Posts

Traditional Sidama Tales

Image
link

በደቡብ ክልል በ2ዐዐ4 ዓ/ም በሁሉም ዘርፎች ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን የደኢህዴን ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የደኢህዴን ከፍተኛ አመራሮች እያካሄዱ ባሉት 6ኛ ቀን የግምገማና የስልጠና መድረክ ላይ ያለፈው ዓመት በርካታ ተግባራት የተከናወነበት ዓመት መሆኑን ገምግሟል፡፡ በግብርናው ዘርፍ በተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት ውስጥ በከፋ ዞን የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተደረገው ጥረት ከ75 ሚሊዮን በላይ የቡና ችግኝ መተከሉን በአብነት አንስቷል፡፡ በሰብል ምርትና ምርታማነት ረገድ በክልሉ ማዕከላዊ ዞኖች ውስጥ በስልጤ፣ በሀድያ፣ በከምባታ ጠምባሮና በወላይታ ዞኖች ውስጥ ከፍተኛ የሰብል ምርት እድገት መመዝገቡ ተገልጿል፡፡ በመሆኑም ድርጅቱ ባካሄደው የ2ዐዐ4 ዓ/ም አፈፅፀም የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራትን በማስቀጠል የአቶ መለስ ዜናዊን ራዕይ በማሳካት የህዳሴ ጉዞን እውን ማድረግ በሚቻልበት ቁመና ላይ መድረሱንም ገልጿል፡፡ባልደረባችን ታሪኩ ለገሰ ዘግቧል፡፡ ማህበራቱ ውጤታማ እንዲሆኑና የቁጠባ ባህላቸውን እንዲያሳድጉ በወጪና ገቢ አያያዝ ላይ ስልጠና  እንደሚሰጥም ተናግረዋል፡፡ ሳሙኤል መንታሞ ከወልቂጤ ቅርንጫፍ እንደዘገበው፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/14TikTextN405.html

የዴሞክራሲ ስርዓትና መልካም አስተዳደር ለመገንባት የህግ የበላይነት መረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልሉ ለሚገኙ ዳኞች በወንጀለ ቅጣት አወሳሰን በግሙሩክና በታክስ ጉዳዮች የእስራት ቅጣት ዙሪያ በቡታጅራ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡          የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዝዳንት አቶ ታረቀኝ አበራ እንደተናገሩት መልካም አስተዳደር ለመገንባትና ልማትን ለማፋጠን እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ለማስቀጠል በህግ የበላይነት ላይ የተመሰረተ የፍትህ አሰጣጥ እንዲኖር የቅጣት አወሳሰን ወጥና ትክክለኛ መሆን አለበት፡፡ በወንጀል ፍትህ ስርዓት ውጤታማነትና ፍትሀዊነትን በማረጋገጥ ስራ ላይ ከዚህ በፊት የተለያዩ ችግሮች ይታዩ እንደነበር የጠቆሙት ኘሬዝዳንቱ ችግሩን ለመቅረፍ በቅጣት አወሳሰን ላይ ተቀራራቢ የሆነ የቅጣት አወሳሰን እንዲኖር እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ስልጠናው ሁሉም ዳኞች በተገቢው እውቀት ቅጣት አወሳሰድ ላይ ወጥ የሆነ ሥራ  እንዲሰሩ የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በስልጠናቸው ከክልሉ የተውጣጡ የዞኑ የወረዳ የፍርድ ቤት ኘሬዝዳንቶች እንዲሁም ዳኞች ተሳታፊ ሆነዋል ሲል የጠቅላይ ፍርድ ቤት የመንግሰት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዘግቧል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/13TikTextN105.html

ከ2ዐዐ2 ዓ/ም ጀምሮ በደቡብ ክልል ምክር ቤት አባልነት ሲያገለግሉ የቆዩት የተከበሩ አቶ ሀይሌ ባልቻ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡

ክቡር አቶ ኃይሌ ባልቻ ከወጣትነት እድሜያቸው ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማዎች የተመራውን ፀረ ፊውዳላዊ ተቃውሞ በወቅቱ የነበሩ የይርጋዓለም ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችም በትግል አጋርነት እንዲቀላቀሉ አስተባባሪ በመሆን መርተዋል፡፡ ክቡር አቶ ሀይሌ ባልቻ በደርግ ዘመን በ1997 ዓ/ም በተካሄደው ብሔራዊ ሸንጎ ምርጫ በጎርቼ ምርጫ ክልል በእጩነት ቀርበው የደርግ ሥርዓት እስከ ተወገደበት እስከ 1983 ዓ/ም ድረስ የመርጣቸው ህዝብ መብት መከበር የበኩላቸውን ድርሻ ማበርከታቸውን የህይወት ታሪካቸው ይገልፃል፡፡ በማህበሪዊ ህይወታቸውም የስኳር በሽታ ህሙማን የሆኑና ከፍለው መታከም የማይችሉ የሀዋሣና የአካባቢው ታማሚዎችን በማስተባበር የስኳር ህሙማን ማህበር በማቋቋም የህክምና እርዳታና ስለ በሽታው ግንዛቤ እንዲያገኙ በጎ ተግባርን ፈፅመዋል፡፡ በቤተሰብ ህይወታቸውም ሴት ልጅን በማስተማር በአካባቢው ህብረተሰብ ዘንድ እንደ መልካም አርአያ ይቆጠሩ አንደነበር የህይወት ታሪካቸው ያመለክታል፡፡ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ጥቅምት 12/2ዐዐ5  ሲፈፀም ሥነ ሥርዓቱ ላይ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጨምሮ የከልል፣ የሲዳማ ዞንና የሀዋሣ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል፡፡ ክቡር አቶ ሀይሌ ባልቻ ባለትዳርና የ6 ወንድና የ4 ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡ የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች እንደዘገበው፡፡

መምህራንን ለመመዘን ዝግጅቱ ተጠናቅቋል

Image
ሃዋሳ፡- የመምህራንን የሙያ ምዘና ለማካሄድ ዝግጅት መጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ። የመጀመሪያው የመምህራን ምዘና በሕዳር 2005 መጨረሻ እንደሚካሄድ አስታወቀ። የደቡብ ክልል 18ኛ አጠቃላይ የትምህርት ጉባዔ ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ ሲዳማ ባህል አዳራሽ በተካሄደበት ወቅት በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን ሙያ ፈቃድ አሠጣጥና እድሳት ዳይሬክተር አቶ ሳህሉ ባይሳ እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት የመምህራንን የሙያ ምዘና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማካሄድ በመንግሥት በኩል ዋና ዋና ዝግጅቶች ተጠናቅ ቀዋል። ለምዘና ሥራው የሚረዱ ስታንዳርዶችን የማውጣትና እነዚህን ለማስፈፀም የሚረዱ መመሪያዎችን የማዘጋጀቱ ሥራ መጠናቀቁን የገለጹት አቶ ሳህሉ፤ ለምዘና ሥራው አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁስ መዘጋጀታቸውን አስረድተዋል። የፈተናው ዝግጅት ሥራም በትምህርት ሚኒስቴር በኩል እየተከናወነ መሆኑንና በተያዘው ዓመት መጀመሪያ ተጨባጭ ተግባራት ለመጀመር መታቀዱን አብራርተዋል። በአገራችን የመምህራን ሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ሥርዓት ሲጀመር ይህ የመጀመሪያው እንደሚሆን አቶ ሳህሉ ገልጸው፤ የመምህራን ምዘና ለትምህርት ጥራት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመዋል። መምህራን በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሠረት ሙያቸውን እየፈፀሙ መሆኑን ለማወቅ እንደሚያስችልም ተናግረዋል። የምዘና ሥራው በዋናነት በክልሎች እንደሚመራ የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ ትምህርት ሚኒስቴር ስታንዳርዶችንና መመሪያዎችን የማውጣትና የምዘና ሥራውን በበላይነት የመቆጣጠር ሥራ እንደሚያከናውን አስረድተዋል። በቅርቡ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠው ፈተና በትምህርት ሚኒስቴር እንደሚዘጋጅና በቀጣይ ፈተናው በክልሎች የሚዘጋጅ መሆኑንም አስረድተዋል። ፈተናውን የመምራትና የማስተዳደር ኃላፊነትም የክልሎች እንደሚሆን አስታውቀዋል።