Posts

የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባላት ወደ ግብፅ ሊጓዙ ነው

Image
በዮሐንስ አንበርብር ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ አባላትን ያካተተ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥትን በመወከል፣ ኢትዮጵያ የምትገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በዓባይ ወንዝ ላይ ምንም ጉዳት የሚያስከትል መሆኑን ለማስረዳት፣ የኢትዮጵያንና የግብፅን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር የሚል ተልዕኮ ይዞ ወደ ግብፅ ሊያቀና ነው፡፡ የዲፕሎማሲ ቡድኑ አባላት ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ ከታዋቂ ሰዎች፣ ከመገናኛ ብዙኅን፣ ከሥነ ጥበብና ከእምነት መሪዎች የተውጣጡ ሲሆን፣ በትናንትናው ዕለትም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝተው በተጠባባቂ ማኒስትሩ አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ገለጻ ተደርጐላቸዋል፡፡ ኢትዮጵያና ግብፅ የረዥም ዘመናት ግንኙነት ያላቸው አገሮች መሆናቸውን በመጥቀስ ገለጻቸውን የጀመሩት ተጠባባቂ ሚኒስትሩ፣ ይህ ግንኙነታቸው ከተፈጥሮና ከመንፈሳዊ እምነት ጋር የተዛመደ እንደሆነ አስታውሰዋል፡፡ በዚህ ረጅም ዘመን የሁለቱን አገሮች ግንኙነት የሚያስተሳስሩ በርካታ መልካም ነገሮች የመኖራቸውን ያህል፣ በተለያዩ ጊዜያት የተከሰቱ የፖለቲካ መሪዎችም ግንኙነታቸውን ሲያሻክሩና ጠባሳ ለመፍጠር ሲሞክሩ እንደነበር አስረድተዋል፡፡ ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘ በኋላ ግን ሁለቱ አገሮች ከዚህ ቀደም የነበራቸውን አለመግባባት ለመቅረፍ ጥረት መደረጉን የገለጹት ተጠባባቂ ሚኒስትሩ አምባሳደር ብርሃነ፣ እ.ኤ.አ. በ1993 የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ወደ ግብፅ በመሄድ የሥራ ጉብኝት ያደረጉ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ በዚህ ወቅትም አቶ መለስ መንግሥታቸው በዓባይ ጉዳይ ላይ መወያየትን እንደሚፈልግ በመግለጻቸው፣ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሁለቱ አገሮች ውይይት እንደተጀመረና በከፍተኛ ሁኔታ እንዳደገ ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ግብፆች ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ

Teddy’s “journey to love” Awassa Concert Full Report

Image
By Tibebeselassie Tigabu For many fans of Teddy Afro, traveling 277 km to Hawassa (Awassa) was not too much. Rather, it is a distance that they can travel easily to see and support the artist they love. It is not only from Addis Ababa that the fans of Teddy Afro went to Awassa. Folks from Moyale and Dilla were also at the concert. There are fans who drove their own cars but there are also those who travelled miles by using public transport to hear him live and to see their beloved artist on stage. On November 3, Awassa was different, bedecked with many posters and fliers of the concert. Especially at the gate of Haile Resort, a humongous poster of Teddy Afro in a white suit was posted. The whole town felt the vibe of the concert. Since it is the second concert after the release of the album, many were still waiting eagerly to see him live. The concert was held in the stadium and even before reaching the stadium the music welcomed people and attracted passersby. Around the

በኢትዮጵያ የከተሞች በዓል ላይ የሃዋሳ ከተማ ተሳትፎ

Image
ከተሞች ተሞክሯቸውን እየተለዋወጡ ናቸው   ዜና ሐተታ አዳማ እንግዶቿን ማስተናገድ ከጀመረች ቀናትን አስቆጥራለች። ማዕዷን እያቋደሰች የምትገኘዋ አዳማ ገፅታዋን ለማስተዋወቅ የአራተኛው የከተሞች ሣምንት ኤግዚቢሽን ተሣታፊ ነች። ለሰባት ተከታታይ ቀናት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ የቆየው ኤግዚቢሽን 136 ያህል ከተሞች ወደ አዳማ ያመጣቸውን መገለጫዎቻቸውን በድንኳን በድንኳን ሆነው ራሳቸውን እያስተዋወቁ ናቸው። የአዳማና ዙሪያዋ ከተሞች በርካታ ነዋሪዎች ኢግዜቢሽኑን ይጐበኛሉ። ነዋሪዎቹ አዳማ በዘንድሮው የከተሞች ውድድር አንደኛ እንደምትወጣ ይገልፃሉ። የከተማዋን ገፅታ በኤግዚቢሽኑ እያስጎበኙ የሚገኙ አካላትም ይህንኑ ያጠናክራሉ። አቶ ዘላለም አስራት የአዳማ ከተማን ገፅታ ለማሳየት በተዘጋጀው ድንኳን ውስጥ ስለቀረቡት የተለያዩ ዝግጅቶች ሲያብራሩ «የአዳማ ከተማን ማስተዋወቅ ያስፈለገው ከከተሞች ሁሉ በመሪነት ቦታ ላይ እንድትቀመጥ ታስቦ ነው» ይላሉ። እንደ አቶ ዘላለም ማብራሪያ፤ የአዳማ ከተማ ከ63 ሺ በላይ አባላትን ያቀፉ ከ4ሺ 73 በላይ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አሏት። ከ280 ኪሎ ሜትር በላይ መንገዷ በአስፋልትና በኮብልስቶን ተሸፍኗል። ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል የሚያንቀሳቀሱ ከ700 በላይ ባለሀብቶች ይገኙባታል። አዳማ በቀን 45 ሺ የሚሆኑ ሕዝብ ገብቶ የሚወጣበት 7ሺ ያህል ሰዎች ደግሞ የሚያድሩባት ናት። 8ሺና ከዛ በላይ እንግዶችን ሊያስተናግዱ የሚችሉ የተለያዩ የስብሰባ ማዕከላት ያሏት ስትሆን። ይህም ከተማዋን የኮንፈረንስ ከተማ አሰኝቷታል። ለኢንዱስትሪ፣ ለአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ለሪልስቴት፣ ለጤና፣ ለትምህርትና ለተለያዩ ዘርፎች የሚውል 128ነጥብ 70 ሔክታር መሬት ለልማት ማዘጋጀቷንም አቶ ዘላለም ይጠቁማሉ።  የ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ከተሞች የህዳሴ ጉዞ በትክክለኛ አቅጣጫ ላይ እንደሚገኝ ገለፁ

