Posts

የሐዋሳ ፍርድ ቤት በአንድ የወንጀል ድርጊት ሁለት የተለያዩ ቅጣቶችን መወሰኑ እያነጋገረ ነው

Image
-    በአንደኛው ቅጣት 10 ዓመት በሌላኛው ደግሞ ዕድሜ ልክ እስራት ወስኗል በታምሩ ጽጌ በደቡብ ክልል የሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአንድ ወጣት ላይ በተፈጸመ የግድያ ወንጀል በቀረቡለት የተለያዩ ክሶች ላይ የተለያዩ የቅጣት ውሳኔዎችን መስጠቱ እያነጋገረ ነው፡፡ ድርጊቱ የተፈጸመው አማረ ሙሉጌታ በተባለ የ23 ዓመት ወጣት ላይ በሐዋሳ ከተማ ሚያዝያ 5 ቀን 2003 ዓ.ም. ምሽት ላይ መሆኑን፣ ሁለቱም የክልሉ የከፍተኛ መርማሪ ከሳሾች ክሶች ያስረዳሉ፡፡ የከተማው ከፍተኛ መርማሪ ከሳሽ መጀመርያ ለሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 29 ቀን 2003 ዓ.ም. ክሱን ያቀረበ ሲሆን፣ ለክሱ መነሻ የሆነው ፍሬ ጉዳይ አማረ ሙሉጌታ በተባለ የ23 ዓመት ወጣት ላይ በሁለት ጓደኞቹ የተፈጸመን የግፍ አገዳደል ወንጀል የሚያስረዳ ነው፡፡ ከሳሽ በክሱ ላይ እንዳብራራው፣ ሟች አማረ ሚያዝያ 5 ቀን 2003 ዓ.ም. እስከ ሌሊቱ አጋማሽ ድረስ አፈወርቅ ሌሊሳና ውብሸት ደሞል ከሚባሉ ጓደኞቹ ጋር በተለያዩ ሬስቶራንቶችና ሆቴሎች ሲዝናኑ ያመሻሉ፡፡ ጓደኞቹ አስቀድመው በነበራቸው የመግደል ሐሳብ፣ ወጣቱን በተለያዩ መጠጥ ቤቶች በማዞርና በማጠጣት በስካር ራሱን እንዲስት ካደረጉት በኋላ፣ ወደ ሰዋራ ሥፍራ በመውሰድ ውብሸት የተባለው ጓደኛው ሲይዘው፣ ጌታሁን የተባለው ሌላኛው ጓደኛው በስለት የግራ ደረቱን እንደወጋው ክሱ ያብራራል፡፡ ጓደኞቹ ድርጊቱን ሌላ ሰው የፈጸመው ለማስመሰል ለመሞት በማጣጣር ላይ የነበረውን አማረ ሙሉጌታን በመሸከም አሴር ወደሚባል ሆስፒታል ቢወስዱትም፣ ሕክምና ሳይደረግለት ሕይወቱ ማለፉን የቅጣት ውሳኔው ሰነድ ያስረዳል፡፡ ጓደኞቹ በጥርጣሬ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበው በሰጡት ቃል፣ ጓደኛቸው መሆኑንና ለሦስት ዓመታት

Sidama Coffee and Arba Minch will clash in the southern state derby in Yirgalem.

Image
Addis Ababa, Ethiopia – Week 4 of the Ethiopia Premier League will continue here with current leaders Dedebit FC taking on Ethiopian Insurance; EEPCO hosting Adama and defending champions St. George entertaining newly promoted side, Ethiopian Water Works FC. Mugher Cement will face Harar Beer at home and Sidama Coffee and Arba Minch will clash in the southern state derby in Yirgalem. The league will continue on Monday with two matches featuring Ethiopian Coffee vs Hawassa and CBE vs Defence Force. After 3 matches, Dedebit and Harar Beer seat on top of the league with 7 points each, followed by EEPCO, Ethiopian Coffee and St. George FC. Week 4 Sunday, November 11 Dedebit v Insurance EEPCO v Adama Mugher v Harar Brewery Sidama Coffee v Arba Minch Water Works Sport v St George Monday, November 12: CBE v Defence Force Ethiopian Coffee v Awassa

ኢትዮጵያ ከቡና ለማግኘት ያሰበችውን ገቢ ለማሳካት በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ተቀናጅተው ለመሥራት ተስማሙ

