Posts

Unity over Rights Pave Ethiopian Oppositions’ Future

Image
It takes two to tango. EPRDF’s talk about democracy appears to deal more with the image of democracy than with its reality. The oppositions’ talk about democracy seems to be targeted more at assuming power by whatever means than at providing a unified alternative for the people to choose from. That is the drama of democracy played everyday inEthiopia. The vital question, however, is; how can the drama be abandoned and reality be adopted? Standing at the fore of the stage is the Ethiopian opposition. How the drama would be played out would also be highly dependent on their move. The political climate on the ground is squeezing the opposition with each passing day. To make things worse, the opposition itself is weak due to divisions. Forgoing its purpose, it settles for mere opposition. The opposition has to go through rebirth. Otherwise, it will soon become a do-nothing force as far as peaceful struggle is concerned. Even then, the opposition is not at the mercy

ያበራሽን ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወትም! የጃፓንን ጠባሳ ያየ በውሃ አይጫወትም! የአሜሪካንን ጠባሳ ያየ በንፋስ አይጫወትም!

አንድ የአፈ-ታሪክ ንጉሥ ህዝብ እያጉረመረመና እያደመ ሲያስቸግራቸው እንዲህ ያደርጉ ነበር አሉ፡፡ “እገደል አፋፍ ላይ ትልቅ ድንኳን ጣሉ” ይሉና ያዛሉ፡፡ “ከየት እስከ የት?” ይላቸዋል ባለሟሉ፡፡ “ህዝባችንን የሚይዘውን ያህል አስፍታችሁ ትከሉት” “የዚያን የሚያህል ድንኳን ከየት እናገኛለን ንጉሥ ሆይ?” “ቀጣጥላችሁም ቢሆን በሰፊው ስሩልኝ ብያለሁ፤ ብያለሁ፡፡ ይሄን ይሄንን መሥራት ካልቻላችሁ ለምን ሾምኳችሁ?!” ብለው ቱግ ብለው ይቆጣሉ፡፡ ባለሟሎቹ ሁሉ ይሸማቀቃሉ፡፡ አንደኛው ባለሟል እንደምንም ቀና ብሎ፤ “ለመሆኑ ይሄ ለምን አስፈለገን ንጉሥ ሆይ?” ሲል ይጠይቃል፡፡ “የዚህን ህዝብ ዝርያ ማጥፋት እፈልጋለሁ፡፡ አይታዘዝ፣ ልቡ አይታወቅ፣ ያወቀውን አውጥቶ አይናገር፤ ወይ በደንብ አይስቅ ወይ በደምብ አያለቅስ!... መቀጣት አለበት!” “እንዴት ነው የምንቀጣው?” አለና ጠየቀ ሌላው፡፡ ንጉሡም፤ “የሚበላው በርካታ ምግብ፣ የሚጠጣው ጠጅ፣ ታዘጋጃላችሁ!” “ለህዝቡ ሁሉ የሚበቃ ምግብኮ የለንም፡፡ ያን ያህል ምግብ ልንሰጠው የምንችል ከሆነማ ህዝቡስ ለምን ያጉረመርምብን ነበር?” ንጉሡ ተቆጡ፡- “አንተ ለህዝቡ ነው የቆምከው ለእኔ?! የምልህን በትክክል ካልፈፀምክ ለምን ሾምኩህ ታዲያ?” ሁሉም እጅ ይነሱና “እሺ ንጉሥ ሆይ እንዳሉን እናደርጋለን!” ይላሉ፡፡ “ከዚያ” አሉ ንጉሡ “ጠጁን ጥምብዝ አድርጐ የሚያሰክር ታደርጉታላችሁ!” “ለምን ንጉሥ ሆይ?” “ጥንቢራው እስኪዞር ጠጥቶ ጥምብዝ እንዲል ነዋ!” “ከዛስ? ንጉሥ ሆይ” “የድንኳኑን መውጫ በር በገደሉ በኩል ታረጉታላችሁ! ያኔ በገዛ እጁ ገደል ይገባል፡፡ እኛ አበላን አጠጣነው እንጂ አልገፈተርነውም፡፡ ወዶ በላ! ወዶ ጠጣ፤ ወዶ ገደል ገባ!! አለቀ፡፡ እኛን አያስጠይቀንም!” “እሺ ንጉሥ

