Posts

በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ የሴታሞና አካባቢው መሠታዊ ሁለ ገብ የገበሬዎች አገልግሎት ህብረት..፡፡

በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ የሴታሞና አካባቢው መሠታዊ ሁለ ገብ የገበሬዎች አገልግሎት ህብረት ስራ ማህበር ግማሽ ሚሊዮን በሚበልጥ የገንዘብ ድጋፍ በሁለት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሁለት የመማሪያ ክፍሎችን እያስገነባ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ቢፋቶ ብሬ አንደገለፁት መንግስት የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋፋት እያደረገ ያለው ጥረት ስኬታማ እንዲሆን ማህበራትም የራሳቸውን ድርሻ ማበርከት ይኖባቸዋል፡፡ በዚህ መነሻ ማህበሩ ሴታሞና ሾእቾ በተባሉ ሁለት ቀበሌያት የሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለማስፋፋት በተያዘው እቅድ መሠረት ለእያንዳንዳቸው ደረጃቸውን የጠበቁ አንዳንድ ብሎክ እያስገነባ ይገኛል ብለዋል፡፡ ትምህርት ቤቶቹ በተጀመረው የትምህርት ዘመን አገልግሎት እንዲሰጡ ግንባታቸውን እየተፋጠነ መሆኑን የተናገሩት ሊመቀንበሩ ከ2ዐ ሺህ በላይ ብር ከማህበሩ ወጪ በማድረግ በ4 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ 1 ሺህ 354 ተማሪዎች የትምህር ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡ የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት እንደዘገበው፡: http://www.smm.gov.et/_Text/26TikTextN805.html

ዞኑ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ52 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

አዋሳ ጥቅምት 28/2005 ከተለያዩ የገቢ አርእስቶች ከ52 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የሲዳማ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን አስታወቀ። በመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተሰበሰበው ይኸው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ6 ሚሊዮን ብር ብልጫ ያለው ነው። ገቢዉ የተሰበሰበው ከቀጥተኛና ቀጥተኛ ካልሆኑ ታክሶች ፣ከማዘጋጃ ቤት ገቢና ከሌሎች የገቢ አርእስቶች መሆኑን የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ተሻለ ቡላዶ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ገልጠዋል ። ጽህፈት ቤቱ ከሩብ ዓመቱ ዕቅድና ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ብልጫ ያለው ገቢ ለመሰብሰብ የቻለዉ በዞኑ ለሚገኙ ግብር ከፋዮች የግንዛቤ ማጎልበቻ ስልጠናዎችን በመስጠት፣ የታክስ ስርዓቱን በዞኑ ወረዳዎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ በማድረግና ዘመናዊ የታክስና ቀረጥ መረጃ ስርዓት በመዘርጋት መሆኑን አስታዉቀዋል ። በዞኑ በሚገኙት የይርጋለምና አለታ ወንዶ ከተማ አስተዳደሮች ያሉ ግብር ከፋዮች የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ መጠቀም እንዲችሉ ለማድረግ የኔት ወርክ ዝርጋታ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝና ለግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ስለመሣሪያው ስልጠና በመስጠት በሁለት ወራት ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አቶ ተሻለ ገልጸዋል። ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ አዳዲስ ግብር ከፋዮችን ወደ ታክስ ስርዓቱ በማስገባትና ቀድሞ የነበሩ ግብር ከፋዮችን ደረጃ ገምግሞ በማሳደግ በተያዘው የበጀት ዓመት 344 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። በሩብ ዓመቱ 1ሺ600 አዲስ የደረጃ ሐመሩ ሐ ግብር ከፋዮች ወደ ስርዓቱ መግባታቸውንና 923 የደረጃ ሐመሩ ሐ ግብር ከፋዮች ወደ ደረጃ ለ ግብር ከፋይነት ማሳደግ መቻሉን አስታውቀዋል። http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=3224

