Posts

አዲሱ ጠ/ሚንስትርና የአዲስ ካቢኔ ጉዳይ

Image
አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሀገሪቷን ለመምራት ቃለ-መሃላ የገቡት ባለፈው መስከረም ወር እንደነበረ የሚታወስ ነው። አቶ ኃይለ-ማርያም፤ ወደ ሥልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ካቢኔያቸውን ለኢትዮጵያ ፓርላማ ያቀርባሉ ተብሎ ቢጠበቅም ፣ በይፋ ሲከናወን አልታየም። በተለይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነቱን ሥልጣን የያዘው ሰው እስካሁን ግልጽ አልተደረገም። የካቢኔው ይፋ አለመሆንና በተለይም የውጭ ጉዳይ እስካሁን አለመሾሙ ምክንያቱ ምን ይሆን? በዚሁ ጉዳይ ላይ ገመቹ በቀለ ፣ ኒውዮርክ ከሚኖረው ወጣት የፖሊቲካ ተንታኝ ፣ጀዋር መሐመድ ጋር ቃለምልልስ አድርጓል። አዲሱ ጠ/ሚንስትርና የአዲስ ካቢኔ ጉዳይ

ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ምርትና ምርታማነት በመጨመር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል የግብርና ቴክኖሎጂ እያስተዋወቀ ነው

Image
አዋሳ ህዳር 18/2005 የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነትን ለመጨመርና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከ11 የሚበልጡ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ በማስተዋወቅ ላይ እንደሚገኝ የሀዋሳ ዩነቪርስቲ ገለጸ፡፡  በዩኒቨርስቲው በሲዳማና ገዴኦ ዞኖች በሙከራ ደረጃ እየተሰሩ ያሉ ቴክኖሎጅዎችን የማላመድ፣ የማስተዋወቅና የማስፋፋት ስራዎች ሰሞኑን ተጎብኝቷል፡፡ የዩኒቨርስቲ አካዳሚና ምርምር ምክትል ፕሬዜዳንት ዶክተር ፍቅሬ ደሳለኝ በጉብኝት ወቅት እንደገለጹት በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መጨረሻ የግብርና ምርት በእጥፍ ለማሳደግ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ዝርያዎችን ለማላመድና ማስፋፋት ስራ ዩኒቨርስቲው ትኩረት ተሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ዩኒቨርስቲው በሀገሪቱ የግብርና ምርታማነትን ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ የሚያግዙና በምርምር ጣቢያ ምርታማነታቸው የተረጋገጠ 11 ዝርያዎችን በክልሉ አራት ወረዳዎች የማባዛትና የማላመድ ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በልጆች ላይ የሚከሰተውን የቫይታሚን ኤ ንጥረ ምግብ እጥረት የሚከላከሉ ሰብሎች፣ የቤተሰብ ገቢና የምግብ ዋስትናን ለማሻሻል የሚያግዙ፣ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ፣ የአንስሳት መኖ፣ ሀገር በቀል የበግና ፍየል ዝርያዎችን የማዳቀልና ማባዛት እንዲሁም መኖን በዩሪያ ማከምና ድርቆሽ ሳይበላሽ የማቆየት ዘዴዎች ይገኙበታል ብለዋል፡፡ በሄክታር እስከ 50 ኩንታል ምርት ሊሰጡ የሚችሉ የቢራና የምግብ ገብስ፣ ባቄላና ሌሎች የሰብል ዝርያዎች የሚገኙ ሲሆን በብተናና በመስመር የመዝራት ልዩነትና ከዚሁም ሊገኝ የሚችሉ ጠቀሜታዎች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡ በንጥረ ምግብ ይዘት የበለፀጉ የደጋና የወይና ደጋ የጥራጥሬ ሰብሎችን በማምረት የቤተሰብ የንጥረ ምግብ አቅርቦትን ለማሻሻል፣ ናይትሮጂን ወደ ራሳቸው በማዋ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ ኢትዮጵያ ቡና እና ሀዋሳ ከነማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

Image
በ7ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ ህዳር 16/2005  በተለያዩ ከተሞች አምስት ጨዋታዎች ተካሂደዋል። አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ በ8 ሰዓት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሙገር ሲሚንቶ ተገናኝተው 2 አቻ በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል። ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ታዬ አስማረ እና ሳምሶን ሙሉጌታ ሲያስቆጥሩ ለሙገር ሲምንቶ እስክንድር አብዱአሚድ እና አዲሱ ዋናሮ ጎሎቹን አስቆጥረዋል። 10 ሰዓት ላይ የተደረገው ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮጵያ መድህን ያደረጉት ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና 4 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ለኢትዮጵያ ቡና ታፈሰ ተስፋዬ ፣ሰለሞን ገብረመድህን ፣ቶክ ጀምስ እና ፋሲል አስፋው ጎሎቹን አስቆጥረዋል።አራቱም ጎሎች በመጀመሪያው አጋማሽ ነው የተቆጠሩት። ኢትዮጵያ መድህን ሁለተኛው ግማሽ ላይ በመሐመድ ናስር የማስተዛዘኛውን ጎል አስቆጥሯል። በመብራት ኃይል እና በመከላከያ መካከል የተደረገው ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ ውጤት ተጠናቋል። ጨዋታው በተጀመረው በአራተኛው ደቂቃ መብራት ኃይል በበረከት ይሳቅ የመጀመሪያውን ጎል በማስቆጠር መሪ መሆን ቢችልም መከላከያ ሁለት ጎሎችን በዮሐንስ ኃይሉ አስቆጥሮ እረፍት ወጥቷል። የመብራት ኃይሉ በረከት ጎል ሊሆኑ የሚችሉ አጋጣሚዎች ሳይጠቀምበት ቀርቷል። ሁለተኛው አጋማሽ ላይ መብራት ኃይል ያገኛትን የፍፁም ቅጣት ምት አዲስ ነጋሽ አስቆጥሮ አቻ ወጥቷል። ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከነማ የኢትዮጵያ ውሃ ሰራዎችን አስተናግዶ 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት ሲረታ። ሀረር ቢራ ከሲዳማ ቡና 1 አቻ በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተዋል። ውጤቱን ተከትሎ ሀዋሳ ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በአንድ ነጥብ ዝቅ ብሎ በ13 ነጥብ በሁለተኛነት የሊጉን ደረጃ ይዟል። መብራት ኃይል ፣ኢትዮጵያ ቡና ፣ ሀረር ቢራ

