Posts

ሐዋሳ ከነማ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ መሪ ሆነ

Image
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ ረቡዕ ህዳር 26/2005 በተከናወነው ጨዋታዎች ሐዋሳ ከነማ እና ደደቢት ድል ሲቀናቸው መብራት ኃይልና ኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ጥለዋል። በዘጠነኛው ሳንምት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በዕለቱ አምስት ጨዋታዎች ተከናውነዋል።ከነዚህ መካከል ሐዋሳ ላይ ሐዋሳ ከነማ አርባምንጭ ከነማን ያስተናገደበት ጨዋታ ከፍተኛ ግምት አግኝቶ ነበር። የፕሪምየር ሊጉ መሪ የነበረው ቅዱስ ጊዩርጊስ ህዳር 25/2005 ሐረር ላይ ከሐረር ቢራ ጋር ተጫውቶ ነጥብ ጥሎ በመመለሱ ምክንያት ሐዋሳ መሪነቱን የሚረከብበት መልካም አጋጣሚ ይዞ ነበር ወደ ሜዳ የገባው። ዘንድሮ ጥሩ እንቅስቃሴ እያሳየ ያለው ሐዋሳ የደቡብ ደርቢውን ጨዋታ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በመርታት ለወራት ያክል የደረጃ አናት ላይ የሚሆንበት ጣፋጭ ድል ይዞ ወጥቷል።ብሩክ አየለ የሐዋሳ ከነማን ሁለቱንም ግቦች ሲያስቆጥር በረከት ዳሙ ደግሞ የአርባምንጭን ብቸኛ ግብ ከመረብ አገናኝቷል። ከህዳር 27/2005 ጀምሮ ለብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅትና አፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ሲባል የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች ስለሚቆረጡ ሐዋሳ ከነማ መሪነቱን ይዞ ለበረካታ ሳምንታት ይቆያል። ወደ አዳማ ከነማ ተጉዞ በአዳማው አበበ ቢቂላ ሰታዲየም ውጤት የራቀውን አዳማ ከነማን የገጠመው ደደቢትም 3ለ1 አሸንፎ ተመልሷል።ጌታነህ ከበደ ለደደቢት ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል። በዚህም የሊጉን ከኮከብ ግብ አግቢነት በብቸኝነት ይመራል።በኃይሉ አሰፋ ቀሪዋን የደደቢት ግብ አስቆጥሯል። በውጤቱም ደደቢት ከቅዱስ ጊዩርጊስ እኩል 18 ነጥብ በመያዝ በግብ ክፍያ በልጦ ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላል። ወደ አሰላ ተጉዞ የነበረው ኢትዮጵያ ቡና ከሙገር ሲምንቶ ጋር ያለምንም ግብ በመለያየት ሁለት

የግብር አሠባሰብ ስርዓቱን ለማጠናከር ከግብር ከፋዮች ጋር ተቀራርቦ መስራት እንደሚገባ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሀዋሣ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡

ጽህፈት ቤቱ ለግብር ከፋዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ የጽህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬ ፈቃደ እንዳሉት  በግብር ሰብሳቢውና ግብር ከፋዩ መካከል ጤናማ ግንኙነት መፍጠር ያስፈልጋል፡፡ በግብር አሠባሠብ ሂደቱ ላይ በሚስተዋሉ ችግሮች ላይም ውይይት ተደርጓል፡፡ አቅምን ያላገናዘበ የግብር ግመታ መሻሻል እንዳለበትም ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል፡፡ በምክክር መድረኩ በሀዋሣ ፣ሻሸመኔ ፣ ዲላና ወላይታ ከተሞች የሚገኙ የፌደራል ግብር ከፋዮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ባልደረባችን በሀይሉ ጌታቸው እንደዘገበው፡ http://www.smm.gov.et/_Text/25HidTextN205.html

የሀዋሣሳ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ሁሉን አቀፍና ተደራሽ ህብረተሰብ ለመፍጠር መሰናክሎች ማስወገድ በሚል መሪ ቃል የአለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን አከበረ፡፡

ቀኑ የመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤቶች አካል ጉዳተኞችን ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚያደርጉ እቅዶችን መያዛቸውን ለመገምገም የተዘጋጀ ነው፡፡ የክልሉ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ኤጀንሲ የማህበራዊ  ደህንነት ልማት ኦፊሰር አቶ አየለ ስሜ እንደገለፁት አካል ጉዳተኞች በሁሉም ዘርፎች እኩል ተጠቃሚ የሚሆንበት አሠራር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ  ማህበራት ፌደሬሽን የደቡብ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ  አቶ ወንድማገኘው ይስሀ አካል ጉዳተኝነት ለኤች አይ ቪ ኤድስ እና ለድህነት የሚያጋለጥ በመሆኑ በጤና ተቋማት አካል ጉዳተኞችን  ያካተተ ስራ መጠናከር እንዳለበት ገልፀዋል፡፡ አንዳንድ የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በከተማው ለአይነ ስውራንና  መስማት ለተሳናቸው የሚሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለመኖሩ ትምህርታቸው መጠቀል አለመቻላቸውን ተናግረዋል፡፡ የተለያዩ የስፖርት ውድድሮችም የተካሄዱ ሲሆን ከአንድ እስከ 4 ለወጡ ተወዳዳሪዎችም የብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ ባልደረባችን ቢንያም ተስፋዬ እንደዘገበው፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/25HidTextN305.html

