Posts

በደቡብ ክልል ከሲዳማ ብሄረሰብ ውጪ ፕሬዚዳንት ለማድረግ ኣይሞከርም ተባለ፤ ኣቶ አባተ ኪሾን መልሶ ለመሾም ውስወሳ ተጀምሯል

Image
ኢህአዴግ በፖለቲካ ወለምታ ውስጥ!! ኢህአዴግ በ“ፖለቲካ ወለምታ” ውስጥ እንደሚገኝ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የኢህአዴግ ዲፕሎማት ለጎልጉል ተናገሩ። በከፊል ኢህአዴግን የተለዩ የሚስሉት ዲፕሎማት በጎልጉል የቅርብ ሰው አማካይነት ድምጻቸው ሳይቀረጽ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት የተፈጠረው የፖለቲካ ወለምታ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል አመልክተዋል። የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት በመካከለኛ አመራሩ ውስጥ የመጠራጠር ስሜት መፈጠሩን በፓርቲ ግምገማ ላይ በግልጽ መናገራቸው የዲፕሎማቱን አስተያየት የሚያጠናክር ሆኖ ተገኝቷል። የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የአቶ መለስን ሞት ደብቀው በመያዝና ማስተባበያ በመስጠት ጊዜ የወሰዱት ይኸው የተባለው የፖለቲካ ወለምታ እንዳይፈጠር ለማድረግ በማሰብ እንደነበር ዲፕሎማቱ ያስታውሳሉ። ይሁን እንጂ አቶ መለስ ሁሉንም ጉዳይና ሃላፊነት ብቻቸውን ይዘውት ስለነበር በድንገት ማለፋቸው ፓርቲው ውስጥ አሁን በየደረጃው የሚታየው የመተርተር አደጋ መከላከል ግን አልተቻለም። የፖለቲካ ወለምታ ስለመከሰቱ ማንም ማስተባበያ ሊያቀርብ አይችልም የሚሉት ዲፕሎማት በእርሳቸው እይታና ባላቸው መረጃ መሰረት ድርጅትን መክዳት፣ ድርሻዬ በሚል ገንዘብ ማሰባሰብ፣ ቤተሰብን በተለያዩ ምክንያቶች ማሸሽ፣ በቁልፍ የመከላከያ ሃላፊዎች ላይ ማነጣጠር፣ በግምገማ  ስም ካድሬውን ማመስ፣ በስልጠና ስም የበታች አመራሮችን መደለል፣ ከሁሉም በላይ ማንኛውም ውሳኔ ሲወሰን በተናጠል እንዳይሆን የሚከለክል አሰራር መከተል የመሳሰሉት ተፈጠረ ለተባለው “ወለምታ” ዋና መግለጫዎች ናቸው። ፓርቲያቸው ኢህአዴግ የመለሰን ምስል እየለጠፈ “የታላቁን መሪ ውርስ ሳይበረዝ እናስቀጥላለን” የሚለው ውሸት እንደሆነ በመግለጽ ተጨማሪ ማሳያ የሚ

በሲዳማ ዞን የ10 ሆስፒታሎች ግንባታ ተጀመረ

Image
አዋሳ (ኢዜአ)፦ በጤናው መስክ የሚሌኒየሙን ግብ ለማሳካት በሲዳማ ዞን ከ210 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የ10 ሆስፒታሎች ግንባታ መጀመሩን የዞኑ ጤና መምሪያ ገለጸ፡፡ የመምሪያው የልማት ዕቅድ ዝግጅትና ክትትል የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አክሊሉ ዮሐንስ ትናንት እንደገለጹት ፤ በጤናው መስክ በዞኑ የተቀናጀ ጥረት በመደረግ ላይ ነው፡፡ በ2004 በጀት ዓመት መጨረሻ ግንባታቸው የተጀመሩት እነዚህ ሆስፒታሎች በዞኑ በሚገኙ 10 ወረዳዎች መሆኑን ጠቁመው፤ በዞኑ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ተግባራት ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል። ከአምስት ዓመታት ወዲህ ሁሉም የባለድርሻ አካላት ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት የጤና ጣቢያዎች ቁጥር ብቻ ከ16 ወደ 104 ማደጉን ገልጸዋል፡፡ ከግሎባል ፈንድ በተገኘ በጀት በመገንባት ላይ ያሉ ሆስፒታሎች ለአገልግሎት ሲበቁ በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ከዚህ በፊት ረጅም መንገድ ተጉዘው የሚያገኙትን የጤና አገልግሎት በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ ከማስቻሉም ሌላ የእናቶችና ህፃናት ሞት በመቀነስ የሚሌኒየሙን ግብ ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ የሆስፒታሎቹ ግንባታ በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ በመጠናቀቅና የውስጥ ድርጅቱ ተሟልቶ ለአገልግሎት እንደሚበቁ የተናገሩት አቶ አክሊሉ፤ በዞኑ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ የጤና ሽፋኑም ቀደሞ ከነበረበት 86 በመቶ ወደ 97 በመቶ እንዲሁም የሆስፒታሎች ቁጥርም ከ5 ወደ 15 እንደሚያሳድግ ተናግረዋል፡፡ መከላከልን መሰረት ያደረገውን የጤና ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ በዞኑ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች በ482 ጤና ኬላዎች 1032 የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ተመድበው በጤናው መስክ