የማይዝል ክንድ

በምሕረት አስቻለው ጥቂት የማይባሉ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሰዎች የቫይረሱ በደማቸው ውስጥ መገኘት በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ የመሥራት አቅማቸው፣ ወይም ሌሎች የዕለት ተዕለት ክንዋኔአቸው ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ይሰማቸዋል፡፡ በሌላ በኩል አብረዋቸው የሚሠሩ በዙርያቸው ያሉ ስለ እነዚህ ሰዎች ኤችአይቪ ፖዘቲቭ መሆንና የመሥራት አቅምና ተመሳሳይ አመለካከት ሲያንፀባርቁ ይስተዋላል፡፡ እያንዳንዷን ቀን መርካቶ ጭድ ተራ እየተባለ ከሚጠራው ቦታ ላይ ለሚያሳልፈው ወጣት የቀን ሠራተኛ ቫይረሱ በደሙ ውስጥ የሚገኝ ነገር ግን የሥነ ልቦና ጥንካሬ ያለው ሰው ጉልበት ፈታኝ በሆነው የቀን ሥራ ላይ ቢሰማራ ምንም የሚገርም ነገር እንደሌለው ይናገራል፡፡ ባደረገው የኤችአይቪ ምርመራ የቫይረሱን በደሙ ውስጥ መገኘት ካወቀ አራት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ የመጀመርያዎቹን ሁለት ዓመታት ፀረ ኤችአይቪ መድኃኒት መውሰድ አላስፈለገውም ነበር፡፡ አራቱንም ዓመታት ግን የጉልበት ሥራ ሠርቷል፡፡ የትውልድ ቀዬው ቂጨሞን ጥሎ እንደ ብዙዎቹ የቀዬው ወጣቶች ሠርቶ ለመለወጥ ወደ አዲስ አበባ የመጣው ከአሥር ዓመታት በፊት የ18 ዓመት ወጣት እያለ ነበር፡፡ የሆቴል መስተንግዶ፣ ጀብሎን ጨምሮ የተለያዩ ሥራዎችን ሠርቷል፡፡ እዚህም እዚያም እያለ የጉልበት ሥራ እየሠራ ኑሮውን ለማሸነፍ ደፋ ቀና ሲል በነበረበት ወቅት ከተዋወቃት ጓደኛው ጋር በትዳር ተሳስሮ አንድ ልጅ ማፍራት ችሏል፡፡ ለወጣቱ በምን አጋጣሚ የኤችአይቪ ምርመራ እንዳደረገ ጥያቄ አቅርበንለት ነበር፡፡ ከጓደኛው ጋር በጋብቻ ተሳስረው መኖር እንደጀመሩ ሳንባ መታመም ጀመረ፡፡ ይኖሩ የነበረው የባለቤቱ አክስት የሚያከራዩት አንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ ነበር፡፡ ሕመሙን የተመለከቱት አክስቷ በግልጽ ኤችአይቪ መሆኑን

የነፃ ገበያ ውድድሩ ወዴት?

በዳዊት ታዬ የዜጎችን የመኖርያ ቤት ችግር ለመቅረፍ መንግሥት ተግባራዊ ለማድረግ ያቀደው የጋራ መኖርያ ቤቶች ግንባታ አተገባበር ሲያወያይ መሰንበቱ ይታወቃል፡፡ ማወያየት ብቻ ሳይሆን ብዙ ውዥንብር መፍጠሩንም ከሁለት ሳምንታት በፊት በየቀበሌው ደጃፍ የተመለከትነው ግርግር ይመሰክራል፡፡ የ40/60 የመኖርያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለመሆን የነበረው ጉጉት ከልክ በላይ መሆኑንም የምንረዳበት ነው፡፡ የ40/60 የቤቶች ፕሮጀክት አተገባበር አሁንም ድረስ ብዥታ እንደፈጠረ ነው፡፡ ከዛሬ ነገ ምዝገባው ይጀመራል እየተባለ አሁንም ድረስ እየተጠበቀ ቢሆንም ነገሩ በእንጥልጥል ላይ ቀርቷል፡፡ ምዝገባው ለምን አልተጀመረም? ለሚለው ጥያቄ በቂ መልስ አልተገኘም፡፡ ሌሎች ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮችም እስካሁን ጥርት ብለው አልተገለጹም፡፡ በ40/60 የመኖርያ ቤቶች ፕሮጀክት እየተስተዋለ ያለው ሽፍንፍን ያለ አካሄድ እንደተጠበቀ ሆኖ ፕሮጀክቱን መሬት ላይ ለማውረድ ቤት ፈላጊው እንዲያሟላ የሚጠበቅበት የ40 በመቶ የቅድሚያ ክፍያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል በሚካሄድ ቁጠባ ስለመሆኑ ግን ለሁሉም ግልጽ ነው፡፡ ዜጎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ የግንባታ ወጪውን ከባንክ ጋር አስተሳስሮ ግንባታውን ለማከናወን መቻሉ የሚደገፍ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት አሠራር እስካሁንም መዘግየት አልነበረበትም፡፡ ሆኖም የጋራ መኖርያ ቤቶችን ለመገንባት ወይም አሁን እንደታሰበው በ40/60 የመኖርያ ቤቶች ግንባታ ከባንክ ጋር በማስተሳሰር የሚሠራውን ሥራ ለአንድ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መስጠቱ እንደ ትክክለኛ ዕርምጃ ሊወስድ ግን አይችልም፡፡ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ያሉትን የመኖርያ ቤት ፈላጊዎችን ትተን በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ብቻ ወደ በሚሊዮን የሚገመቱ ዜጎች የራሳቸው

