Posts

ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው ዓለም አቀፍ የቡና ጉባዔ ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ ነው

Image
አዲስ አበባ ጥቅምት 27/2005 ኢትዮጵያ በዚህ ሳምንትለመጀመሪያ ጊዜ ለምታካሂደው ዓለም አቀፍ የቡና ጉባዔ ዝግጅቱ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኮፊ ኤክስፖርተርስ አሶሴሽን የቦርድ አመራር አባላት አስታወቁ። የቢርዱ ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሮ እመቤት ታፈሰና የቦርድ አባሉ አቶ ታደሰ መስቀላ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚደረገው ጉባዔ ዝግጅቱ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።ጉባዔው አገሪቱ የቡና መገኛ ብቻ ሳትሆን፤የተለየ ጣዕምና ማንነት ያለው ቡና ባለቤት መሆኗንም ለማሳየት ያስችላል። በጉባዔው 250 የሚደርሱ ተሳታፊዎች ከውጭና ከአገር ውስጥ እንደሚሳተፉበትም አስረድተዋል። በጉባዔው የዓለም አቀፍ ቡና ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ሚስተር ሮቢዬሮ ኦሊቬራ ሲልቫ፣ታዋቂ የቡና ገበያ ድርጅቶች ኃላፊዎች፣በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት ልዑካን ቡድንና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ዕርዳታ ድርጅት ኃላፊዎች እንደሚገኙም ገልጸዋል። ማህበሩ ከንግድ ሚኒስቴርና ከሌሎች አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በሚያስተናግደው ጉባዔ የኢትዮጵያ ቡና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚገባ በማስተዋወቅ የተሻለ ገቢ የሚገኝበትን መንገድ ለመፍጠር ያስችላል የሚል እምነት እንዳላቸው አመልክተዋል። ጉባዔው ቡና አምራቾችን፣አቅራቢዎችን፣በምርትና በግብይት ሂደት ውስጥ የሚሳተፉ ሌሎች አካላትን በማሰባሰብ አገሪቱ ከምርቱ በይበልጥ ተጠቃሚ የምትሆንበትን ሁኔታ ለመፍጠር እንደሚያስችልም የቦርድ አመራር አባላቱ አስታውቀዋል። በተጨማሪም በቡና ምርትና አቅርቦት ዘርፎች የሚታዩ ችግሮችን የሚያቃልሉ ጥናታዊ ጽሁፎች እንደሚቀርቡበትም ተናግረዋል። ጉባዔው ከሌሎች አገሮች ጋር እየተደባለቀ የሚቀርበውን የአገሪቱን ቡና ችግሮች ለመፍታት እንደሚያስችል ኃላፊዎቹ እምነታቸውን ገልጸዋል። በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ

ኢትዮጵያችንን እየሰጠናት ወይስ እየነጠቅናት?!

Image
‹‹አገሬ ለእኔ ምን አደረገችልኝ ብለህ ከመጠየቅህ በፊት እኔ ለአገሬ ምን አደረግኩላት ብለህ ጠይቅ›› ብለው ነበር የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፡፡ እኛም ደግመን ደጋግመን እንለዋለን፡፡ ‹‹ላድርግላት›› የሚል እየጠፋ ‹‹ታድርግልኝ›› የሚል እየበዛ ነውና፡፡ ‹‹የሰጪ›› ቁጥር እያነሰ ‹‹የነጣቂ›› ቁጥር እየበዛ ነውና፡፡ እስቲ እንደ መንግሥትም፣ እንደ ሕዝብም፣ እንደ ግለሰብም፣ እንደ ዜጋም ራሳችንን እንፈትሽ፡፡ የድርሻችንን እየተወጣን ነን? እስቲ መንግሥትን ከመፈተሻችን በፊት እንደ ሕዝብና እንደ ዜጋ ራሳችንን እንፈትሽ፡፡ ኢትዮጵያችን ከጉቦ፣ ከሙስናና ከአድልዎ ፀድታ ሕገ መንግሥቱን መሠረት አድርጋ የምትንቀሳቀስ አገር እንድትሆን እንመኛለን፡፡ ነገር ግን ራሳችን እነዚህን እኩይ ተግባራት እንታገላለን? ጉቦ ሰጪ ከሌለ ጉቦ ተቀባይ እንደማይኖር አውቀን እምቢ አንሰጥም ብለን በፅናት እንቆማለን? ጉቦ የሚሰጡትንና ጉቦ የሚቀበሉትን እናጋልጣለን? ፈርተን ወይም እኛም ጉዳያችን እንዲፈጸምልን ብለን ተባባሪ እንሆናለን? እዚህ ላይ ከፍተኛ ጉድለትና ድክመት በዜጎችና በተለይም እንደ ሕዝብ እየታየብን ነው፡፡ ጠንክረን ሙስናን እየታገልን አይደለም፡፡ አገራችን ስትነጠቅ፣ ስትሰረቅና በሙስና ስትጨማለቅ የድርሻችን እየተጫወትን አንገኝም፡፡ ሌላው እንዲሠራው እንጂ እኛ ራሳችን ኃላፊነታችንን አንወጣም፡፡ አገራችን እንድትነጠቅ እየተባበርን ነን፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው ስለማንታገል፣ ለመብታችን ስለማንቆምና ግዴታችንን ስለማንፈጽም ነው፡፡ ወንጀል እንዲጠፋ እንፈልጋለን፡፡ መንግሥት ይህን ለምን አያደርግም፣ ፖሊሶች ለምን ዝም ይላሉ፣ ወንጀልኮ እየበዛ ነው፣ ሌብነት ተስፋፋ እንላለን፡፡ ሌላው ማድረግ ያለበትን አለማድረጉ ያስጠይቀዋል፡፡ ነገር ግን እኛ ራሳች

