Posts

Beyond the Politics: - A look at a Reality of Sidama Economy

Image
By Kinkino Kiya, October 25, 2012 According to the most recent World Bank’s report that analysis the World poverty index; Ethiopia by all measures remains one of the poorest countries of the world. The most critical challenge facing the Sidama authorities and the Ethiopian policy makers at large -today and for the years ahead is the urgent task of reducing absolute poverty from the Sidama region as well as for the federal authorities addressing the issues at a national level. The basic objective of economic resources management and the fundamental goal of government anywhere, at all times must be working towards improving the standard of living of their respective people’s over time in the given periods of time. [...] The numerous Ethiopians including the Sidama nation were so optimistic trusting that the current might declare war on the greatest enemy of our people, the abject poverty that has incarcerated the nation of the country with varying degrees. Regardless of the a

ድህነትን ታሪክ ለማድረግ የተቀናጀ ዘመቻ

Image
ተስፋዬ ለማ ከዛሬ አራት ቀን በፊት ማለትም ጥቅምት 2/2005 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አጀንዳ አምድ በዚሁ ርዕስ ከታላላቅ የሀገራችን ልማት ሥራዎች የስኳር ልማት ፕሮጀክት እንቅስቃሴ ላይ ያተኮረ ጽሑፍ ማቅረባችን ይታወሳል። በጽሑፉ በአገራችን በመስፋፋትና በመገንባት ላይ ያሉ ነባርና አዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያ የምትመራ በትን የግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለማሸጋገር የሚያስችል መሠረት ለመጣል ከተያዙ ታላላቅ ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ልማቶች በዋናነት የሚጠቀሱ መሆኑን ዳስሰናል።  በአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መሠረት ነባሮቹን የማስፋፋትና አዳዲሶች የመገንባት አቅጣጫ ተይዞ እየተሠራ መሆኑን ለማየትም ተሞክሯል። ከእዚሁ ጋር ተያይዞ የአገሪቱ የስኳር ፍላጎት ከሚመረተው ምርት ጋር ባለመጣጣሙ መንግሥት ከተለያዩ አገራት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ስኳር እያስገባ መሆኑን ጠቁመን ከሦስት ዓመታት በኋላ ግን አገሪቱ የሕዝቧን የስኳር ፍላጎት አሟልታ የተረፈውን ለውጭ ገበያ በማቅረብ የተሻለ የውጭ ምንዛሪ የምታስገባበት ሁኔታ እንደሚፈጠር አይተናል።  ከስኳር ልማት ፕሮጀክቶቹ ጋር ተያይዞ በተለያዩ ወገኖች የሚነሱ መሠረት የለሽ አሉታዊ ዘገባዎች የአገራችንን የልማት አቅጣጫ ለማስቀየስ እንጂ መሠረታዊ ጠቀሜታ ኖሯቸው እንዳልሆነና በአሁኑ ወቅት ልማታችንን ለማደናቀፍ የሚሰነዘሩ አሉባልታዎችን የሚሰማ ጆሮ ያለው ኢትዮጵያዊ አለመኖሩንም ለማስገንዘብ ተሞክሯል። የኢትዮ ጵያ ሕዝብ ዋነኛ ጠላት ድህነት መሆኑን መግባ ባት ላይ መደረሱንም ነው በመጀመሪያው ጽሑፍ የቃኘነው።  በዛሬው ጽሑፍ በሀገራችን እየተገነቡ ካሉ አዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክትን እንመለከታለን።  የወልቃይ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የቡና ጉባኤ ሊካሄድ ነው ለውጭ ገበያ ከሚቀርበው ቡና 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሪ ገቢ እንደሚገኝ ይጠበቃል

Image
አዲስ አበባ ጥቅምት 16/2005 በቡና ንግድ ዘርፍ መላው ባለድርሻ አካላትን የሚያሳትፍ የመጀመሪያው ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ በቅርቡ አዲስ አበባ ውስጥ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ኮፊ ኤክስፖትርስ አሶሴሽን አስታወቀ፡፡ ኢትዮጵያ ዘንድሮ ለዓለም አቀፉ ገበያ ከምታቀርበው የቡና ምርት 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሪ ገቢ እንደምታገኝ ይጠበቃል፡፡ የአሶስዬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰር አቶ ጌታቸው አድማሱ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጸው ጉባኤው የቡና ምርቶች መገኛ የሆነችውን ኢትዮጵያን ገጽታን ከመገንባት ባሻገር የተለያዩ ምርቶቿን ለዓለም አቀፉ ገበያ ለማስተዋወቅ የሚረዳ ነው፡፡ አሶስዬሽኑ ጉባኤውን በሚቀጥለው ሳምንት በአዲስ አበባ ሒልተን ለማካሄድ ከንግድ ሚኒስቴርና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑንና በአሁኑ ወቅትም አስፈላጊውን ቅድም ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ለሁለት ተከታታይ ቀና በሚካሄደው ዓለም ዓቀፍ የቡና ጉባኤም 250 ሰዎች እንደሚሳተፉ ገልጸዋል፡፡ እንደ አቶ ጌታቸው ገለጻ ከአገር ውስጥ በቡና ንግድ የተሰማሩ ላኪዎችና አቅራቢዎች ድርጅቶች፣ የሕብረት ስራ ማህበራት ዩኒየኖችና የክልል ግብርና ቢሮ ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት ተጠሪዎችና የገንዘብ ተቋማት ይሳተፋሉ፡፡ በተጨማሪም ከውጭ ዓለም ዓቀፍ የቡና ገዢዎች፣ ቆይና ቸርቻሪዎች የጉባኤው እድምተኞች ይሆናሉ፡፡ በጉባኤውም በተለይ በቀጣዩ አውሮፓውያን ዓመት የኢትዮጵያ ቡና ምርት የውጭ ገበያ አቅርቦት በሚያድግበት እንዲሁም አገሪቱ ከዘርፉ የምታገኝው የውጭ ምንዛሪ ገቢም በዚያው ልክ የሚጨምርበት ሁኔታ በመምከር አዎታዊ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡ በዓለም ዓቀፉ ገበያ የኢትዮጵያ የቡና ወጪ ንግድ አቅርቦት አሁን ካለበት መጠ

