“ሕዝቡ ከማጉረምረም አልፎ ንዴቱን በእንቅስቃሴ ለማሳየት ዝግጁ የሆነ አይመስልም” ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፤ ሲዳማም ውስጥ ያለው እውኔታ ይሄው ነው
በኣጠቃለይ በኢትዮጵያ ደረጃ በኣገሪቱ ውስጥ ያሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚሉት ከሆነ ህዝቡ በመልካም ኣስተዳደር ይዞታ ላይ ያለውን ቅሬታ ኣውጥቶ ለመናገር ወነ ያጣ ሲሆን ተመሳሳይ ሁኔታ በሲዳማ ውስጥም በመከሰት ላይ ነው፤ ምናልባት የሲኣን በኣዲስ ኣመራር መዋቀር ህዝቡን ከላነቃቃው በስተቀር ማለት ነው። በኣጠቃላይ ኣገሪቱን በተመለከተ ዝርዝሩን ከታች ያንቡ። ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር - ኢሕአዴግ ለሕዝብ ደንታ የለውም አሉ - ብልሹ የምርጫ ሥርዓት መስፈኑን ወቀሱ በጋዜጣው ሪፖርተር ባለፈው እሑድ ኅዳር 16 ቀን 2005 ዓ.ም. አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ በአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ባደረገው ውይይት ላይ የመነሻ ሐሳብ ያቀረቡት የፓርቲው ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሶተኛና በማጉረምረም ደረጃ ላይ የሚገኝ እንጂ፣ ንዴቱን በእንቅስቃሴ ለማሳየት ዝግጁ የሆነበት ደረጃ ላይ የደረሰ አይመስልም አሉ፡፡ የአገሪቱን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በዳሰሱበት ክፍል ላይ በሰጡት ማብራሪያ ሕዝቡ በርካታ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እንዳሉበት ገልጸው፣ ይህንን ሰቆቃውንና ብሶቱን ያማርራል እንጂ በይፋና በአደባባይ አይገልጽም ብለዋል፡፡ “ብሶቱ በማጉረምረም ደረጃ የሚገለጽ ነው እንጂ ወደ ኅብረተሰባዊ ንዴት አልተለወጠም ብለው፣” የተናጠል ንዴቶች አልፎ አልፎ ቢገለጹም ሰፊና የአጠቃላይ ኅብረተሰቡ አለመሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ “እነዚህ የተናጠል ትናንሽ ንዴቶች ወደተደራጀና ሕዝባዊ የእምቢተኝነት እንቅስቃሴዎች አልተለወጡም፡፡ በሌሎች አገሮች በዳቦ ወይም በነዳጅ ዋጋ ላይ ትንሽ ጭማሪ ከታየ የኅብረተሰቡ ንዴት ይገነፍላል፡፡ በእኛ ሕዝብ ዘንድ ግን ይህ አይታይም፡፡ ምልክቶች ከታዩ ጥቂ