በጃፓን የኢፌዴሪ የክብር ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ተከፈተ

Image
አዲስ አበባ፡- በጃፓን ናጎያ ከተማ የኢፌዴሪ የክብር ቆንስላ ጽሕፈት ቤት መከፈቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ለጋዜጣው በላከው መግለጫ፤ ጽሕፈት ቤቱ በተከተፈበት ወቅት በጃፓን የኢፌዴሪ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ «ኢትዮጵያ ነፃነቷን አስጠብቃ የቆየችና ለጥቁር ሕዝቦች ነፃነትና ፓን አፍሪካኒዝም የጐላ ሚና የተጫወተች ሀገር ናት» ማለታቸውን አስታውቋል። በአሁኑ ወቅትም ሠላምና መረጋጋት የሰፈነባት ከመሆኗም ባሻገር ልማቷን በማፋጠን ድህነትን ድል ለማድረግ እየተንቀሳቀሰች መሆኑ ተጠቁሟል። እንደ አምባሳደር ማርቆስ ገለጻ፤ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ያስቆጠረ ነው። ጃፓን በጠንካራ አጋርነቷ በተለይም የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ውጤታማነትን ከፍ በማድረግና በጐ ፈቃደኞችን በመላክ የቴክኒክና ዕውቀት ሽግግር እንዲስፋፋ አስተዋፅኦ እያበረከተች ነው። በጃፓን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ቪንቺ አሳዙማ በበኩላቸው፤ ጃፓንና ኢትዮጵያ ረጅም ጊዜ የቆየ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው አመለክተው፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን እያደረገች ያለው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በቀጣይ በምታዘጋጀው ለአፍሪካ ልማት የቶክዮ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይም ጠንካራ አስተዋፅኦ እንደሚኖራት ያላቸውን እምነት ጠቁመዋል። የክብር ቆንስላ ጽሕፈት ቤቱ መከፈት ሁለቱ አገራት ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የራሱ አስተዋፅኦ እንዳለው አመልክተዋል። በዕለቱ በጃፓን የኢትዮጵያ መንግሥት የክብር ቆንስላ ሆነው እንዲሠሩ የተመረጡት ሚስተር ላዲማቺ ማትሲሞት የሹመት ደብዳቤ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማን ከአምባሳደር ማርቆስ ተክሌ እጅ ተረክበዋል።

ብሄራዊ የስነ- ህዝብ ምክር ቤት ሊቋቋም ነው

Image
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በያዝነው ዓመት የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር 84 ነጥብ 3 ሚሊዮን ገደማ መድረሱን ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ያደረገው ሳይንሳዊ ግምት ያመለክታል። የሃገሪቱ ፖሊሲ የህዝብ ቁጥርን መቀነስ ላይ ከማተኮር ይልቅ ፥ ያለውን የህዝብ ቁጥር ከሃገሪቱ የልማት አቅምና የኢኮኖሚ ክፍፍል ጋር ማጣጣም ላይ አተኩሮ የሚሰራ ነው። ኢትዮጵያም የህዝብ ቁጥሩን ዕድገት ከኢኮኖሚ ዕድገቷ ጋር ለማመጣጠን እንዲያስችላት ፥ ከዛሬ 18 ዓመት በፊት የስነ-ህዝብ ፖሊሲ ቀርጻ ወደ ትግበራ ብትገባም ፥ እስካሁን ተግባራዊ አልተደረገም። ይህንኑ የስነ-ህዝብ ጉዳይ የሚያስተባብረውን የብሄራዊ ስነ-ህዝብ ምክር ቤት ለማማቋም ፥ ባለፈው አመት ረቂቅ ደንብ በማዘጋጀት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን ፤ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ተጠባባቂ የስነ-ህዝብ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ መኮንን ናና ተናግረዋል። እሳቸው እንዳሉት የሚቋቋመው ምክር ቤት ይበልጥ ውጤታማ ይሆን ዘንድ ፥ እንደገና ሰፋ ያለ ጥናት ተደርጎበት ፤ በዚህ አመት መጨረሻ ወይም በሚቀጥለው አመት መጀመሪያ ላይ ፥ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ይቀርባል። ረቂቁ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ አስኪጸድቅ ድረስም ፥ የማስተባበሩን ሒደት ለማከናወን ሃገር አቀፍ ግብረ ሃይል በያዝነው ወር ውስጥ በማቋቋም ፥ ምክር ቤቱ እስኪመሰረት ግብረ ሃይሉ የማስተባበሩን ስራ እያከናወነ ይቆያል ብለዋል አቶ መኮንን። ሃገሪቱ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ባለሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ ዕድገት ብታስመዘግብም ፥ ካላት የህዝብ ብዛት ጋር መመጣጠን ባለመቻሉ አጠቃላይ የምርት መጠኗ 412 አሜሪካን ዶላር ላይ እንዲወሰን አስገድዷታል። የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ እንደሚያመለክተው ደግሞ ፥ በሃገሪ