Posts

የሲዳማ ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄ

በ Hagerselam Haroressa ከማህበራዊ መረብ ላይ የተገኘ ጽሁፍ የሲዳማ ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄ መግቢያ አገራችን ለአያሌ ዘመናት ለተለያዩ ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ተጋልጣ የቆየች በመሆኗ አብዛኛው ህዝቧ በድህነት አረንቋና በኋላቀርነት ቀንበር ተተብትቦ መኖሩ የማይካድ ታሪካዊ ሀቅ ነው :: የሲዳማ ህዝብም የዚሁ አስከፊ ሰቆቃ ተጠቂ በመሆኑ ይህንን ነባራዊ ችግር ለመታገልና ለመፍታት ፈርጀ - ብዙ ትግል ማድረግ በማስፈለጉ፣ እንዲሁም የችግሩን መሠረታዊ ምንጭ አጉልቶ ለማሳየትና የመፍትሔውንም አቅጣጫ ለመጠቆም የሚያስችል የትግል ስልት ያካተተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጽሑፍ ለ ማዘጋጀት ተገደናል :: እንደሚታወቀው የሲዳማ ብሔር ባለፉት አፋኝ ፀረ - ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቶች ሥር ከመውደቁ በፊት የራሱ የሆነ ባሕላዊ የአስተዳደር ሥርዓት (The Luwa System) ፣ ቋንቋና (Sidaamu Afoo) ባህል፣ የራሱ የሆነ ታሪካዊ አመጣጥ ያለው ህዝብ ሆኖ በአንድ ጆኦግራፊያዊ ክልል ሰፍሮ የሚኖር በአንድ ስነልቦና የተሳሰረ ታላቅ ብሔር እንደሆነ ይታወቃል :: ይሁን እንጂ ህዝቡ በእነዚያ አስከፊና አፋኝ ፀረ - ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቶች ሥር ከወደቀ በኋላ በራሱ ማስተዳደር እንዳይችልና ነፃነት እንዳይኖረው ፣ በገዛ ክልሉ ሊኮራባቸው ቀርቶ በአደባባይ በቋንቋውና በባህሉ እንዳይጠቀምበት ይልቁንም እንዲያፍርበት ተደርጎ ቆይቷል ::  በአጠቃላይ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ልማት የበላይ ባለቤትነትና ተጠቃሚነት እንዳይኖረው በተለያዩ ሥውር ስልቶች ተከልክሎ ቆይቷል :: ከእነዚህ አስከፊና አፋኝ ፀረ - ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቶች ለመላቀቅ በየሥርዓቱ በተናጠል፣ በቡድንና በተደራጀ መልኩ ሳይታገል ያለፈበት አንድም ጊዜ አልነበረም :: በተለይ የንጉሣዊው ሥርዓ