በሀዋሳ ከተማ ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች እየተካሄዱ ነዉ

አዋሳ ጥቅምት 28/2005 በሀዋሳ ከተማ ለዘንድሮ በጀት አመት በተመደበ ከ700 ሚሊዮን ብር በጀት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች እየተካሄዱ መሆናቸውን የከተማው አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ገለጸ ።  ለፕሮጀክቶቹና ፕሮግራሞቹ ማስፈፀሚያ የሚዉለዉ ወጪ በአብዛኛው በከተማው አስተዳደር ገቢ የሚሸፈን መሆኑ ተመልክቷል ።  የመምሪያው ምክትል ሃላፊ አቶ አሻሬ ኡጋ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት እየተካሄዱ ካሉት የልማት ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞቹ መካከል አስፓልት መንገድ ግንባታን ጨምሮ የመጠጥ ውሃ፣ የተቀናጀ የቤቶች ልማት፣ የጤና፣ የትምህርት፣ የግብርናና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡  በተለይ በመንገድ ልማት ዘርፍ የ6 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር አዲስ አስፓልት ግንባታና የ4 ኪሎ ሜትር የነባር አስፓልት ጥገና፣ የ160 ኪሎ ሜትር አዲስ የጠጠር ምንገድ ስራና የ144 ኪሎ ሜትር የነባር መንገዶች ደረጃ የማሻሻል ተግባራት እንደሚከናወኑ አስረድተዋል፡፡ እንዲሁም የከተማው የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሻሻል ከ253 ሚልዮን ብር በላይ የስድስት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ ፣ የፓምፕ ተከላ ፣ የዉሀ ቧንቧ መስመር መዘርጋትና ሌሎች ተጓዳኝ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸዉን አቶ አሻሬ አስታዉቀዋል ። የመኖሪያ ቤት እጥረት ለማቃለል ቀደም ብለው የተጀመሩ የ1ሺህ 890 ቤቶች ግንባታ በማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ የማሰረከብ ስራ እንደሚካሄድም ተናግረዋል፡፡  የከተማው ጤና አገልገሎት ሽፋንም አሁን ካለበት 70 በመቶ ወደ 92 በመቶ ለማሳደግ የአንድ አዲስ ጤና ጣቢያና ሌሎች ቀደም ብለው የተጠናቀቁ ጤና ጣቢያዎችን በሰው ሃይልና በቁሳቁስ በማደራጀት ለአገልገሎት የማብቃት ስራ እንደሚከነወንም ገልጠዋል ። በከ

ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው ዓለም አቀፍ የቡና ጉባዔ ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ ነው

Image
አዲስ አበባ ጥቅምት 27/2005 ኢትዮጵያ በዚህ ሳምንትለመጀመሪያ ጊዜ ለምታካሂደው ዓለም አቀፍ የቡና ጉባዔ ዝግጅቱ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኮፊ ኤክስፖርተርስ አሶሴሽን የቦርድ አመራር አባላት አስታወቁ። የቢርዱ ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሮ እመቤት ታፈሰና የቦርድ አባሉ አቶ ታደሰ መስቀላ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚደረገው ጉባዔ ዝግጅቱ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።ጉባዔው አገሪቱ የቡና መገኛ ብቻ ሳትሆን፤የተለየ ጣዕምና ማንነት ያለው ቡና ባለቤት መሆኗንም ለማሳየት ያስችላል። በጉባዔው 250 የሚደርሱ ተሳታፊዎች ከውጭና ከአገር ውስጥ እንደሚሳተፉበትም አስረድተዋል። በጉባዔው የዓለም አቀፍ ቡና ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ሚስተር ሮቢዬሮ ኦሊቬራ ሲልቫ፣ታዋቂ የቡና ገበያ ድርጅቶች ኃላፊዎች፣በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት ልዑካን ቡድንና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ዕርዳታ ድርጅት ኃላፊዎች እንደሚገኙም ገልጸዋል። ማህበሩ ከንግድ ሚኒስቴርና ከሌሎች አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በሚያስተናግደው ጉባዔ የኢትዮጵያ ቡና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚገባ በማስተዋወቅ የተሻለ ገቢ የሚገኝበትን መንገድ ለመፍጠር ያስችላል የሚል እምነት እንዳላቸው አመልክተዋል። ጉባዔው ቡና አምራቾችን፣አቅራቢዎችን፣በምርትና በግብይት ሂደት ውስጥ የሚሳተፉ ሌሎች አካላትን በማሰባሰብ አገሪቱ ከምርቱ በይበልጥ ተጠቃሚ የምትሆንበትን ሁኔታ ለመፍጠር እንደሚያስችልም የቦርድ አመራር አባላቱ አስታውቀዋል። በተጨማሪም በቡና ምርትና አቅርቦት ዘርፎች የሚታዩ ችግሮችን የሚያቃልሉ ጥናታዊ ጽሁፎች እንደሚቀርቡበትም ተናግረዋል። ጉባዔው ከሌሎች አገሮች ጋር እየተደባለቀ የሚቀርበውን የአገሪቱን ቡና ችግሮች ለመፍታት እንደሚያስችል ኃላፊዎቹ እምነታቸውን ገልጸዋል። በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ

ኢትዮጵያችንን እየሰጠናት ወይስ እየነጠቅናት?!

Image
‹‹አገሬ ለእኔ ምን አደረገችልኝ ብለህ ከመጠየቅህ በፊት እኔ ለአገሬ ምን አደረግኩላት ብለህ ጠይቅ›› ብለው ነበር የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፡፡ እኛም ደግመን ደጋግመን እንለዋለን፡፡ ‹‹ላድርግላት›› የሚል እየጠፋ ‹‹ታድርግልኝ›› የሚል እየበዛ ነውና፡፡ ‹‹የሰጪ›› ቁጥር እያነሰ ‹‹የነጣቂ›› ቁጥር እየበዛ ነውና፡፡ እስቲ እንደ መንግሥትም፣ እንደ ሕዝብም፣ እንደ ግለሰብም፣ እንደ ዜጋም ራሳችንን እንፈትሽ፡፡ የድርሻችንን እየተወጣን ነን? እስቲ መንግሥትን ከመፈተሻችን በፊት እንደ ሕዝብና እንደ ዜጋ ራሳችንን እንፈትሽ፡፡ ኢትዮጵያችን ከጉቦ፣ ከሙስናና ከአድልዎ ፀድታ ሕገ መንግሥቱን መሠረት አድርጋ የምትንቀሳቀስ አገር እንድትሆን እንመኛለን፡፡ ነገር ግን ራሳችን እነዚህን እኩይ ተግባራት እንታገላለን? ጉቦ ሰጪ ከሌለ ጉቦ ተቀባይ እንደማይኖር አውቀን እምቢ አንሰጥም ብለን በፅናት እንቆማለን? ጉቦ የሚሰጡትንና ጉቦ የሚቀበሉትን እናጋልጣለን? ፈርተን ወይም እኛም ጉዳያችን እንዲፈጸምልን ብለን ተባባሪ እንሆናለን? እዚህ ላይ ከፍተኛ ጉድለትና ድክመት በዜጎችና በተለይም እንደ ሕዝብ እየታየብን ነው፡፡ ጠንክረን ሙስናን እየታገልን አይደለም፡፡ አገራችን ስትነጠቅ፣ ስትሰረቅና በሙስና ስትጨማለቅ የድርሻችን እየተጫወትን አንገኝም፡፡ ሌላው እንዲሠራው እንጂ እኛ ራሳችን ኃላፊነታችንን አንወጣም፡፡ አገራችን እንድትነጠቅ እየተባበርን ነን፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው ስለማንታገል፣ ለመብታችን ስለማንቆምና ግዴታችንን ስለማንፈጽም ነው፡፡ ወንጀል እንዲጠፋ እንፈልጋለን፡፡ መንግሥት ይህን ለምን አያደርግም፣ ፖሊሶች ለምን ዝም ይላሉ፣ ወንጀልኮ እየበዛ ነው፣ ሌብነት ተስፋፋ እንላለን፡፡ ሌላው ማድረግ ያለበትን አለማድረጉ ያስጠይቀዋል፡፡ ነገር ግን እኛ ራሳች