Posts

“ኢትዮጵያ - አነቃቂ ጉዞ፤” አዲስ መጽሃፍ

Image
የኢትዮጵያን የተፈጥሮ መስህብና ቅርሶች፥ የሕዝቦቿን ባህል፤ ልማድ፥ ወጎችና አናኗር፤ እንዲሁም ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች፤ ማራኪ የመልክዓ ምድራዊ ትእይንትና ተፈጥሮ፥ በካሜራው መነጽር ቀርጾ ያስቀረውን ምስል ለአንባቢያን እይታና ንባብ ካበቃ ወጣት ባለ ሞያ ጋር የተካሄደ ቃለ ምልልስ ነው።   እሱባለው መዓዛ ይባላል። ነዋሪነቱ በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በአሌግዛድሪያ ከተማ ነው። ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ ለበርካታ ጊዜያት ወደ ልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በተደጋጋሚ ባደረጋቸው ጉብኝቶች ወቅት ባነሳቸው የፎቶ ግራፍ ምስሎች የተዋበ መጽሃፍ ነው።  “ኢትዮጵያ - አነቃቂ ጉዞ፤” ይሰኛል http://amharic.voanews.com/

የትምህርት ባለድርሻ አካላት ለተማሪ ውጤት ትኩረት እንዲሰጡ ይደረጋል

Image
ሀ ዋሳ፦ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ለተማሪ ውጤትና ሥነ ምግባር መሻሻል ትኩረት እንዲሠጡ ማድረግ የዘንድሮ የትምህርት ዘመን ቁልፍ ተግባሩ መሆኑን የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ። በክልሉ በ2004 ዓ.ም በትምህርት ሥራ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራን፣ ተማሪዎችና ሱፐርቫይዘሮች ተሸለሙ። በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት 18ኛ አጠቃላይ የትምህርት ጉባኤ ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ በተካሄደበት ወቅቱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ አህመዲን እንደገለጹት፤ የተጀመረውን የትምህርት ልማት ሠራዊት ግንባታ ሥራ በማጠናከር ባለድርሻ አካላት ለተማሪ ውጤትና ሥነምግባር መሻሻል ትኩረት ሰጥተው እንዲሠሩ ማድረግ የበጀት ዓመቱ ቁልፍ ተግባር ነው። ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት በክልሉ በትምህርት ሠራዊት ግንባታ ሥራ መሠረት መጣሉን አስታውሰው፣ በ2005 ዓ.ም ሠራዊቱ ትክክለኛ ቁመና ተላብሶና የተቆጠረ ተግባር ወስዶ በተማሪዎች ውጤት ላይ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጣ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ አስታውቀዋል። ዘንድሮ በትምህርት ልማት ሠራዊት ውስጥ ያሉ ባለድርሻ አካላትን ውጤት ሊያመጣ በሚችል መልኩ ለማንቀሳቀስ መታሰቡን ያመለከቱት አቶ አህመድ፤ በሚሌኒየሙና በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ የተቀመጡትን ግቦች ከማሳካት አኳያ በተያዘው ዓመት ለትምህርት ተደራሽነት ሥራም ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጥ አመልክተዋል። በጎልማሶች ትምህርት ላይም የተሻለ ሥራ ለመሥራት መታቀዱን አብራርተዋል። የትምህርትን ጥራት የሚያረጋግጥ ሥራ በዋናነት የሚመራው በመምህሩ እንደሆነ ጠቁመው፤ ክልሉ የመምህራንን አቅም ለማጎልበት የቅድመ ሥራ ላይ ሥልጠና፣ የሥራ ላይ ሥልጠናና አጫጭር ሥልጠናዎችን እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል በቅርቡ ከ35ሺ