ሹመት ብቻ ሳይሆን ሽረትም እንጠብቃለን

Image
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ለፓርላማ ያቀረቡትን ሹመት ፓርላማው አፅድቆታል፡፡ ተጨማሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችም ተሹመዋል፡፡ እያንዳንዱ ሹመት በፓርቲ ውስጥ ተሳትፎን ያረጋገጠ፣ አመኔታ ያሳደረ፣ የሕዝብ ጥቅምና ክብርን ግምት ውስጥ ያስገባ፣ ሕገ መንግሥቱን መሠረት ያደረገ መሆኑን አደራ በማለት ልዩ ትኩረት ሰጥታችሁ አረጋግጡ፣ ወስኑ፣ ፈጽሙ፣ ከማለት በስተቀር ለምን ሾማችሁ አንልም፡፡ ተሿሚዎች ኃላፊነታቸውን በሚፈለገው ብቃት፣ ሥነ ምግባርና ፍጥነት ሲወጡ ለማየት እንጓጓለን እንጂ፡፡ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም፣ በአጠቃላይ ለመንግሥት፣ መንግሥታዊ ሥልጣን ለያዘው ኢሕአዴግ አንድ ዓብይና ጠቃሚ እንዲሁም አስቸኳይ የሆነ የምናቀርበው ጥያቄ ግን አለን፡፡ ጥያቄያችንም ስለመሾም ስታስቡ ስለሚሻሩም ታስባላችሁ ወይ? የሚል ነው፡፡ በግልጽ ለማስቀመጥ ከተፈለገም ክፍት ቦታ ላይ መሾም ብቻ አይደለም ቁም ነገሩ፡፡ የተያዘ የሥልጣን ወንበር ካለና ወንበሩ ላይ የተቀመጠው ሹምም ብቁ ካልሆነ፣ ከሥልጣኑ በማንሳት የተሻለ መሾም አስፈላጊ መሆኑን አምናችሁ ለመንቀሳቀስ ዝግጁ ናችሁ ወይ? የሚል ነው፡፡ መሾም አለባቸው ከሚለው ጎን ለጎን መሻር አለባቸው የሚባሉ እንዳሉም መታመን አለበት፡፡ በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ የኃላፊነትና የሥልጣን ወንበሮች ላይ ተቀምጠው ሥራቸውን በሕግ፣ በግልጽነት፣ በኃላፊነትና በተጠያቂነት መንፈስ መወጣት ያልቻሉ አሉ፡፡ በአቅም ማነስ፣  በሥነ ምግባር ጉድለትና በፖለቲካዊ አመለካከት ምክንያት፡፡ መንግሥትም ሆነ ኢሕአዴግ ይህንን ሁኔታ በድፍረትና በቆራጥነት አይተው የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት የማይወጡትን ከኃላፊነት ማንሳት አለባቸው እንላለን፡፡ ብቁዎችን ሾሜያለሁ ከማለት ጎን ለጎን ብቃት የሌላቸውን ሽሬያለሁ ወይም እ