Posts

የመጀመሪያው ''ሲዳማ በዚህ ሳምንት'' የኢንተርኔት ላይ የሬዲዮ ፕሮግራም ኣየር ላይ ውሏል

Image
የሬዲዮ ፕሮግራሙ በዚህ ሳምንት ዝግጅቱ በተለያዩ የኣለማችን ክፍሎች የሚገኙትን የሲዳማ ዳይስፖራ የሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎችን ኣሳትፏል። እንደኣዘጋጆቹ ከሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ እና ሲዳማ የሚገኙ  የሬድዮ ፕሮግራሙን የምከተታዮች በዝግጅቱ ላይ ኣስተያየት እንዲስጡ እና በፕሮግራሙ ላይ በመሳተፊ ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ ጥሪ ኣቅርበዋል። የ''ሲዳማ በዚህ ሳምንት የሬድዮ ፕሮግራም'' ኣዘጋጅን በምከተለው ኣድራሻ ማግኘት ይቻላል ፦ e-mail: nomonanoto@gmail.com   ሲዳማ ሻው ለማድመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ

«ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የምርጫና ዴሞክራሲ አማካሪ ተቋም ጋር ተባብሮ ለመሥራት ዝግጁ ናት» ጠ/ሚ ኃይለማርያም

Image
ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የምርጫና ዴሞክራሲ አማካሪ ተቋም ጋር ተብብሮ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አረጋገጡ። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የአማካሪ ተቋሙን ዋና ጸሐፊ ቪዳር ሄልግሰን ጥቅምት 22/2005 በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው ሲያነጋግሩ እንደገለፁት ኢትዮጵያ ከተቋሙ ጋር ተባብራ ለመሥራት ፍላጎቷ ነው። ተቋሙ በኢትዮጵያ በ2002 የተካሄደውን ብሔራዊና ክልላዊ ምርጫ በምርምር ያቀረበው የሥነ ምግባር መመሪያ በሁሉም ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት ያተረፈ እንደነበር አስታውሰዋል። መንግሥት ቀደም ሲል የተፈጠረውን ግንኙነት መሠረት በማድረግ ከተቋሙ ጋር በቀጣዩም ተባብሮ ለመሥራት ፍላጎት እንዳለውም አስታውቀዋል፡፡ ተቋሙ በምርጫና በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ላይ አዳዲስ ሐሳቦችን በማመንጨት እንዲያቀርብም መጠየቃቸውን አንድ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን ለጋዜጠኞች ገልፀዋል። ሚስተር ሄልገሰን በበኩላቸው በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት ጥልቅ ኀዘን እንደተሰማቸው አስታውቀው፣ በእሳቸው አመራር ዘመን በኢትዮጵያ የተጀመሩ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ወደፊትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡ በተለይ በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት እስካሁን የተመዘገቡ ስኬቶች በአዲሱ አመራር ለማስቀጠል በስፋት ተነጋግረዋል፡፡ ዋና ፀሐፊው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽንና በአፍሪካ ኅብረት ትብብር አዲስ አበባ ውስጥ ''ወጣቶችና የአፍሪካ ዴሞክራሲ'' በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ዐውደ ጥናት እየተሳተፉ ናቸው። http://www.ertagov.com/amerta/erta-news-archive/49-erta-tv-hot-news-ad

ጠ/ሚኒስትሩ ከ “ልማታዊ ተቃዋሚዎች” ጋር ቢወያዩስ?