በደቡብ የክልል የም/ቤትና የቀበሌ ምርጫዎችን ጨምሮ በአዲስአበባ የከተማ አስተዳደር፣የዞንና የወረዳ ም/ቤቶች ምርጫ በሚያዚያ ወር 2005 ለማካሄድ ቦርዱ አቅዶአል፡፡

ተቃዋሚዎች በዘንድሮ ምርጫ መዳከም አሳይተዋል ኢሳት ዜና:-ዘንድሮ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የአካባቢና የአዲስአበባ ከተማ ምርጫ ተቃዋሚዎች እስካሁን ምንም ዓይነትጥቅምት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ዝግጅት አለማድረጋቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡ ምርጫ ቦርድ በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ምርጫው የሚያካሄድበትን የጊዜ ሰሌዳ ባለፈው ሳምንት ይፋ ያደረገ ሲሆን በዚህ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተወዳዳሪ ፓርቲዎች በምርጫው ዕጩዎቻቸውን ለማስመዝገብ የቀራቸው ጊዜ ሶስት ወራት ብቻ ነው፡፡ ይህም ሆኖ እስካሁን አንድም ፓርቲ በምርጫው እንደሚሳተፍ የገለጸበት ሁኔታ ካለመኖሩም በላይ ምርጫ ስለመኖሩም እየተነገረ አለመሆኑ ታውቋል፡፡ኢህአዴግ ሆን ብሎ ስለምርጫው ብዙም ሳይወራ በግርግር አሸናፊ ተብሎ እንዲያልፍ እንደሚፈልግ ምንጫችን አስታውሶ ተቃዋሚዎች ግን በአዲስአበባ እንኳን ጥቂትም ቢሆን ወንበር ለማግኘት ከወዲሁ መስራት አለመቻላቸው በጣም መዳከማቸውን እንደሚያሳይ ገልጾአል፡፡ትልቁን ተቃዋሚ ፓርቲ መድረክን ጨምሮ እንደ መኢአድ ያሉ ፓርቲዎች በምርጫው ለመሳተፍ እስካሁን አለመወሰናቸው ታውቋል፡፡ ይህ አጋጣሚ ደግሞ ለገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ አመቺ ሁኔታን ከመፍጠር ያለፈ ፋይዳ እንደሌለው የዜና ምንጫችን ጠቁሟል፡፡ አብዛኛዎቹ ፓርቲዎች ከምርጫው በፊት በአገሪቱ ካሉ የፖለቲካ ችግሮች ጋር በተያያዘ ለመወያየት ፍላጎት እንዳላቸው ከሳምንት በፊት በአዳማ ምርጫ ቦርድ በጠራው ስብሰባ ላይ ያሳወቁ ቢሆንም በምርጫ ቦርድ በኩል ያለው ዝምታ ግን ጊዜ መግደያ መሆኑን አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እየተናገሩ ነው፡፡ ፓርቲዎቹ ለመወያየት ያቀረቡት ጥያቄ እንደተጠበቀ ሆኖ ለምርጫው እየተዘጋጁ ቢጠባበቁ የተሻለ ዕድል እንደሚኖራቸው ምንጫችን መክሮአል፡፡ይህ

