Posts

በሲዳማ ዞን 25 የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ይካሄዳል

Image
አዋሳ ህዳር 6/2005 በሲዳማ ዞን የሚሊኒየሙን የልማት ግብ ለማሳካት በበጀት ዓመቱ ከ89 ሚልዮን ብር በሚበልጥ በጀት 25 የመጠጥ ውሃ ፐሮጀክት ግንባታ እንደሚካሄድ የዞኑ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ገለጸ፡፡ የመምሪያው ሃላፊ አቶ አብሩ ዳቃሞ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ከፕሮጀክቶቹ መካከል 20ዎቹ ጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮ ቀሪዎቹ ማከፋፈያ፣ የማጠራቀሚያ ጋን፣ የውሃ ቦኖና ምንጭ ማጎልበት ናቸው፡፡ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶቹ የሚሰሩት በመንግስት፣ በዋሽ፣ በዩኒሴፍ ፕሮግራምና በህብረተሰብ ተሳተፎ መሆኑን ጠቁመው ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡ ፕሮጀክቶቹ በተያዘው የበጀት ዓመት መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቀው አገልገሎት እንዲሰጡ ከዞን ምክር ቤት ጀምሮ በየደረጃው ለሚገኙ አመራር አካላትና ህብረተሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ የፕሮጀክቶቹ ግንባታ ሲጠናቀቅ ከ380ሺህ የሚበልጡ የዞኑ ነዋሪዎች የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶቹ በዞኑ 50 በመቶ ላይ የነበረውን አጠቃላይ የዞኑን የመጠጥ ውሃ ሽፋን ወደ 62 በመቶ እንደሚያሳድግ ገልጸዋል፡፡ በዞኑ ወረዳዎች በሚገኙ 32 ቀበሌዎች ለ2006 የበጀት ዓመት ከመንግስት በተመደበ 75 ሺህ ብር 312 ፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይን ስራ 24 ተቋማት የጣራ ላይ ውሃ ማሰባሰብ፣ 2ሺህ ነባር ተቋማትን መልሶ የማደራጀት ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡ የቦርቻ፣ አለታ ወንዶና አለታ ጩኮ ወረዳ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት መጠጥ ውሃ ፍለጋ ረጅም ርቀት በመጓዝ ያባክኑት የነበረውን ጊዜ ለልማት በማዋል ምርትና ምርታማነታቸውን ለመጨመር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ በ2004 በዞኑ አስራ ሁለት ወ

የሁለት ብሄሮችን ግጭት ማስተዳደር አቅቶኛል ያሉ ሰውዬ በየትኛው ቀመር የ80 ብሄሮች ቀንበር ይሸከማሉ ???

ጥቅምት 10 2005 ዓ.ም. ለንባብ የበቃው የሪፖርተር ጋዜጣ ልዩ ዕትም ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የኋላ ታሪክ ሰፊ ሽፋን ሰጥቶ ብቅ ማለቱ ይታወሳል፡፡ የዘገባውን ተኣማኒነት ለማጎልበት ጋዜጣው የጠቅላይ ሚኒስትሩን የቀድሞ የሥራ ባልደረቦችንና ወዳጆች አግኝቶ ለማነጋገር ብዙ የደከመ ይመስላል፡፡  ሆኖም ግን ሪፖርተር ጋዜጣ የአቶ ኃይለማሪያምን ጠንካራ ጎን ለመዳሰስ ባደረገው ጥረት፤የጠቅላይ ሚኒስትሩን የመጠቅለል ብቃትን በጥርጣሬ ዓይን የሚያዩ  ወገኖች በግብዓትነት ሊጠቀሙበት የሚችሉትን መረጃዎችን ሳያቀብል አልቀረም፡፡  በእኔ እምነት ዘገባው አንባቢያን ዘንድ ሲደርስ በአዘጋጆቹ ዘንድ ፈጽሞ ያልተጠበቀን ትርጉም (unintended interpretation) የመስጠት አቅም አለው፡፡ ለምሳሌ አንዳንድ ወገኖች የአቶ ኃይለማሪያምን ከደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል ርዕሰ መስተዳደርነት ወደ ቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ቤተመንግስት ለመዛወራቸው በመንስኤነት የሚያስቀምጡት የአመራር ብቃታቸውን ማነስ ነው፡፡  ሪፖርተር ጋዜጣም ይህንኑ ግምት የሚያጠናክር መረጃን ነበር ይዞ ብቅ ያለው፡፡ የአቶ ኃይለማሪያም የእምነት ተምሳሌትና አማካሪ (Informal adviser) የነበሩ ቢሾፕ ሕዝቅኤል የሲዳማና የወላይታ ግጭት የአቶ ኃይለማሪያም አመራርን ክፉኛ ተፈታትኖት እንደነበረ በጋዜጣው ላይ በግልጽ ተናግረዋል፡፡  ጋዜጣው የቢሾፑን ምላሽ ያስቀመጠው እንደዚህ ነው፦ “አንድ ጊዜ በዚህ በሐዋሳ ጉዳይ አሁን አስቸጋሪውን ጉዳይ ለመወጣት እየሞከርኩ ነው ያለሁትና ጸልዩልኝ ብሎኝ ነበር፤የሚሉት ቢሾፑ አቶ ኃይለማሪያም እንዴት ከክልል ወደ ፌደራል መንግስት በአቶ መለስ ዜናዊ ጥሪ መሠረት እንደሄዱ ያብራራሉ…..” በዚህ ጉዳይ ላይ በጣ