Written by  - ኤልያስ - ጋዜጠኞች ለኢትዮጵያ ህዳሴ አያስፈልጉም እንዴ? አባት ተርብ የሆኑ ነጋዴ ናቸው፡፡ ሴት ልጃቸው ደግሞ ሰቃይ ተማሪ ናት - በአሜሪካ ዩኒቨርስቲ፡፡ በነገራችን ላይ ሁለቱም አሜሪካውያን ሲሆኑ የሚኖሩትም እዚያው አሜሪካ ነው፡፡ አባት ባለሃብቶች ላይ ከፍተኛ ግብር የሚጥለውን የዲሞክራት ፓርቲ አይደግፉም፡፡ የሪፐብሊካኖች ቀንደኛ ደጋፊ ናቸው፡፡ ልጅት ደግሞ ዲሞክራት ናት፡፡ የኮሌጅ ፕሮፌሰሯም እንዲሁ፡፡ እናም ሁሌ ይወያያሉ - የአሜሪካን ሃብት ጠቅልለው ስለያዙት 1በመቶ ባለሃብት አሜሪካውያንና 99 በመቶ ምስኪኖች፡፡ “እነዚህ ስግብግቦች እኮ ናቸው …” እያሉ ያማሉ፤ ይተቻሉ፡፡ (ኢህአዴግ ኪራይ ሰብሳቢ ባለሃብት እንደሚለው) አንድ ቀን ልጅትና አባት ቁጭ ብለው ሲያወጉ የተለመደው አከራካሪው ጉዳይ ተነሳ፡፡ “መንግስት የጣለብህን ግብር እየከፈልክ እኮ አይደለም …ህዝብ እየበዘበዝክ ነው… በጣም ኢ-ሰብዓዊ ተግባር ነው” ስትል ልጅ አባቷን ትወቅሳለች፡፡ አባት ከመናደድ ይልቅ መላ አመጡ፡፡ “ግን ትምህርት እንዴት ነው የእኔ ልጅ? ውጤትስ?” ይሏታል “እኔስ ቀንቶኛል … 4A እና 3B አግኝቻለሁ … ጓደኛዬ ግን ጠቅላላ C ነው ያመጣችው” “ታዲያ ካንቺ 4Aዎች አታካፍያትም?” ጠየቁ አባት (ለብልሃታቸው) “እንዴ … ለፍቼ እኮ ነው ያገኘሁት” አባት ፈገግ ብለው “እኔም ለፍቼ ያመጣሁትን እኮ ነው ስጥ የምትይኝ… ገባሽ?” አሏት፡፡ (የገባት ግን አይመስለኝም) እኔ የምለው የአሜሪካን ምርጫ እየተከታተላችሁ ነው? እኔማ ቀናሁባቸው! በነገራችሁ ላይ ኢቴቪ የኦባማ (ዲሞክራቶች) ደጋፊ ነው እንዴ? (ጥያቄ ነው!) የሰሞኑን የአሜሪካ ምርጫ ዘገባዎች በኢቴቪ ካስተዋላችሁ እኮ የአሜሪካ ዲሞክራት ፓርቲ ደጋፊ ነው የሚመስላችሁ፡፡ ኢቴቪ ዲሞክራቶችን

ዓለም አቀፍ የቡና ጉባዔ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፡- የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ቡና ጉባዔ በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት እንደሚካሄድ ኢትዮጵያን ኮፊ ኤክስፖርተስ አሶሴሽን አስታወቀ። አሶሴሽኑ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ «የቡናችን መገኛ ታሪካችንን ማጠናከር» በሚል መሪ ሃሳብ ጥቅምት 29 እና 30 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል በሚካሄደው በዚህ ጉባዔ ከ250 በላይ ተሣታፊዎች ይገኛሉ። ከንግድ ሚኒስቴርና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የሚካሄደው የዚህ ጉባዔ ዓላማ የኢትዮጵያ ቡና በዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ የሚኖረውን ድርሻ ማሳደግ በሚያስችሉ ስልቶች ላይ ለመወያየትና መረጃና ልምድ ለመለዋወጥ ነው። ባለድርሻ አካላት በቡና ዓለም አቀፍ ግብይት ላይ ስላሉት ዕድሎችና ተግዳሮት በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ እና የኢትዮጵያን ቡና ልዩ ጣዕም በማስተዋወቅ ረገድ መጫወቱ ስለሚገባቸው ሚና እንዲያውቁ ለማድረግ ታስቦ መዘጋጀቱንም መግለጫው አመልክ ቷል። በጉባዔ በቡና ንግድ ዘርፍ ላይ ዋነኛ ተዋንያን የሆኑትን ላኪዎች፣ አቅራቢዎች፣ ወኪሎች፣ ማኅበራት፣ የክልል ግብርና ቢሮዎች፣ የንግድ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ፣ የግብርና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን፣ የአካባቢ የፋይና ንስ ተቋማት፣ ዓለም አቀፍ ቡና ገዥ ኩባንያዎች ይሣተፋሉ። የዓለም አቀፉ የቡና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ሮቤይሮ ኦሊቬይራ ሲልቫ፣ የአውሮፓ ሕብረት ልዑክ መሪ እና በኢትዮጵያ የዩኤስ ኤይድ ዳይሬክተር በጉባዔው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። «ወደ ውጭ የሚላከው ቡና በ25 በመቶ የሚጨምር፣ መጠኑም ከ200ሺ ቶን በላይ፣ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ አንድ ቢሊዮን ዶላር እንደሚልቅ ይጠበቃል» ሲል መግለጫው አመልክቷል። 

The sidama Students in Universities: Any positive Role played in contemporary Political Realities?

Image
Kinkino Kiya By : Kinkino Kia, Hawassa University ( Oct, 2012)  As many scholars contend, a very little is known about sidama people due to the consistent lack of such a status as a nations in the Ethiopian historiography. As Seyoum rightly argues, the general lack of useful sources on sidama studies has been a bone of contention among the contemporary sidama intellectuals for quite some time. The paucity of information has resulted in confusion and ambiguity in identifying the people, its culture, the history and the current development underlying the change and continuity in Sidama land. Sidama people conceive the modern government administrative structure from their historical experience of conquest and subsequent alienation in the past. Therefore, a brief review of the place of Sidama within the modern Ethiopian state is appropriate. Ever since the conquest of Menlik II, in early 1890s, the sidamaland and its people have been subjected to relentless oppression and exploitation.