ተቃዋሚዎቹ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መነጋገር ይፈልጋሉ

Image
ሰላሣ ሦስት የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በዚህ ዓመት የሚደረገው የአካባቢ ምርጫና ወደፊትም የሚካሄዱት ምርጫዎች እንደ 2002 ዓመተ ምኅረቱ ከሆኑ ለአገሪቱ ህልውናም አስጊ ናቸው አሉ። ፓርቲዎቹ ከዚህ አኳያ መንግሥት እንዲያነጋግራቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት ጥያቄ እንደሚያቀርቡ አስታውቀዋል። ባለፈው ወር አዳማ ከተማ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ2005 ዓ.ም የአባባቢ ምርጫን አስመልክቶ መርኃግብሩን ካሣወቀ በኋላ እነዚህ ፓርቲዎች ላቀረቡት የጋራ ጥያቄ “አጥጋቢ መልስ አልሰጠም” ሲሉ ሰላሣ ሦስቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያቋቋሙት ጊዜያዊ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አሥራት ጣሴ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡ አቶ አሥራት ጣሴ ​​ በኢትዮጵያ የሚካሄዱት ምርጫዎች ነፃ፣ ፍትሐዊ፣ ሕጋዊና ተቀባይነት ያላቸው እንዲሆኑ ከተፈለገ ያለፈውን መንገድ መድገሙ ዋጋ የለውም፣ የበለጠ ችግርም ውስጥ ይከትተናል ብለዋል ፓርቲዎቹ፡፡ ይህ የፓርቲዎቹ ብቻ ዕምነት እንዳልሆነ የጠቆሙት አቶ አሥራት ጣሴ በ2002 ዓ.ም የተካሄደውን ሃገርአቀፍ ምርጫና ኢሕአዴግ 99.6 ከመቶ አሸንፌበታለሁ ያለበትን ምርጫ ዓለምአቀፍ ታዛቢዎች አይቀበሉትም” ብለዋል፡፡ ዝርዝሩን ከመለስካቸው አምኃ ዘገባ ያዳምጡ፡፡

በደቡብ ደርቢ በጉጉት የሚጠበቀው የሀዋሳ ከነማና አርባ ምንጭ ከነማ ፍልሚያ ሀዋሳ ላይ ይደረጋል: ሀዋሳ ከነማ በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ በድል ከተወጣ ለሁለት ወራት ያህል የደረጃ ሰንጠረዡን መምራት የሚያስችለውን አጋጣሚ ያገኛል

9ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መለስ ዋንጫ ህዳር 25/2005 ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል። በ8ኛው ሳምንት መርሀ ግብር በሜዳው በሀዋሳ ከነማ ሽንፈት የደረሰበት ቅዱስ ጊዮርጊስ ህዳር 25/2005 ሀረር ላይ ከሀረር ቢራ አንድ አቻ በመለያየት ተመልሷል፡፡ባለ ሜዳዎቹ ሀረር ቢራዎች አሸናፊ አደም ባስቆጠራት ግብ ለበርካታ ደቂቃዎች መርተዋል። የደረጃ ሰንጠረዡ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ነጥብ ያገኘበትን የአቻነት ግብ ኡመድ ኡኩሪ በ77ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡በሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ 5 ነጥቦችን የጣለው ቅዱስጊዮጊስ ህዳር 26/2005 ሀዋሳ ከነማ የሚያሸንፍ ከሆነ የደረጃ መሪነቱን ይነጠቃል፡፡ደደቢትም በተሻለ ግብ ልዩነት ድል ከቀናው ከቅዱስ ጊዮርጊስ በላይ መቀመጥ ይችላል፡፡ የህዳር 25/2005 መርሀ ግብር የሆነው ሌላው በአዲስ አበባ ስታድየም መከላከያና የኢትዮጵያ ውሀ ስራዎች ፍልሚያ ነበር፡፡መከላከያ 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት በመርታት ሁለት ደረጃዎችን በማሻሻል ከ10ኛ ወደ 8ኛ ከፍ ማለት ችሏል፡፡ኢትዮጵያ ውሀ ስራዎች ግን ከዘጠኝ ጨዋታዎች በምንም ማሸነፍ ተስኖታል፡፡ያለው ብቸኛ ነጥብ ከሙገር ሲሚንቶ ጋር አንድ አቻ የተለያዩበት ሲሆን በርካታ የግብ ክፍያዎችን ይዞ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ ህዳር 25/2005 የ9ኛው ሳምንት ቀሪ አምስት ጨዋታዎች ይጠበቃሉ፡፡በደቡብ ደርቢ በጉጉት የሚጠበቀው የሀዋሳ ከነማና አርባ ምንጭ ከነማ ፍልሚያ ሀዋሳ ላይ ይደረጋል፡፡ሀዋሳ ከነማ በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ በድል ከተወጣ ለሁለት ወራት ያህል የደረጃ ሰንጠረዡን መምራት የሚያስችለውን አጋጣሚ ያገኛል፡፡ደደቢት በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም ውጤት ከራቀው አዳማ ከነማ ይገናኛል፡፡እዚህ አዲስ አበባ ስታድየም