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በይርጋዓለም ከተማ አዲስ ካምፓስ ከፈተ

Image
ሀዋሳ (ኢዜአ)፦ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቅበላ አቅሙን ለማሳደግ በይርጋዓለም ከተማ በ55 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባው አዲሱ የአዋሳ ካምፓስ ትናንት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ ካምፓሱን መርቀው የከፈቱት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የዩኒቪርሲቲው አስተዳደር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ናቸው፡፡ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሴፍ ማሞ በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ እንደገለጹት፤ የዩኒቨርሲቲውን የቅበላ አቅም ለማሳደግ ከሚካሄዱ የማስፋፊያ ግንባታዎች አንዱ አካል የሆነው አዲሱ የአዋሳ ካምፓስ በ65 ሄክታር ቦታ ላይ ያረፈ ነው፡፡ በ2002 ዓ.ም ተጀምሮ በአሁኑ ወቅት የተጠናቀቀው ይኸው ካምፓስ ለ800 ተማሪዎች የመኝታ አገልግሎት የሚሰጥ ዘመናዊ ህንፃ ፣ የመማሪያና ሌሎችም ክፍሎችን የያዘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ካምፓሱ በአሁኑ ወቅት በአካውንቲንግ፣ በማኔጅመንት፣ በኢኮኖሚክስና፣ በኮፕሬቲቭስ ዘርፍ በመጀመሪያ ዲግሪ የተቀበላቸውን 580 ተማሪዎችን በመመዝገብ ለማስተማር መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በዚሁ አዲስ ካምፓስ በ38 ሚሊዮን ብር ወጪ የተጀመሩ የአስተዳደር ቢሮዎች፣ የተማሪዎች መመገቢያ፣ ቤተመጻሕፍትና የመምህራን መኖሪያ ግንባታ በቅርቡ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ዶክተር ዮሴፍ አመልክተው፤ የካምፓሱን የቅበላ አቅም በማገናዘብ ሌሎች የማስፋፊያ ግንባታዎች ለማካሄድ 320 ሚሊዮን ብር መመደቡን ጠቁመዋል፡፡ አዲሱን ካምፓስ እንዲከፈት ድጋፍ ላደረጉ ለክልሉ፣ ለሲዳማ ዞን፣ ለዳሌ ወረዳና ለይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር፣ ለአካባቢው ማህበረሰብና ለሌሎችም ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡  የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ካምፓሱን መርቀው ከከፈቱ በኋላ እንደ

አካል ጉዳተኞችን በማቋቋምና በመደገፍ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ማብቃት በሚል የክልሉ አካል ጉዳተኞች ማህበር ያዘጋጀው የኘሮጀክት ትውውቅ መድረክ በአለታ ወንዶ ወረዳ ተካሄደ፡፡

አቶ ባልጉዳ ጳውሎስ የአለታ ወንዶ ወረዳ አካል ጉዳተኞች ማህበር ሊቀመንበር እንዳሉት አካል ጉዳተኞች ካለባቸው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ተላቀው የበኩላቸውን  አስተዋፅኦ ለማበርከት የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የባለ ድርሻ አካላት ድጋፍና ትብብር ወሳኝ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ አቶ ተፈራ ጨመሳ የክልሉ አካል ጉዳተኞች ማህበር አማካሪ በበኩላቸው አካል ጉዳተኛችን ለማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ልማት ከማብቃት በተጨማሪ የአካል ጉዳተኛ ህፃናትን የትምህርት ተሳትፎ በማሳደግ የወደፊቱን የትውልድ ተስፋ እንዲያብብ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለአስሩ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ለእያንዳንዱ ተማሪ በወር 15ዐ ብር ለአስር ወራት ድጋፍ በማድረግ ለሁሉም ተማሪዎች 15 ሺህ ብር ተመድቦላቸው በመማር ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን እንደዘገበው፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/02HidTextN405.html

ባለፈው ዓመት በሁሉም የልማት እቅዶች አፈፃፀም ላይ የታዩ ክፍተቶችንና ውስንነቶችን ለመቅረፍ መዘጋጀቱን በሲዳማ ዞን የቡርሳ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የወረዳው ምክር ቤት 3ኛ ዙር 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ሲካሄድ ዋና አስተደደሪው አቶ አማረ ሻላሞ እንዳሉት  የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት ሁሉም የልማት እቅዶች በጠንካራና በተደራጀ የልማት ሰራዊት መመራት አለባቸው ብለዋል፡፡ በወረዳው በሚከናወነው የበልግና የመኸር እርሻ 7 ሺህ 831 ሄክታር መሬት በዋና ዋና ሰብሎች በመሸፈን 16 ሺህ 584 ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን ገልፀዋል፡፡ ለዚህም15 ሺህ 13ዐ ኩንታል ዳኘና ዩሪያ ማዳበሪያ እንዲሁም አሲዳማ አፈርን በማከም ለእርሻ ሥራ ለማዋል 2ዐዐ ኩንታል ኖራና የተለያዩ ሰብሎች 3 ሺህ 289 ኩንታል ምርጥ ዘር በግብዓትነት እንደሚሠራጭም አቶ አማረ አስረድተዋል፡፡ ጉባኤው ከ39 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በማፅደቅ መጠናቀቁንም የሲዳማ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ዘግቧል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/02HidTextN505.html