በደቡብ ክልል ከሲዳማ ብሄረሰብ ውጪ ፕሬዚዳንት ለማድረግ ኣይሞከርም ተባለ፤ ኣቶ አባተ ኪሾን መልሶ ለመሾም ውስወሳ ተጀምሯል

Image
ኢህአዴግ በፖለቲካ ወለምታ ውስጥ!! ኢህአዴግ በ“ፖለቲካ ወለምታ” ውስጥ እንደሚገኝ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የኢህአዴግ ዲፕሎማት ለጎልጉል ተናገሩ። በከፊል ኢህአዴግን የተለዩ የሚስሉት ዲፕሎማት በጎልጉል የቅርብ ሰው አማካይነት ድምጻቸው ሳይቀረጽ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት የተፈጠረው የፖለቲካ ወለምታ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል አመልክተዋል። የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት በመካከለኛ አመራሩ ውስጥ የመጠራጠር ስሜት መፈጠሩን በፓርቲ ግምገማ ላይ በግልጽ መናገራቸው የዲፕሎማቱን አስተያየት የሚያጠናክር ሆኖ ተገኝቷል። የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የአቶ መለስን ሞት ደብቀው በመያዝና ማስተባበያ በመስጠት ጊዜ የወሰዱት ይኸው የተባለው የፖለቲካ ወለምታ እንዳይፈጠር ለማድረግ በማሰብ እንደነበር ዲፕሎማቱ ያስታውሳሉ። ይሁን እንጂ አቶ መለስ ሁሉንም ጉዳይና ሃላፊነት ብቻቸውን ይዘውት ስለነበር በድንገት ማለፋቸው ፓርቲው ውስጥ አሁን በየደረጃው የሚታየው የመተርተር አደጋ መከላከል ግን አልተቻለም። የፖለቲካ ወለምታ ስለመከሰቱ ማንም ማስተባበያ ሊያቀርብ አይችልም የሚሉት ዲፕሎማት በእርሳቸው እይታና ባላቸው መረጃ መሰረት ድርጅትን መክዳት፣ ድርሻዬ በሚል ገንዘብ ማሰባሰብ፣ ቤተሰብን በተለያዩ ምክንያቶች ማሸሽ፣ በቁልፍ የመከላከያ ሃላፊዎች ላይ ማነጣጠር፣ በግምገማ  ስም ካድሬውን ማመስ፣ በስልጠና ስም የበታች አመራሮችን መደለል፣ ከሁሉም በላይ ማንኛውም ውሳኔ ሲወሰን በተናጠል እንዳይሆን የሚከለክል አሰራር መከተል የመሳሰሉት ተፈጠረ ለተባለው “ወለምታ” ዋና መግለጫዎች ናቸው። ፓርቲያቸው ኢህአዴግ የመለሰን ምስል እየለጠፈ “የታላቁን መሪ ውርስ ሳይበረዝ እናስቀጥላለን” የሚለው ውሸት እንደሆነ በመግለጽ ተጨማሪ ማሳያ የሚ

