Posts

የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአማራ በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች በ1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወጪ የርብና ጊዳቦ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ እያካሄደ መሆኑን ገለጸ።

Image
አዲስ አበባ ህዳር 09/2005 የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአማራ በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች በ1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወጪ የርብና ጊዳቦ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ እያካሄደ መሆኑን ገለጸ። ግንባታው ሲጠናቀቅ 26 ሺህ ሄክታር የሚደርስ የመስኖ መሬትን ማልማት እንደሚያስችል ተገልጿል። የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ብዙነህ ቶልቻ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስተማማኝ የውኃ አቅርቦት እንዲኖር ለማስቻል የርብና የጊዳቦ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች የግድብ ግንባታ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በደቡብ ጎንደር ዞን በእብናትና ፋርጣ ወረዳዎች እንዲሁም በፎገራ ሜዳማ አካባቢ የሚገነባው የርብ ግድብ 234 ሜትር ኩብ ውኃ የመያዝ አቅም እንዳለው ገልጸዋል፡፡ የግድቡ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ 14 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ የማልማት አቅም የሚኖረው ሲሆን ከ28 ሺህ በላይ አባዎራዎቸን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡ በግድቡ ግንባታ ወቅት 400 ለሚደርሱ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የታቸለ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 75 ያህሉ ሴቶች መሆናቸውን ተናግረዋል። የርብ ግድብ ግንባታ አጠቃላይ ወጪ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መሆኑን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ የግድቡ ግንባታ በያዝነው ዓመት ሰኔ ወር እንደሚጠናቀቅ ገልጸዋዕል፡፡ በተመሳሳይም በኦሮሚያና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ክልሎች በሲዳማና ቦረና ዞን አዋሳኝ በሚገኙ ዓባያና ለኮዓባያ ወረዳዎች 117 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ የመያዝ አቅም ያለው የጊዳቦ የመስኖ ልማት ግድብ ፕሮጀክት በመገንባት ላይ እንደሚገኝ አቶ ብዙነህ አመልክተዋል፡፡ የግድቡ ግንባታ ሲጠናቀቅ 11 ሺህ 924 ሄክታር ማልማት የሚያስችል ሲሆን ከ79 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍልን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አስረ

የመጀመርያው የቡና ሙዚየም በመጠናቀቅ ላይ ነው

Image
በዮናስ አብይ በኢትዮጵያ የመጀመርያው ነው የተባለለትና ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ በደቡብ ክልል በቦንጋ ከተማ በመገንባት ላይ የሚገኘው ብሔራዊ የቡና ሙዚየም በቅርቡ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የቦንጋ ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡ ለ2000 ዓ.ም. የሚሊኒየም በዓል ተቋቁሞ የነበረው የበዓሉ አስተባባሪ ሴክሬተሪያት ሥራው ከመጠናቀቁ በፊት ካሳለፋቸው ውሳኔዎች አንዱ፣ የቡናን ባህላዊና ታሪካዊ አመጣጥ የሚያሳይ ሙዚየም ስለመገንባት ነበር፡፡ ምንም እንኳ የሙዚየሙ ግንባታ ከዕቅዱ ቢዘገይም በጥቂት ወራት ውስጥ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት እንደሚጀምር የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ክፍሌ ገብረ ማርያም በተለይ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ እንደ አስተዳዳሪው ገለጻ፣ የሚሊኒየም አካባበር አስተባባሪ ኮሚቴው በወቅቱ ኃላፊነቱን ለደቡብ ክልል የሰጠ ቢሆንም፣ ክልሉ ደግሞ ግንባታውን የማስተባበርና የመከታተል ኃላፊነቱን ለዞኑ አስተዳደር ሰጥቷል፡፡ ሙዚየሙ ብሔራዊ እንዲሆን በመወሰኑ በጀቱን የፌዴራል መንግሥት እንዲመድብ በቅድሚያ ተወስኖ የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ግን ክልሉና ዞኑ እንዲሸፍኑ መደረጉን አክለው ገልጸዋል፡፡ ግንባታው ለምን እንደዘገየ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ክፍሌ በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹በወቅቱ የሚያስፈልገንን ያህል በጀት ማግኘት ባለመቻላችንና የግንባታ ዕቃ ባለማሟላታችን ነበር፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡ ሙዚየሙ ቋሚና ጊዜያዊ ኤግዚቢሽኖችን የሚያካትት ሲሆን፣ የዲዛይን ሥራው የገጠሪቱን ኢትዮጵያ ባህላዊ ቤቶችን እንዲያንፀባርቅ ተደርጐ የተሠራ ነው፡፡ በተጨማሪም ሙዚየሙ የአገሪቷን የቡና መገኛነት ከማንፀባረቁም ባሻገር የቡናን ባህላዊና ታሪካዊ ዳራና ሥነ ሥርዓት እንዲያሳይ ታስቦበት የተሠራ መሆኑን የዞኑ አስተዳዳሪ ያብራራሉ፡፡ ግንባታውን ታዬ አስፋው

የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባላት ወደ ግብፅ ሊጓዙ ነው

Image
በዮሐንስ አንበርብር ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ አባላትን ያካተተ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥትን በመወከል፣ ኢትዮጵያ የምትገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በዓባይ ወንዝ ላይ ምንም ጉዳት የሚያስከትል መሆኑን ለማስረዳት፣ የኢትዮጵያንና የግብፅን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር የሚል ተልዕኮ ይዞ ወደ ግብፅ ሊያቀና ነው፡፡ የዲፕሎማሲ ቡድኑ አባላት ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ ከታዋቂ ሰዎች፣ ከመገናኛ ብዙኅን፣ ከሥነ ጥበብና ከእምነት መሪዎች የተውጣጡ ሲሆን፣ በትናንትናው ዕለትም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝተው በተጠባባቂ ማኒስትሩ አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ገለጻ ተደርጐላቸዋል፡፡ ኢትዮጵያና ግብፅ የረዥም ዘመናት ግንኙነት ያላቸው አገሮች መሆናቸውን በመጥቀስ ገለጻቸውን የጀመሩት ተጠባባቂ ሚኒስትሩ፣ ይህ ግንኙነታቸው ከተፈጥሮና ከመንፈሳዊ እምነት ጋር የተዛመደ እንደሆነ አስታውሰዋል፡፡ በዚህ ረጅም ዘመን የሁለቱን አገሮች ግንኙነት የሚያስተሳስሩ በርካታ መልካም ነገሮች የመኖራቸውን ያህል፣ በተለያዩ ጊዜያት የተከሰቱ የፖለቲካ መሪዎችም ግንኙነታቸውን ሲያሻክሩና ጠባሳ ለመፍጠር ሲሞክሩ እንደነበር አስረድተዋል፡፡ ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘ በኋላ ግን ሁለቱ አገሮች ከዚህ ቀደም የነበራቸውን አለመግባባት ለመቅረፍ ጥረት መደረጉን የገለጹት ተጠባባቂ ሚኒስትሩ አምባሳደር ብርሃነ፣ እ.ኤ.አ. በ1993 የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ወደ ግብፅ በመሄድ የሥራ ጉብኝት ያደረጉ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ በዚህ ወቅትም አቶ መለስ መንግሥታቸው በዓባይ ጉዳይ ላይ መወያየትን እንደሚፈልግ በመግለጻቸው፣ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሁለቱ አገሮች ውይይት እንደተጀመረና በከፍተኛ ሁኔታ እንዳደገ ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ግብፆች ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ

Teddy’s “journey to love” Awassa Concert Full Report

Image
By Tibebeselassie Tigabu For many fans of Teddy Afro, traveling 277 km to Hawassa (Awassa) was not too much. Rather, it is a distance that they can travel easily to see and support the artist they love. It is not only from Addis Ababa that the fans of Teddy Afro went to Awassa. Folks from Moyale and Dilla were also at the concert. There are fans who drove their own cars but there are also those who travelled miles by using public transport to hear him live and to see their beloved artist on stage. On November 3, Awassa was different, bedecked with many posters and fliers of the concert. Especially at the gate of Haile Resort, a humongous poster of Teddy Afro in a white suit was posted. The whole town felt the vibe of the concert. Since it is the second concert after the release of the album, many were still waiting eagerly to see him live. The concert was held in the stadium and even before reaching the stadium the music welcomed people and attracted passersby. Around the

በኢትዮጵያ የከተሞች በዓል ላይ የሃዋሳ ከተማ ተሳትፎ

Image
ከተሞች ተሞክሯቸውን እየተለዋወጡ ናቸው   ዜና ሐተታ አዳማ እንግዶቿን ማስተናገድ ከጀመረች ቀናትን አስቆጥራለች። ማዕዷን እያቋደሰች የምትገኘዋ አዳማ ገፅታዋን ለማስተዋወቅ የአራተኛው የከተሞች ሣምንት ኤግዚቢሽን ተሣታፊ ነች። ለሰባት ተከታታይ ቀናት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ የቆየው ኤግዚቢሽን 136 ያህል ከተሞች ወደ አዳማ ያመጣቸውን መገለጫዎቻቸውን በድንኳን በድንኳን ሆነው ራሳቸውን እያስተዋወቁ ናቸው። የአዳማና ዙሪያዋ ከተሞች በርካታ ነዋሪዎች ኢግዜቢሽኑን ይጐበኛሉ። ነዋሪዎቹ አዳማ በዘንድሮው የከተሞች ውድድር አንደኛ እንደምትወጣ ይገልፃሉ። የከተማዋን ገፅታ በኤግዚቢሽኑ እያስጎበኙ የሚገኙ አካላትም ይህንኑ ያጠናክራሉ። አቶ ዘላለም አስራት የአዳማ ከተማን ገፅታ ለማሳየት በተዘጋጀው ድንኳን ውስጥ ስለቀረቡት የተለያዩ ዝግጅቶች ሲያብራሩ «የአዳማ ከተማን ማስተዋወቅ ያስፈለገው ከከተሞች ሁሉ በመሪነት ቦታ ላይ እንድትቀመጥ ታስቦ ነው» ይላሉ። እንደ አቶ ዘላለም ማብራሪያ፤ የአዳማ ከተማ ከ63 ሺ በላይ አባላትን ያቀፉ ከ4ሺ 73 በላይ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አሏት። ከ280 ኪሎ ሜትር በላይ መንገዷ በአስፋልትና በኮብልስቶን ተሸፍኗል። ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል የሚያንቀሳቀሱ ከ700 በላይ ባለሀብቶች ይገኙባታል። አዳማ በቀን 45 ሺ የሚሆኑ ሕዝብ ገብቶ የሚወጣበት 7ሺ ያህል ሰዎች ደግሞ የሚያድሩባት ናት። 8ሺና ከዛ በላይ እንግዶችን ሊያስተናግዱ የሚችሉ የተለያዩ የስብሰባ ማዕከላት ያሏት ስትሆን። ይህም ከተማዋን የኮንፈረንስ ከተማ አሰኝቷታል። ለኢንዱስትሪ፣ ለአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ለሪልስቴት፣ ለጤና፣ ለትምህርትና ለተለያዩ ዘርፎች የሚውል 128ነጥብ 70 ሔክታር መሬት ለልማት ማዘጋጀቷንም አቶ ዘላለም ይጠቁማሉ።  የ