Posts

የህብረተሰብ ጤና ልማት ሰራዊትን ለመገንባት 63 ሺህ በላይ ሞዴል ቤተሰቦች ማፍራቱን የሀዋሣ ከተማ ጤና መምሪያ ገለፀ፡፡መምሪያው የ2ዐዐ5ሩብዓመትእቅድክንውንገምግሟል፡፡

Image
የእቅድ ክንውን ሪፖርት በቀረበበት ወቀት የመምሪያው ኃላፊ አቶ ደሰታ ዶጊሶ አንደተናገሩት በሩብ አመቱ የእናቶችንና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ ከከተማዋ ፈጣን እድገት ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ የጤናና የማህበራዊ ችግሮች በመፈታት ነዋሪውን ጤናማ፣ አምራችና የበለፀገ ለማድረግ የጤና ልማት ሰራዊት ግንባታ ተግባራዊ መሆን መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡ የህብረተሰብ ጤና ልማት ሰራዊትን ከመገንባት አንፃርም ከ63 ሺህ 993 ሞዴል ቤተሰቦች ማፍራቱን ተናግረዋል፡፡ በሪፖርቱ እንደቀረበው የሳንባ ነቀርሳ በሽታን መከላከያ ክትባት ለ2 ሺህ 678 ህፃናት ለመስጠት ታቅዶ 2 ሺህ 971 የተከናወነ ሲሆን ባለፈው ሩብ አመት አብዛኛዎቹ አፈፃፀሞች ከእቅዱ 9ዐ በመቶ እና ከዚያ በላይ ተግባራዊ መሆናቸው በሪፖርቱ ቀርቧል፡፡ ከመንጋጋ ቆልፍ በሽታ የተጠበቀ ህፃናት እንዲወለዱ ከማድረግ አንፃርም በሩብ አመቱ 2 ሺህ 678 ህፃናት አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ ከእቅድ በላይ መከናወኑንም ተጠቁሟል፡፡ በመቀጠልም በበጀት ዓመቱ የጤና ሴክተር ትኩረት የሚያደርገው የጤና ተቋማት በማስፋፋትና በግብዓት በሟሟላት የጤና አገልግሎቶች ጥረት ማሻሻል የእናቶችና የህፃናት ሞትን በመቀነስና ዋና ዋና ተላላፊ በሽታዎችና መከላከልና መቆጣጠር ላይ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ በጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች አማካኝነት 124 እናቶች የወሊድ አገልግሎት ለመስጠት እቅድ ተይዞ ለ49 እናቶች ብቻ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም በተሻለ ሁኔታ ለመስራት ጥረት እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡ በምክክር መድረኩም የሀዋሣ ክፍለ ከተሞች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የጤና ባለሙያዎች እና ሌሎች አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡http://www.smm.gov.et/_Text/1

የህፃናት መብቶችን በተመለከተ ከጊዜ ወደ ጊዜ የህብረተሰቡ ግንዛቤ እያደገ መምጣቱን በኢትዮጵያ ሠብአዊ መብት ኮሚሽን ሀዋሣ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ጽህፈት ቤቱ 7ኛውን የአለም ህፃናት ቀን ከትምህርት ቤቶች ጋር አክብ b ል፡፡ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ አስተባባሪ አቶ አብርሃ አታሮ እንዳሉት ትምህርት ቤቶች ሰብአዊ መብትን በተመለከተ ህፃናት ተኮትኩተው የሚያድጉበት በመሆኑ የኮሚሽኑን አላማ ለማሳካት ትልቅ ፋይዳ አላቸው፡፡ መጪው ትውልድ ሰብአዊ መብቶችን ለማክበርና ለማስከበር የሚያስችለውን ስንቅ ከትምህርት ቤቶች ይቀስማል ብለዋል ፡፡ በሀገራችን ዘንድሮ ለ7ኛ ጊዜ የሚከበረው የዓለም ህፃናት ቀን “ሁሉም ህፃናት ሰብአዊ መብቶችን በማከበር፣ በማስከበርና ሌሎችንም በማስገንዘብ ትምህርት ቤቶች ትልቅ ሚና አላቸው” የሚል መርህ አላው፡፡ በበአሉ አለም አቀፍ የህፃናት መብቶች ኮንቬንሽንን፣ የአፍሪካ ህፃናት ሰብአዊ መብትንና የኢትዮጵያ መንግስት ለሠብአዊ መብቶች የሠጠውን ትኩረት የሚዳስስ ጽሑፍ ቀርቧል፡፡ የበአሉ ተሳታፊ ህፃናቶች የተለያዩ ጭውውቶችንና ሥነ ጽሑፎችን አቅርበዋል፡፡ ትምህርት ቤቶች በሥነ ምግባር የታነፀ የሞራል እሴት ያለው፣ የነቃና ህግ አስከባሪ ዜጋ ለመፍጠር የሚያደርጉትን ጥረት  ህብረተሰቡና ባለድርሻ አካላት እንዲደግፉ ጥሪ ቀርቧል ፡፡ ባለደረባችን ደስታ ወ/ሰንበት እንደዘገበው፡፡http://www.smm.gov.et/_Text/11HidTextN305.html