በሲዳማ ዞን የ10 ሆስፒታሎች ግንባታ ተጀመረ

Image
አዋሳ (ኢዜአ)፦ በጤናው መስክ የሚሌኒየሙን ግብ ለማሳካት በሲዳማ ዞን ከ210 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የ10 ሆስፒታሎች ግንባታ መጀመሩን የዞኑ ጤና መምሪያ ገለጸ፡፡ የመምሪያው የልማት ዕቅድ ዝግጅትና ክትትል የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አክሊሉ ዮሐንስ ትናንት እንደገለጹት ፤ በጤናው መስክ በዞኑ የተቀናጀ ጥረት በመደረግ ላይ ነው፡፡ በ2004 በጀት ዓመት መጨረሻ ግንባታቸው የተጀመሩት እነዚህ ሆስፒታሎች በዞኑ በሚገኙ 10 ወረዳዎች መሆኑን ጠቁመው፤ በዞኑ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ተግባራት ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል። ከአምስት ዓመታት ወዲህ ሁሉም የባለድርሻ አካላት ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት የጤና ጣቢያዎች ቁጥር ብቻ ከ16 ወደ 104 ማደጉን ገልጸዋል፡፡ ከግሎባል ፈንድ በተገኘ በጀት በመገንባት ላይ ያሉ ሆስፒታሎች ለአገልግሎት ሲበቁ በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ከዚህ በፊት ረጅም መንገድ ተጉዘው የሚያገኙትን የጤና አገልግሎት በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ ከማስቻሉም ሌላ የእናቶችና ህፃናት ሞት በመቀነስ የሚሌኒየሙን ግብ ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ የሆስፒታሎቹ ግንባታ በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ በመጠናቀቅና የውስጥ ድርጅቱ ተሟልቶ ለአገልግሎት እንደሚበቁ የተናገሩት አቶ አክሊሉ፤ በዞኑ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ የጤና ሽፋኑም ቀደሞ ከነበረበት 86 በመቶ ወደ 97 በመቶ እንዲሁም የሆስፒታሎች ቁጥርም ከ5 ወደ 15 እንደሚያሳድግ ተናግረዋል፡፡ መከላከልን መሰረት ያደረገውን የጤና ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ በዞኑ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች በ482 ጤና ኬላዎች 1032 የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ተመድበው በጤናው መስክ

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በይርጋዓለም ከተማ አዲስ ካምፓስ ከፈተ

Image
ሀዋሳ (ኢዜአ)፦ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቅበላ አቅሙን ለማሳደግ በይርጋዓለም ከተማ በ55 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባው አዲሱ የአዋሳ ካምፓስ ትናንት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ ካምፓሱን መርቀው የከፈቱት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የዩኒቪርሲቲው አስተዳደር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ናቸው፡፡ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሴፍ ማሞ በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ እንደገለጹት፤ የዩኒቨርሲቲውን የቅበላ አቅም ለማሳደግ ከሚካሄዱ የማስፋፊያ ግንባታዎች አንዱ አካል የሆነው አዲሱ የአዋሳ ካምፓስ በ65 ሄክታር ቦታ ላይ ያረፈ ነው፡፡ በ2002 ዓ.ም ተጀምሮ በአሁኑ ወቅት የተጠናቀቀው ይኸው ካምፓስ ለ800 ተማሪዎች የመኝታ አገልግሎት የሚሰጥ ዘመናዊ ህንፃ ፣ የመማሪያና ሌሎችም ክፍሎችን የያዘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ካምፓሱ በአሁኑ ወቅት በአካውንቲንግ፣ በማኔጅመንት፣ በኢኮኖሚክስና፣ በኮፕሬቲቭስ ዘርፍ በመጀመሪያ ዲግሪ የተቀበላቸውን 580 ተማሪዎችን በመመዝገብ ለማስተማር መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በዚሁ አዲስ ካምፓስ በ38 ሚሊዮን ብር ወጪ የተጀመሩ የአስተዳደር ቢሮዎች፣ የተማሪዎች መመገቢያ፣ ቤተመጻሕፍትና የመምህራን መኖሪያ ግንባታ በቅርቡ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ዶክተር ዮሴፍ አመልክተው፤ የካምፓሱን የቅበላ አቅም በማገናዘብ ሌሎች የማስፋፊያ ግንባታዎች ለማካሄድ 320 ሚሊዮን ብር መመደቡን ጠቁመዋል፡፡ አዲሱን ካምፓስ እንዲከፈት ድጋፍ ላደረጉ ለክልሉ፣ ለሲዳማ ዞን፣ ለዳሌ ወረዳና ለይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር፣ ለአካባቢው ማህበረሰብና ለሌሎችም ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡  የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ካምፓሱን መርቀው ከከፈቱ በኋላ እንደ