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ

Image
የክልሎችን የ2004 እቅድ አፈጻጻም ማጠቃለያና የ2005 እቅድ ዝግጅትና ፈጻሚ ማዘጋጀት ስራዎችን በመፈተሽ ስብሰባውን የጀመረው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ባለፈው አመት የገጠር ልማትን በተመለከተ በተፋሰስ፣ በመስኖና በሰብል ልማት ስራዎች አፈጻጻም የነበረው አንጻራዊ ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ በሁሉም ክልሎች የተሻለ እንቅስቃሴና ውጤት መታየቱን አረጋግጧል፡፡ ይኸው አበረታች እንቅስቃሴ በ2005 የአርሶ አደሩን ምርታማነትና አጠቃላይ ሀገራዊ ምርትን ለማሳደግ የሚደረገው ርብርብ አዎንታዊ ድርሻ እንዳለው ገምግሟል፡፡ በማህበራዊ ልማት ዘርፍም በተለይም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ሰፊ እንቅስቃሴ መደረጉንና በወላጅ፣ በመምህራንና በተማሪዎች የተደራጀ ጥረት አመርቂ ውጤት መታየቱን አረጋግጧል፡፡ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙን በሰፊ የህዝብ ተሳትፎ በማስፋፋትና የእናቶችና ህጻናትን ሞት ለመቀነስና በአጠቃላይ ጤንነቱ የተጠበቀ ህብረተሰብ በመገንባት የጀመርነውን ፈጣን እድገትና የሀገሪቱን ህዳሴ ለማስቀጠል በተለይ የሴቶች አደረጃጀቶች ላይ ተመሰርቶ የተደረገው ጥረት ከፍተኛ ውጤት በማሳየቱ በሁሉም ክልሎች የተገኙትን ልምዶች በመቀመር አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥቶ መክሮበታል፡፡ ከመልካም አስተዳደር ጋር በተያያዘ በገጠሩ የተሻለ ሁኔታ መኖሩን የገመገመው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የተገኘውን ለውጥ መሰረት በማድረግና የተጀመረውን የህዝቡን ልማታዊ እንቅስቃሴ በማጠናከር በህዝቡ በራሱ ተሳትፎ አልፎ አልፎ የሚገጥሙ ችግሮችን ማስወገድ የሚችልበት ሁኔታ መፈጠሩን በመገምገም ከስምምነት ላይ ደርሷል፡፡ የከተማ ሰራዎችን በተመለከተ በዋነኝነት የከተማውን ነዋሪ የገቢ አቅም ለማሳደግ የተካሄደው የስራ እድል ፈጠራና የጥቃቅንና አነስተኛ ተ

ከሲዳማ ዞን በህገ ወጥ መንገድ የእሸት ቡና ወደ ሌሎች አካባቢ ሲያዘዋውሩ የተገኙ የሦስት የጭነት መኪናዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

የጭነት መኪናዎቹ የተያዙት የዞኑ ፖሊሲ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ በዘርፉ ከተቋቋመው ግብረ ኃይል በመተባበር ነው፡፡ የጭነት መኪናዎቹ ሦስት አይሱዚዎች ሲሆኑ ኮድ ሦስት ታርጋ ቁጥር 67218፣ 68896፣ እና 48 3ዐ7 አዲስ አበባ የሚሉ ናቸው፡፡ የሲዳማ ዞን ፖለሲ መምሪያ ህገ ወጥ የቡና ግብይትን ለመቆጣጠር በዞኑ ከተቋቋመው ግብረ ኃይል ጋር በመተባበር ባለፈው አርብ ከሌሊቱ 9 ሰዓት በተደረገው ክትትል ተሽከርካሪዎቹ በቁጥጥር ሲውሉ አሽከርካሪዎቹ አምልጠዋል፡፡ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ዴቢሶ አንደገፁት ቡና ጥራቱን ጠብቆ ለማዕከላዊ ገበያ ቀርቦ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት የሚጫወቱት ሚና በተገቢው መልኩ እንዲወጣ ማድረግ ከተፈለገ ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች ሊቆሙ ይገባል፡፡ የአገሪቱን ኢኮኖሚ የሚጐዱ የንግድ እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉ የንግዱ ማህበረሰብ ከድርጊታቸው ከወዲሁ ሊቆጠቡ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡ ድርጊቱን የማጋለጥ ሥራ በዞኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኢንስፔክተር ተስፋዬ አልክተዋል፡፡ የሲዳማ ዞን ቡና አቅርራቢዎች ማህበር ምክትል ሊቀመንብር አቶ ቶንጐላ ቶርባ በሰጡት አስተያየት ቡና የአገሪቱ ኢኮኖሚ ዋልታ በሆኑ በዘርፉ የተሰማሩ በተቀመጠው ደንብና መምሪያ መሠረት መንቀሳቀስ ሲገባ ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ የሚያደርገትን አጥብቀው እንደሚቃወሙ ተናግረዋል፡፡ ህገና ህጋዊነት ለማክበር መዘጀታቸውን በማረጋገጥ የዞኑ ግብይትና ህብረት ስራ መምሪያ ኃላፊ አቶ ቡርቃ ቡላሾ በበኩላቸው ማንኛውም የቡና ግብይት በተፈጠረላቸው የግብይት ማዕከላት ብቻ እንዲካሄድ የወጣውን ደንብ ወደ ጐን በመተው የተፈፀመ ድርጊት በቡና ጥራት ላይ አሉታዊ ተፅኖ የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡ በዞኑ እንዲሁ ዓይነት ድርጊት እንዳይፈጠር ለማድረግ በበጀት ዓመቱ