Image
አዲስ አበባ ህዳር 1/2005 ኢትዮጵያ ከቡና በዚህ ዓመት ለማግኘት ያሰበችውን ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማሳካት በዘርፉ የተሰማሩ አካላት የተቀናጀ ጥረት እንደሚያደርጉ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የቡና ጉባዔ ተሳታፊዎች አረጋገጡ። በአዲስ አበባ ከተማ ላለፉት ሁለት ቀናት የተካሄደው ጉባዔ ተካፋዮች በማጠናቀቂያቸው ላይ እንደገለጹት የአገሪቱ ቡና በዓለም ገበያ ባለው ተቀባይነትና በተለይም ስፔሻሊቲ ቡና ባለው ተፈላጊነት ምርቱን በጥራትና በብዛት በማቅረብ በዕቅዱ የተያዘውን ገቢ ለማሟላት የጋራ ጥረት ያደርጋሉ። አገሪቱ ለዓለም ያበረከተችውን ቡና አልምታ ልትጠቀምባቸው የምትችላቸው ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉ ተሳታፊዎቹ አመልክተው፣የቡናውን ልዩ ባህርያት በመመርኮዝ ልማቱንና ግብይቱን በማሳደግ የተሻለ ገቢ ለማግኘት እንደሚቻል አስረድተዋል። ለዚህም ባለድርሻ አካላት ተገቢ ሚናቸውን እንዲወጡ በተቀናጀ መንገድ መንቀሳቀስ እንደሚገባቸውም አሳስበዋል። ጉባዔው በቡና ምርትና ግብይት ሂደት የተሰማሩ አካላትን በማሳበሰብ የኢትዮጵያን ቡና ሁኔታ የሚያሳውቅበት መልካም አጋጣሚ መፍጠሩን የኢትዮጵያ ኮፊ ኤክስፖርተርስ አሶሴሽን የቦርድ አባል አቶ ታደሰ መስቀላ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አስረድተዋል። ጉባዔው በቡናው ዘርፍ ያሉትን ችግሮችና መልካም አጋጣሚዎች በስፋት በመዳሰስ በቀጣይ መከናወን ያለባቸውን ተግባራት ለመለየት የሚያስችሉ ጥናታዊ ጽሁፎች እንደቀረቡበት አስታውቀዋል። ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ጉባዔው በየዓመቱ ኤግዚቢሽንና የመስክ ጉብኝትን በማካተት እስከ አራት ቀናት ቆይታ እንዲኖረው ለማድረግ ከስምምነት ላይ መደረሱን አቶ ታደሰ ተናግረዋል። ተሳታፊዎቹ ኢትዮጵያ ጥራቱ የተጠበቀ ቡና ተከታታይነት ባለው መንገድ ማቅረብ በምትችልበት፣የኢትዮጵያን ቡና በዓለም አቀፍ ገበያ ያ

ማሸነፍም መሸነፍም እንደ አሜሪካ ምርጫ!

Image
የኦባማ ማሸነፍና የኢህአዴግ 1ለ5 ስትራቴጂ ሚስታቸውን የሚወዱ መሪዎች እንፈልጋለን!በምርጫ 99 በመቶ ማሸነፍ ከመሸነፍ እኩል ነው!ከሁሉም በፊት መወያየት ያለብን የኢቴቪ ደባል ሆኖ ስለገባው የቻይና ኮሙኒስት መንግስት የቴሊቪዥን ጣቢያ /ሲሲቲቪ/ ነው፡፡ እንዴ --- እኔ እኮ እንዲህ አልመሰለኝም ነበር፡፡ ባለፈው ሰሞን  የቻይና ቴሊቪዥን ሃላፊዎች ከኢቴቪ ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት መፈራረማቸውን ስሰማ ትከሻዬን የከበደኝ ለካ ለዚህ ነው፡፡ በቃ ደስ አላለኝም ነበር፡፡ እናንተ ነገሩ ቀልድ እንዳይመስላችሁ - ቻይና በአጭር ጊዜ ውስጥ አፍሪካን በሙሉ ኮሙኒስት ካላደረገች ታዘቡኝ፡፡ አረ አያያዟ አያምርም! ኢህአዴግማ ደስታው ነው - በሰበቡ የኮሙኒስትነት አራራውን ይወጣብናል! /እንኳን ዘንቦብሽ --/  እኔ ግን ተናግሬአለሁ---አንድ ቀን አማን ነው ብለን ከእንቅልፋችን ስንነሳ እቺ ምስኪን አገር ኮሙኒስት ሆና እንዳትጠብቀን፡፡ የኢህአዴግን ባህል የማያውቁ የዋህ ዜጎች “እንዴ እኛ ሳንፈቅድ?” ሊሉ እንደሚችሉ እገምታለሁ /ሰውየው “ሚስትህ አረገዘች ወይ?” ቢሉት “ማንን ወንድ ብላ” አለ!/ የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት የአሁኑ የተቃዋሚ ፓርቲ ሊ/መንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ያሉትን አልሰማችሁም? “ኢህአዴግ አስር ዓመት ሙሉ ሶሻሊስት ነኝ ሲል ቆይቶ ድንገት ተነስቶ “ነጭ ካፒታሊዝም” ተከታይ ነኝ አለኝ” ብለው ክህደት እንደተፈፀመባቸው ተናግረዋል እኮ፡፡ ስለዚህ እንደሳቸው “ሰርፕራይዝድ” እንዳትሆኑ! ወዳጆቼ--- የስነልቦና ዝግጅት ማድረግ እኮ ቀላል በረከት አይደለም፡፡ እንደው ሌላው ቢቀር ድንገት ፌንት ከማድረግ ይታደጋል፡፡ እኔ የምለው--- ባለፈው ሳምንት ሲሲቲቪ በኢቴቪ ያሰራጨውን ዜና ሰማችሁልኝ? አንደኛው የቻይና ዳያስፖራዎች ወደ አገራቸው እየተመለ

