Posts

The sidama Students in Universities: Any positive Role played in contemporary Political Realities?

Image
Kinkino Kiya By : Kinkino Kia, Hawassa University ( Oct, 2012)  As many scholars contend, a very little is known about sidama people due to the consistent lack of such a status as a nations in the Ethiopian historiography. As Seyoum rightly argues, the general lack of useful sources on sidama studies has been a bone of contention among the contemporary sidama intellectuals for quite some time. The paucity of information has resulted in confusion and ambiguity in identifying the people, its culture, the history and the current development underlying the change and continuity in Sidama land. Sidama people conceive the modern government administrative structure from their historical experience of conquest and subsequent alienation in the past. Therefore, a brief review of the place of Sidama within the modern Ethiopian state is appropriate. Ever since the conquest of Menlik II, in early 1890s, the sidamaland and its people have been subjected to relentless oppression and exploitation.

ቦርዱ የአካባቢና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች ምርጫ የጊዜ ሰሌዳን ይፋ አደረገ

Image
አዲስአበባ፣ጥቅምት 21፣2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ በመጪው ሚያዚያ ለሚካሄደው የአካባቢና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ። በቀጣይም የምርጫውን ሂደት በተመለከተ ፥ ከፓርቲዎች ጋር ተከታታይ ምክክሮች እንደሚያደርግም አስታውቋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ይፋ ያደረገው 22 ክንውኖችን ያካተተ የአካባቢና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ አፈጻጸም የጊዜ ሰሌዳ ነው። የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እንዳሉት ፥ ቦርዱ የጊዜ ሰሌዳውን ያጸደቀው  ከ75 የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በረቂቅ ሰነዱ ላይ ሰፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ ነው። በውይይቱም ፓርቲዎቹ የጊዜ ሰሌዳው የሚያሰራ መሆኑን መግለጻቸውን ያስታወሱት ሰብሳቢው  ፥ የተሰጡ አስተያየቶችን ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ የግዜ ሰሌዳው መጽደቁን ነው የተናገሩት። በግዜ ሰሌዳው በተቀመጡ ት  ክንውኖች መሰረት ወደ ትግበራ እንደሚገባ  የገለጹት ደግሞ የቦርዱ ጽህፈት ቤት ዋና ሃላፊ አቶ ነጋ ዱሪሳ ናቸው። በዚህም መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች የመወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ህዳር 14  2005 ቀርበው የሚወስዱ ሲሆን ፥ የየምርጫ ክልሉ ጽህፈት ቤቶች ደግሞ ህዳር 24  ቀን 2005  ተከፍተው ስራቸውን የሚጀምሩ ይሆናል። የመራጩ ዝብ ፣ የየፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎች ፣ እንዲሁም የግል እጩ ተወዳዳሪዎች  ምዝገባ ከታህሳስ 22 እስከ ጥር 21 2005  ይሆናል። የከተማ ፣ የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤት ምርጫ የድምጽ ቆጠራ በየምርጫ ጣቢያው የሚከናወንበት እለት ሚያዚያ 6 ከምሽቱ 12 ሰኣት ጀምሮ ሲሆን ፥ ሚያዚያ 7 ደግሞ በየምርጫ ጣቢያው ውጤት ለህዝብ ይፋ ይሆናል። በመጨረሻም የአካባቢ

በደቡብ ክልል በከተሞች ለነዋሪዎች ስኳር ስንዴና የምግብ ዘይት ተከፋፈለ

አዋሳ ጥቅምት 22/2005 በደቡብ ክልል ከተሞች ገበያን ለማረጋጋት ባለፉት ሶስት ወራት 27ሺህ 475 ኩንታል ስኳርና ስንዴ እንዲሁም ከ613ሺህ ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለተጠቃሚው መከፋፈሉን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ ገለፀ፡፡ የቢሮው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ባለቤት አቶ መላኩ እንዳለ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የፍጆታ ሸቀጦቹ የተከፋፈሉት ሀዋሳን ጨምሮ በክልሉ ከተሞች በሚገኙ 133 የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት ነው፡፡ ከተከፋፈለው መካከል 19ሺህ 345 ኩንታል ስኳር፣ 8ሺህ 130 ኩንታል ስንዴና ከ613ሺህ ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለአባላትና ለአካባቢው ህብረተሰብ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ባለፉው የበጀት ዓመትም በ123 የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት ከ2 ነጥብ 5 ሚልዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት፣ ከ533ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር ፣ የምግብ እህልና የተለያዩ ሸቀጦች በተመሳሳይ ለተጠቃሚዎች መከፋፈሉን ገልጸዋል፡፡