1433ኛው የዒድ አል አድሃ አረፋ በዓል ዛሬ እየተከበረ ነው

Image
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) 1ሺህ 433 ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው ። ከስያሜው ጀምሮ ከነቢያት አባት ከኢብራሂም አሌሂሰላም ታሪክ ጋር ቀጥተኛ ተዛምዶ ያለው የአረፋ በዓል ፥ የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ የእርሳቸውን ታሪክ በማስታወስ ለሰው ልጅ ደህንነት የከፈሉትን መስዋዕትነት በየዓመቱ የሚዘክሩበት በዓል ነው ። በቅዱስ ቁርአን እንደመለከተው ነብዩ ኢብራሂም ልጃቸው እስማኤልን በአላህ ትእዛዝ ለመስዋት ሲያዘጋጁ ፤ በምትኩ ሙክት በግ መስዋት መቅረቡን ያሳያል በዚህም ኢድ አል አድሃ የመስዋት በዓል ተብሎ ይከበራል። በዓሉ ኢድ አልአድሃ ተብሎ የሚከበረውም ኡዲሂያ ወይም መስዋዕት ስለሚታረድ መሆኑን ፥ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ አህመዲን ሼህ አብዱላሂ ጨሎ ይናገራሉ። በዚህ ታላቅ ሃይማኖታዊ ቀን እርስ በርስ መዘያየርና ደስታን መገላለጽ በፈጣሪ ዘንድ በእጅጉ የሚወደድ ተግባር ነውና ከሁሉም ይህ ይጠበቃል። በአሉ ሲከበርም ሁሉም የእምነቱ ተከታይ በዓሉን በደስታ ያከብር ዘንድ ያለው ለሌለው መዘየር ዋነኛ ተግባር ይሆናል። በኢድ ቀን ከሚፈጸሙት ኢባዳዎች አንዱ ኡዲሂያ ሲሆን ፥ ለኡሂዲያ ከሚታረደው ከብት መካከል ለጎረቤትና ለተቸገሩ ማጋራት የእምነቱ ስርዓት ያዛል። የበአሉ አካል የሆነው የስግደት ስነ ስርዓት /ሶላት/ ማለዳ 1 ሰዓት ከ30 ላይ በጋራ በየአካባቢው እየተካሄደ  ሲሆን ፥ በመዲናችን አዲስ አበባም የሶላት ስነ ስርዓቱ በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተፈጸመ ይገኛል ።  የበአሉ አካል የሆነው የስግደት ስነስርዓት /ሶላት/ ማለዳ ላይ በጋራ በየአካባቢው የተካሄደ  ሲሆን ፥በመዲናችን አዲስ አበባም የሶላት ስነስርዓቱ በአዲስ አበባ ስታዲየም በ

የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ለአቶ መለስ መታሰቢያነት እንዲውል ተወሰነ

Image
የዘንድሮው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መታሰቢያነት በማዋል እንዲከበር መወሰኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ እንደ ዋልታ ዘገባ፣ ከመጪው ኅዳር ወር መጀመርያ አንስቶ ለአንድ ወር በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በየደረጃው የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ክብረ በዓል መታሰቢያነቱ በሞት ለተለዩት አቶ መለስ እንዲሆን የወሰነው ምክር ቤቱ ነው፡፡ ምክር ቤቱ ይህን የወሰነው ባለራዕዩ መሪ ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች እኩልነት አብዛኛውን ዕድሜያቸውን በፅናት የታገሉለት ዓላማ ስለነበር ነው መባሉን ዘገባው አስረድቷል፡፡ የዘንድሮ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን “ብዙም አንድም ሆነን የታላቁ መሪ ራዕይ በሕገ መንግሥታችን ለህዳሴያችን” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተጠቁሞ፣ ከመጪው ወር መጀመርያ ጀምሮ በአገሪቱ ሁሉም ቀበሌዎች ውይይት እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡ በብሔራዊ ደረጃ ኅዳር 29 ቀን በባህር ዳር ከተማ በዓሉን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ዘገባው አመልክቷል፡፡