34 ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው ፍትሃዊነት ላይ ጥያቄ አለን አሉ

Image
ኢህአዴግ ሚዲያውን ለምርጫ ቅስቀሣም ሆነ ፖሊሲውን በስፋት ለህዝቡ ለማድረስ እየተጠቀመበት እንደሆነና በፓርቲው ንብረትና በኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት መካከል ያለው ልዩነት እንደማይታወቅ በመግለፅ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ የሚያቀርቡትን አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ያሉት ኃላፊው፤ ህዝቡ ኢህአዴግን መንግስት አድርጐ ሲመርጥ ፖሊሲውን በስፋት እንዲያስተዋውቅ እውቅናና ይሁንታ ሰጥቶታል ብለዋል፡፡ በተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚቀርቡትን ቅሬታና አቤቱታዎች በጋራ ምክር ቤት እያዩ መፍትሔ እንደሚፈልጉና በተባለው ጉዳይ ግን የቀረበላቸው አንዳችም ቅሬታ አለመኖሩን አቶ ተመስገን ጨምረው ገልፀዋል፡፡    የምርጫ ሥነ ምግባር ህግ ከፈረማችሁ በኋላ የዚህ ዓይነት ጥያቄ ማቅረብ የሥነ ምግባር ህጉን እንደመጣስ አያስቆጥራችሁም ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ በ2002 ዓ.ም ምርጫው በተካሄደ በ3ኛው ቀን ኢህአዴግ በምርጫው ማሸነፉን በመግለፅ የምርጫ ሥነ ምግባሩን በግንባር ቀደምትነት ጥሶታል ብለዋል፡፡ የምርጫ ቦርድ ለጥያቄያቸው ተገቢ ምላሽ ካልሰጣቸው ሰላማዊና እርምጃ እንወስዳለን ይህ እርምጃም ሰላማዊ ሰልፍን ጨምሮ ህዝባዊ ንቅናቄ እስከመፍጠር የሚደርስ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡ የምርጫ ቦርድ የህዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ኃላፊ ወ/ሮ የሺ ፈቃድ፤ ፓርቲዎቹ ስላቀረቡት ጥያቄ የሚያውቁት ነገር አለመኖሩን ገልፀው፣ ጥያቄያቸው በቦርድ የሚፈታና አግባብነት ያለው ከሆነ በወቅቱ ምላሽ እንደሚሰጧቸው ተናግረዋል፡፡ ቦርዱ ለገዥው ፓርቲ የሚያዳላና ገለልተኛ አይደለም በማለት ፓርቲዎቹ ያቀረቡትን አቤቱታ አስመልክቶ ሲናገሩም የ2002 ምርጫ ሲጠናቀቅ ቦርዱ አዘጋጅቶት በነበረው የምርጫ ግምገማ መድረክን ጨምሮ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ በቦርዱ ቅሬታ እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የዚህ አይነት ቅሬታ የሚያ