Image
“ከተሞች የኢንዱስትሪያሊስቶች መፍለቂያ ማዕከል በመሆን የመለስን ራዕይ ያሳካሉ” በሚል መርህ በአዳማ ሲካሄድ የቆየው 4ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ሳምንት ተጠናቋል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በዓሉ በከተሞች መካከል የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የሚያስችል እና ጠንካሮችን በማበረታታት በዘርፉ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ንቅናቄ መፍጠር የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡ የከተሞች የህዳሴ ጉዞ በትክክለኛ አቅጣጫ ላይ ይገኛል ያሉት አቶ ደመቀ በማደግ ላዩ ያሉ ከተሞችን ወደ ላቀ የልማት ደረጃ ለማሸጋገር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሊረባረቡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ በገጠር እየተመዘገበ ያለው የልማት ውጤት በከተሞች እየታየ ላለው መጠነ ሰፊ ለውጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል ብለዋል፡፡ ከተሞችንና ገጠሮችን አስተሳስሮ መሄድ ቀጣይ የመንግስት አቅጣጫ መሆኑንም ነው አቶ ደመቀ የተናገሩት፡፡ በ4ኛው የከተሞች ሳምንት ለሰባት ቀናት በቆየው ኤግዚቢሽን ላይ በተለያዩ የከተማ ልማት መስኮች ያከናወኗቸውን ተግባራት እና እራሳቸውን በማስተዋወቅ ከየምድባቸው ላቅ ያለ አፈፃፃም ያስመዘገቡ ከተሞች ተሸልመዋል፡፡ በተለይም በስድስት ቁልፍ የከተማ ልማት ስራዎች የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮችም በ4ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ሳምንት ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስራዎች የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል፣ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የትግራይ ክልል ከአንድ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ሲይዙ በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ስራዎች ደግሞ የትግራይ ክልል አንደኛ፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛ እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አሸናፊ ሆነዋል፡፡

የሲዳማ ሕዝቦች አርነት ንቅናቄን ጨምሮ የዘንድሮ ምርጫ ተቃዋሚ ፓርቲዎችንና ምርጫ ቦርድን ማወዛገብ ጀመረ

በታምሩ ጽጌ በሚያዝያ ወር 2005 ዓ.ም. የሚደረገው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤትና የአካባቢ ምርጫ ከወዲሁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድንና የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማወዛገብ ጀመረ፡፡ ቦርዱ ጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓ.ም. “የምርጫ ሰሌዳ የምክክር መድረክ” በሚል በአዳማ ከተማ በተደረገው ውይይት፣ በወቅቱ ከተሳተፉት 66 የፖለቲካ ፓርቲዎች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት፣ ቦርዱ ካዘጋጀው የመወያያ ርዕሰ ጉዳይ ውጭ የተለያዩ ጥያቄዎችን ማንሳታቸውንና ምላሽ ማጣታቸውን ተከትሎ አለመግባባት ተፈጥሯል፡፡  ቦርዱ ከምርጫ ሰሌዳው በኋላ በሚወጡ የምርጫ የማስፈጸሚያ ደንቦችና መመርያዎችን ረቂቅ አዘጋጅቶ ፓርቲዎቹን ለማወያየት በጠራው የውይይት መድረክ ላይ፣ 41 የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተስማሙበትንና መስተካከል እንዳለበት ያመኑበትን ጥያቄ ማቅረባቸውን፣ በ34 ፓርቲዎች የተወከለውና ሰባት አባላት ያሉት ጊዜያዊ ኮሚቴ ጥቅምት 30 ቀን 2005 ዓ.ም. አስታውቋል፡፡  “በምርጫ ሰሌዳ ዙርያ ከመወያየታችን በፊት የአገሪቱ የፖለቲካ ምኅዳር መጥበብና የምርጫ ውድድር ሜዳው የተስተካከለ አለመሆን፣ ቀደም ብሎ የተደረጉ ምርጫዎች በአፈጻጸም ችግሮች የተተበተቡ መሆቸውን፣ በየደረጃው ያሉ የምርጫ ቦርድ አመራርና አስፈጻሚዎች ተዓማኒነትና ተቀባይነት ላይ ቅድሚያ ሰጥተን ብንወያይ ይገባል፤” የሚል ጥያቄ ከኢሕአዴግና አጋር የፖለቲካ ድርጅቶች ውጭ ያሉት 41 የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች ጥያቄ ማንሳታቸውን ኮሚቴው አስታውሷል፡፡  አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ ሰማያዊ ፓርቲ፣ የጌዴኦ ሕዝቦች ንቅናቄ፣ የከንባታ ሕዝቦች ኮንግረንስ፣ የሲዳማ ሕዝቦች አርነት ንቅናቄን ጨምሮ 34 የፖለቲካ ፓርቲዎች ከላይ ያነሷቸው ጥያቄዎች