአጀንዳው አቀራረብም ሆነ የሹመቱ አፀዳደቅ ከፓርላማው የአሰራር ስነስርዓት ጋር ያልተጣጣመና በተለመደው ጥድፊያ የተከናወነ ነው አጀንዳው ለፓርላማ አባላት በተለመደው አሰራር መሰረት ያልተሰራጨ ከመሆኑም በላይ በሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ከህገመንግስቱ አንፃር ሳይመረመርና ሳይታይ መፅደቁ ይህን ያረጋግጣል” ብለዋል ፓርቲዎቹ፡፡ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤትም በተለያዩ ጊዜያት የህገመንግስቱን ድንጋጌዎች የሚጥሱ አምዶችን ተቀብሎ ማፅደቁን ፓርቲዎቹ ጠቁመው፤ አሁንም ከዚህ ድርጊቱ ሳይቆጠብ በህገ መንግስቱ አንቀፆች 74፣ 75 እና 76 ሀገሪቱ አንድ ምክትል ጠ/ሚኒስትር እንደሚኖራትበግልጽ ቢቀመጥም ከህገመንግስቱ ውጪ ሌሎች ሹመቶችን ተቀብሎ ማጽደቁ ህገመንግስቱን መጣስ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡ ገዢው ፓ

ሐዋሳ ከነማ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ መሪ ሆነ

Image
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ ረቡዕ ህዳር 26/2005 በተከናወነው ጨዋታዎች ሐዋሳ ከነማ እና ደደቢት ድል ሲቀናቸው መብራት ኃይልና ኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ጥለዋል። በዘጠነኛው ሳንምት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በዕለቱ አምስት ጨዋታዎች ተከናውነዋል።ከነዚህ መካከል ሐዋሳ ላይ ሐዋሳ ከነማ አርባምንጭ ከነማን ያስተናገደበት ጨዋታ ከፍተኛ ግምት አግኝቶ ነበር። የፕሪምየር ሊጉ መሪ የነበረው ቅዱስ ጊዩርጊስ ህዳር 25/2005 ሐረር ላይ ከሐረር ቢራ ጋር ተጫውቶ ነጥብ ጥሎ በመመለሱ ምክንያት ሐዋሳ መሪነቱን የሚረከብበት መልካም አጋጣሚ ይዞ ነበር ወደ ሜዳ የገባው። ዘንድሮ ጥሩ እንቅስቃሴ እያሳየ ያለው ሐዋሳ የደቡብ ደርቢውን ጨዋታ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በመርታት ለወራት ያክል የደረጃ አናት ላይ የሚሆንበት ጣፋጭ ድል ይዞ ወጥቷል።ብሩክ አየለ የሐዋሳ ከነማን ሁለቱንም ግቦች ሲያስቆጥር በረከት ዳሙ ደግሞ የአርባምንጭን ብቸኛ ግብ ከመረብ አገናኝቷል። ከህዳር 27/2005 ጀምሮ ለብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅትና አፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ሲባል የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች ስለሚቆረጡ ሐዋሳ ከነማ መሪነቱን ይዞ ለበረካታ ሳምንታት ይቆያል። ወደ አዳማ ከነማ ተጉዞ በአዳማው አበበ ቢቂላ ሰታዲየም ውጤት የራቀውን አዳማ ከነማን የገጠመው ደደቢትም 3ለ1 አሸንፎ ተመልሷል።ጌታነህ ከበደ ለደደቢት ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል። በዚህም የሊጉን ከኮከብ ግብ አግቢነት በብቸኝነት ይመራል።በኃይሉ አሰፋ ቀሪዋን የደደቢት ግብ አስቆጥሯል። በውጤቱም ደደቢት ከቅዱስ ጊዩርጊስ እኩል 18 ነጥብ በመያዝ በግብ ክፍያ በልጦ ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላል። ወደ አሰላ ተጉዞ የነበረው ኢትዮጵያ ቡና ከሙገር ሲምንቶ ጋር ያለምንም ግብ በመለያየት ሁለት

የግብር አሠባሰብ ስርዓቱን ለማጠናከር ከግብር ከፋዮች ጋር ተቀራርቦ መስራት እንደሚገባ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሀዋሣ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡

ጽህፈት ቤቱ ለግብር ከፋዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ የጽህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬ ፈቃደ እንዳሉት  በግብር ሰብሳቢውና ግብር ከፋዩ መካከል ጤናማ ግንኙነት መፍጠር ያስፈልጋል፡፡ በግብር አሠባሠብ ሂደቱ ላይ በሚስተዋሉ ችግሮች ላይም ውይይት ተደርጓል፡፡ አቅምን ያላገናዘበ የግብር ግመታ መሻሻል እንዳለበትም ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል፡፡ በምክክር መድረኩ በሀዋሣ ፣ሻሸመኔ ፣ ዲላና ወላይታ ከተሞች የሚገኙ የፌደራል ግብር ከፋዮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ባልደረባችን በሀይሉ ጌታቸው እንደዘገበው፡ http://www.smm.gov.et/_Text/25HidTextN205.html

የሀዋሣሳ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ሁሉን አቀፍና ተደራሽ ህብረተሰብ ለመፍጠር መሰናክሎች ማስወገድ በሚል መሪ ቃል የአለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን አከበረ፡፡

ቀኑ የመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤቶች አካል ጉዳተኞችን ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚያደርጉ እቅዶችን መያዛቸውን ለመገምገም የተዘጋጀ ነው፡፡ የክልሉ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ኤጀንሲ የማህበራዊ  ደህንነት ልማት ኦፊሰር አቶ አየለ ስሜ እንደገለፁት አካል ጉዳተኞች በሁሉም ዘርፎች እኩል ተጠቃሚ የሚሆንበት አሠራር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ  ማህበራት ፌደሬሽን የደቡብ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ  አቶ ወንድማገኘው ይስሀ አካል ጉዳተኝነት ለኤች አይ ቪ ኤድስ እና ለድህነት የሚያጋለጥ በመሆኑ በጤና ተቋማት አካል ጉዳተኞችን  ያካተተ ስራ መጠናከር እንዳለበት ገልፀዋል፡፡ አንዳንድ የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በከተማው ለአይነ ስውራንና  መስማት ለተሳናቸው የሚሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለመኖሩ ትምህርታቸው መጠቀል አለመቻላቸውን ተናግረዋል፡፡ የተለያዩ የስፖርት ውድድሮችም የተካሄዱ ሲሆን ከአንድ እስከ 4 ለወጡ ተወዳዳሪዎችም የብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ ባልደረባችን ቢንያም ተስፋዬ እንደዘገበው፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/25HidTextN305.html