የትናንቱ ጐዳና ተዳዳሪ የዛሬው ብሔራዊ ቡድን ፈርጥ

Image
በደረጀ ጠገናው ብራዚል ለዛሬው የእግር ኳስ ስፖርቷ፣ ክብሯንና ማንነቷን የገነባችው ትናንት ከየጐዳናውና ጉራንጉሩ ትመለምላቸው በነበሩ የኳስ ፈርጦቿ አማካይነት መሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ነው፡፡ ከእነዚህ የምንግዜም ዝነኛ የኳስ ክዋክብት መካከል ጋሪንቻና ሌሎችም በርካታ ቁጥር ያላቸው ብራዚላውያን ታዳጊዎች ይጠቀሳሉ፡፡ ገና በለጋ ዕድሜያቸው የሕይወት ውጣ ወረድ ገፈት ሊጋፈጡ የተገደዱት ጋሪንቻና ሌሎቹም የቱንም ያህል እግር ኳስን ቢወዱም፣ የቱንም ያህል ችሎታና ክህሎቱ ቢኖራቸውም በተለይ ጋሪንቻ ‹‹እግረ ደጋን›› እየተባለ ፈላጊ አልነበረውም፡፡ እግሩ ያነክሳልና ለእግር ኳስ አይመጥንም እየተባለ ብዙ ተንከራቷል፡፡ የኋላ ኋላ ግን የኳስ አምላክ ትክከለኛውን የኳስ ግጣም አገናኘና ጋሪንቻ በብራዚል ሜዳዎች ብቻ ሳይሆን በዓለም ዋንጫ መድረኮች ሁሉ ገነነባቸው፡፡ እንደ ጋሪንቻ ሁሉ ሌሎችም ከብራዚል ጐዳናዎች የተገኙ የእግር ኳስ ጠበብት ሮናልዶ ናዛሪዮ ሊዊስ ዴሌማ፣ ሮናልዲኒሆ ጐቹን ጨምሮ ለዓይን የሚታክት በርካታ ፈርጦች ልጥቀስ ይቻላል፡፡ ለመነሻ ያህል ስለብራዚላውያን የጐዳና ፈርጦች አወሳን እንጂ ልናወራ ያሰብነው፣ የኢትዮጵያ ጐዳናዎችም የጨርቅ ኳስን ከእግራቸው አፋቅረው የመንገደኞችን ቀልብ እየገዙ ኳስን የሚያንከባልሉ ጥቂት አይደሉምና የምንለውን ለማለት ነው፡፡ በርካቶች ግን ፈላጊ እያጡ ችሎታቸውን አይቶ ተገቢ ቦታ የሚሰጣቸው ባለማግኘታቸው እየደበዘዙ ሲጠፉ ቆይተዋል፡፡ በዚህ ዘመን ግን አንድ ያልተጠበቀ ጮራ በድንገት ፈንጥቋል፡፡ አስገዳጁና እንዲያም ሲል በጐዳና የጨርቅ ኳሶች ላይ ሲሾሩ የቆዩት የታዳጊ ወጣት እግሮች ቦታቸውን እንዲያገኙ ግድ ብሏል፡፡ በአሁኑ ጊዜም የአገርን ባንዲራ አስከብረው የባላንጣ ውጋት እየሆነ እግሮቹ ምትሀት እያሳዩ ይገኛሉ፡

የስኳር ምርትን ወደ ውጭ ለመላክ ከፍተኛ ጥረት እንደሚደረግ ተገለጸ

Image
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 21 ፣2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የስኳር ምርትን ባለፈው ዓመት ወደ ውጭ መላክ ይጀመራል ተብሎ የነበረ ቢሆንም የስኳር ፕሮጀክቶቹ በታሰበላቸው ፍጥነት እየሄዱ እንዳልሆነ ተገለጸ።  የስኳር ኮርፖሬሽን እንደሚለው ለፕሮጀክቶቹ መጓተት ዋነኛው ምክንያት የአቅም ውስንነት ነው።  ቀደምሲልየማስፋፊያስራእየተሳራባቸውየነበሩየስኳርፋብሪካዎችንና ነባርየስኳርፋብሪካዎችንበመጠቀምካለፈውዓመትጀምሮየስኳርምርትለውጭገበያለማቅረብታቅዶየነበረሲሆን፥እንደታቀደውግንማድረግአተቻለም። የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ልዩ አማካሪ አቶ አስፋው ዲንጋሞ እንዳሉት ፥ የኮንትራክተሮችም ሆነ የአማካሪዎች አቅም ውስንነት ፣ የገንዘብ እጥረት ፣ በበቂ የሰው ኃይል አለመደራጀት ፣ ለፕሮጀክቶቹ መጓተት በምክንያትነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው። ከፕሮጀክቶቹ ግዝፈትና ውስብስብነት ጋር በተያያዘም ፥ የስኳር ኮርፖሬሽንም ቢሆን የፕሮጀክት አመራርና አስተዳደር ድክመት እንደነበረበትና፥ በአሁን ወቅት ግን ችግሮቹ በመለየታቸው በያዝነው ዓመት ፕሮጀክቶቹን በአዲስ መልክ ለማፋጠንና ለማጠናቀቅ ርብርብ በመደረግ ላይ መሆኑንም ነው ያስረዱት። ኮርፖሬሽኑ ፕሮጀክቶቹን በአዲስ መልክ ለመምራት እንዲያስችለውም ፥ ባለፉት ሶስስት ወራት ቁልፍ ችግሬ ነበር ላለው የአቅም ውስንነት ትኩረት ሰጥቶ ሰርቷል ፥ እየሰራም ነው። የሰው ኃይሉን አቅም ለማጎልበትም በውጭ ሃገራት ጭምር በመላክ የተለያዩ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ እያደረገ ነው። የከሰም ስኳር ፋብሪካ በጣም ከዘገዩት ውስጥ አንዱ ሲሆን ፥ የፋብሪካ ግንባታውንም በዚህ ዓመት በአብዛኛው በማጠናቀቅ በቀጣዩ ዓመት ወደ ማምረት ስራ እንዲገባ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል ፥ የወልቃይት፣የበለስና ስድስት ፋብሪካዎች የሚገነቡበት የደ