ከመፈክር ይልቅ ዲሞክራሲ!

ሰላም! ሰላም! ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ላላችሁ በሙሉ። አንድ ወዳጄ ይኼንን የአቅጣጫ ሰላምታ እንደማይወደው አጫውቻችሁ አውቃለሁ? ለምንድን ነው ስለው ‹‹የሰው ልጅ እንደ ንፋስ በአቅጣጫ ላይ ተመሥርቶ ሰላምታ ሲለዋወጥ እበሽቃለሁ፤›› አይለኝ መሰላችሁ? የዘንድሮን ሰው የሚያበሽቀውን ነገር ብዛት ቆጥረን መጨረስ አቃተን! ግን ግን ንፋስን ለምንከተል የዘመኑ ሰዎች ይህ ሰላምታ ካልተሰጠ ለማን ይሰጥ? ለራስ ብቻ የሚሮጥበት ዘመን መሆኑን ካየን ዘንዳ ከዚህ ሌላ ምን ይባላል? አንዳችን ያለ ሌላችን መኖር እንደማንችል እያወቅነው ‘እኔ’ን ብቻ ላማከለ ነፍስ መሮጣችን ይገርመኛል። የሚገርማችሁ ደግሞ አባባልን እንኳ መርጠን አለመጠቀማችን ነው። ለምሳሌ ‹‹ዘመኑ የውድድር ነው›› የሚለውን አባባል ለተቀደሰ ይሁን ለረከሰ ተግባር እንደምንጠቀምበት ሳንለይ ለሁለቱም እንዳሻን እንገለገልበታለን። አሁንማ ሙሰኛውም በሰሞነኛ ተቆጣጣሪዎች ሲያላግጥ ‘ዘመኑ የውድድር ነው’ ማለት ጀምሯል አሉ። ‹‹ውድድሩ ጤናማ ዕድገት ለማስመዝገብ ነው? ወይስ እንደተለመደው ጠልፎ ለመጣል ነው?›› ይሉኝ ነበር ባሻዬ ይኼን ጉድ ቢሰሙ፡፡ ሌባ ቀጪ አጥቶ ለሕዝብ አገልግሎት በሚውል ገንዘብ ደልቦ ሲንጎማለል ይውላል። ተጠቂው ሰፊው ሕዝብ አቧራ ለብሶ ለዕለት ጉርሱ ይማስናል። ፍትሕ የናፈቃት ዓለም። በየጥጋጥጉ ዲስኩር ብቻ ተለጥፎ ይነበባል! ይነበነባል! የባሻዬ ልጅ፣ ‹‹አሁንማ የሰለቸኝ መፈክር ማንበብ ነው፤›› አለኝ፡፡ ‹‹ለምን?›› ብለው፣ ‹‹በመፈክር ውስጥ የተሸጎጡ በርካታ ውሸቶች አሉ፤›› ሲለኝ የገዛ ሳቄ ጆሮዬን አደነቆረው፡፡ ባለፈው ሰሞን አንድ የመንደራችን ጎበዝ ተማሪ ‹‹እኔ ከእንግዲህ ወዲያ ትምህርት የሚባል በቃኝ አቅለሸለሸኝ፤›› ብሎ አቆመው

ድብልቅልቅ ስሜቶችን የፈጠረው የኢትዮጵያ የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባልነት

Image
በዮሐንስ አንበርብር ሰሞኑን ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች 18 አገሮችን በሥሩ ለሚገኘው የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል አድርጐ መርጧል፡፡ ኢትዮጵያ የምክር ቤቱ አባል ሆና መመረጧ በርካታ ኢትዮጵያውያንን አስደንቋል፤ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የኢትዮጵያን አባል መሆን በአገሪቱ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያላገናዘበ ሲሉ ተችተውታል፡፡ በሌላ በኩል የውጭ ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች አጋጣሚውን የወደዱት ቢመስልም የሰብዓዊ መብት ወቀሳቸው ግን ቀጥሏል፡፡ የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ባለፈው ሳምንት ባካሄደው ምርጫ 47 መቀመጫዎች ላሉት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤቱ 18 አባል አገሮችን በተተኪ አባልነት ለቀጣይ ሦስት ዓመታት እንዲያገለግሉ መምረጡን ይፋ አድርጓል፡፡ የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ የ193 አባል አገሮችን ድምፅ የያዘ ሲሆን፣ በሰብዓዊ መብቶች ካውንስል ውስጥ አባል ለመሆን ከ96 በላይ የሚሆኑ አባል አገሮችን ይሁንታ ማግኘት ይጠይቃል፡፡ ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ምርጫ ከኢትዮጵያ ጋር ሌሎች ስድስት የአፍሪካ አገሮችም ተመርጠዋል፡፡ እነዚህ የአፍሪካ አገሮች ያገኙት ድምፅ የተሻለ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ከ193 የጠቅላላ ጉባዔው አባላት ድምፅ የ178 አገሮችን ይሁንታ በማግኘት ምክር ቤቱን በአባልነት ተቀላቅላለች፡፡ ለሰብዓዊ መብቶች  መከበር የፀና እምነት መኖርና ለተግባራዊነታቸው መንቀሳቀስ፣ የተሻለ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝና ለዚህ የሚሠሩ ጠንካራ ተቋማት መኖር የምክር ቤቱ አባል ሆኖ ለመመረጥ ከሚያበቁ ዋነኛ መስፈርቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ምክር ቤቱ ለሰብዓዊ መብቶች መከበርና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲፈጠር በመላው የዓለም አገሮች ውስጥ የሚሠራ ነው፡፡ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓ

ሲዳማ ቡና ቅጣት ተላለፈበት

Image
•ፕሪሚየር ሊጉ ነገና ከነገ በስቲያ ቀጥሎ ይካሄዳል ሲዳማ ቡና እየተካሄደ በሚገኘው የ2005ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መለስ ዋንጫ ውድድር በአራተኛው ሣምንት ሲዳማ ቡና በሜዳው ይርጋለም ላይ አርባ ምንጭ ከነማን ባስተናገደበት ጨዋታ በተፈጠረው የዲሲፕሊን ጥሰት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቅጣት ተላልፎበታል። ፌዴሬሽኑ ያደረሰን ዘገባ እንደሚያመለክተው ውድድሩን የሚመራው የሊግ ኮሚቴ ከዲሲፕሊን ኮሚቴ የደረሰውን ሪፖርት ከገመገመ በኋላ ሲዳማ ቡና በስድስተኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ነገ በሜዳው ከሃዋሳ ጋር ሊያደርግ የነበረውን ጨዋታ በሌላ ገለልተኛ ሜዳ እንዲያካሂድ ወስኖበታል። ይህንንም ተከትሎ ሁለቱ ቡድኖች ይርጋለም ላይ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ የቦታና ሰዓት ለውጥ ተደርጎበት በአሰላ ስታዲየም ከቀኑ በስምንት ሰዓት የሚካሄድ ይሆናል። ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጪ የሆኑ ተግባራት የተመልካቾች ማነስ እያሳሰበው ለሚገኘው የዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መለስ ዋንጫን የበለጠ የሚያደበዝዙት በመሆኑ ክለቦች ደጋፊዎቻቸውንም ሆነ ተጫዋቾቻቸውን ለስፖርታዊ ጨዋነት መርሆዎች ተገዢ እንዲሆኑ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። የስድስተኛው ሣምንት የፕሪሚየር ሊጉ ውድድር ነገና ከነገ በስቲያ ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን፤ ሰባት ጨዋታዎችም ይከናወናሉ። አምስቱ ጨዋታዎች ነገ በአበበ ቢቂላና በክልል ከተሞች የሚደረጉ ሲሆን፤ ሁለቱ ደግሞ ሐሙስ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋሉ። በእዚሁ መሠረት ነገ ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል ኢትዮጵያ ቡና ከመከላከያ የሚያደርጉት ጨዋታ ትልቅ ትኩረት ስቧል። ሁለቱ ክለቦች በደረጃ ሠንጠረዡ በአንድ ነጥብ ተበላልጠው ስምንተኛና ዘጠንኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ መከላከያ በሰባት ነጥብ ስምንተኛ እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና