ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሹመቱ ህገመንግስቱን የሚጋፋ ነው አሉ
Written by መታሰቢያ ካሳዬ ኃላፊነቴን ከህዝቡ ጋር በአግባቡ እወጣለሁ - ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ሹመቱ ኢህአዴግ ያለበትን የፖለቲካ ሽኩቻ ለማስታገስ ያደረገው ነው የተሰጠው ሹመት በብቃት ላይ የተመሰረተ አይደለም ሹመቱ የቀድሞ ጠቅላይ ሚ/ር አሻራ አለበት (ተቃዋሚዎች) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከትናንት በስቲያ ያፀደቀውን የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት፣ የንግድ ሚኒስትርነት፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትርነትና ሌሎች ሹመቶችን አስመልክቶ ሹመቱ በአግባቡና በሥርዓት ያልተሰጠና ህጋዊ ሥርዓት የሚጐድለው ነው ሲሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተናገሩ፡፡ ሹመቱ ህገመንግስቱን የሚጋፋና ከህግና ሥርዓት ውጪ የተሰጠ ነው ሲሉም ተችተውታል፡፡ በአንድ ድምፀ ተአቅቦና በሙሉ ድምጽ ድጋፍ በፀደቀው ሹመት መሠረት ሁለት ተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትሮችም ተሹመዋል፡፡ ከትናንት በስቲያ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተከናወነው ሥነሥርዓት ሹመታቸው የፀደቀላቸው አቶ ሙክታር ከድር በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር እና ሪፎርም ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በምክትል ጠቅላይ ሚ/ር ማዕረግ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ አቶ ታደለ ጫኔ የንግድ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና ዶ/ር ከስተብርሃን አድማሱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡ ብቸኛው የመድረክ ተወካይና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ በሹመቱ ወቅት ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል፡፡ አቶ ግርማ ድምፀ ተአቅቦ ያደረጉበትን ምክንያት ሲናገሩም፤ ሹመቱ ከመሰጠቱ በፊት ስለተሿሚዎቹ ለም