ኢትዮጵያ የንቅናቄውን 15ኛ ዓለም ዓቀፍ ጉባዔ ከጥቅምት 12 ጀምሮ ታስተናግዳለች

Image
አዲስ አበባ ጥቅምት 10/2005 ኢትዮጵያ 15ኛውን የትብብር ለታዳጊ ከተሞችና ልማት ንቅናቄ(ኮዳቱ)ን ዓለም ዓቀፍ ጉባዔን ለማስተናገድ ዝግጅቷን ማጠናቀቋን የጉባዔው ዝግጅት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከድርጅቱ ጋር በመተባበር ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ለአራት ቀናት በአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ " የከተሞች ጉዞ ለከተሞች አደረጃጀትና እድገት" በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል፡፡ የኮሚቴው ሰብሳቢና የአንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ በድሉ አሰፋ ዝግጅቱን አስመልክቶ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ጉባዔው በከተማዋ የሚካሄደውን ፈጣን የለውጥ ጉዞ አጠናክሮ ለመቀጠል ያግዛል፡፡ ጉባዔው በከተማዋ በትራንስፖርት ዘርፍ ያለውን ዕድገት፣ ተሞክሮዎችንና አማራጮችን ለአገሪቷ በሚስማማ ሁኔታ ለመጠቀም እንደሚያስችልም አስረድተዋል። በጉባዔው ላይ ከ600 በላይ የከተሞች የትራንስፖርት አመራር አባላትና ባለሀብቶች እንደሚሳተፉበትና ከዚህ ወስጥ ከ250በላይ የሚሆኑት የአገር ውስጥ ተሳታፊዎች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ እንዲሁም የከተማዋን እምቅ የኢንቨስትመንትና የንግድ አማራጮችን ለማስተዋወቅና የቱሪዝም መስህቦችን ለማስተዋቅ መልካም ዕድል እንደሚፈጥርም ሰብሳቢው ገልጸዋል፡፡ በጉባዔው ላይ የ30 አገሮች ተጨባጭ ተሞክሮዎች ይቀርባሉ ያሉት ሰብሳቢው፣በዚህም የሌሎች አገሮችን ልምድ ለመቅሰም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አስረድተዋል፡፡ የጉባዔው ተሳታፊዎች አገሪቱን ለማወቅ የሚያስችላቸው ድረ ገጽ መከፈቱንና የትራንስፖርት አገልግሎት መዘጋጀቱን አቶ በድሉ ተናግረዋል፡፡ እንዲሁም በእንግሊዝኛና በፈረንሳይና ቋንቋዎች ትርጉምና መረጃ በመስጠትና በማስተላለፍ በኩል ሁለገብ አገልግሎት የሚሰጡ ወጣት ባለሙያዎች መዘጋጀታቸው

የሲዳማ ኣርነት ግንባር ሊቀመንበር ካላ ቤታና ሆጤሳ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሰይፌ ነበልባል ሬዲዮ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ

Image
ከካላ ቤታና ሆጤሳ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ከ5 ደቂቃ ጀምሮ  ይከታተሉ።

ጉዞ ኃይለ ማርያም - ከአረካ እስከ አራት ኪሎ

Image
በዮናስ አብይ የ43 ዓመቱ ጐልማሳ መንገሻ መንዳዶ የተወለደባትንና አድጐ የተማረባትን አነስተኛዋን የአረካ ከተማን ለቆ መኖርያውን በአርባ ምንጭ ከተማ ካደረገ ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ አስቆጥሯል፡፡ ዛሬ የሥራ ጠባዩ በፈጠረለት አጋጣሚ ሙሉ ጊዜውንና ኑሮውን በአርባ ምንጭ ላይ በመመሥረቱ አልፎ አልፎ በአዕምሮው ውልብ ከሚሉበት ትዝታዎች በስተቀር ስለተወለደባት የአረካ ከተማ ሲያወሳ አይሰማም፡፡ ነገር ግን ስለተወለደባት ከተማ ከማይረሳቸው የልጅነት ትውስታዎቹ ውስጥ አንድ አስገራሚ ታሪክን ከተማሪነት ዘመኑ መዝዞ በፈገግታና ኩራት በተሞላበት ሁኔታ ሲያወጋ፣ ያድማጭን ጆሮ በጉጉት ሊያቆም እንደሚችል በቅድሚያ ከገጽታው ደማቅነት መረዳት ይቻላል፡፡ የታሪኩ ክስተት ወደኋላ 28 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ 300 ኪሎ ሜትር በምትርቀው በአረካ ከተማና በነዋሪዎቿ ታላቅ የመደነቅ ስሜትን ስለፈጠረ  የአንድ ጎበዝ ተማሪን አስደናቂ ጉዳይ ያወሳል፡፡ መንገሻ በወቅቱ ከሚማርበት የአረካ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይልቅ ከከተማዋ ዕምብርት ሦስት ኪሎ ሜትር ርቀት ስለሚገኘው ዱቦ የካቶሊክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ስላለ አንድ ተማሪ ጉብዝና መስማትና ማውራት ይመስጠው ነበር፡፡ “በዚያ የሕፃንነት ዕድሜ ሁሉም ሰው ስለሱ ጉብዝና ብቻ ሲወራ ትዝ ይለኛል፡፡ እኔም በእኛ ትምህርት ቤት ውስጥ ካሉ ጐበዝ ተማሪዎች ይልቅ በዚያኛው ትምህርት ቤት ስላለው ጐበዝ ተማሪ ብሰማም ባወራም አልጠግም ነበር፤” በማለት የሚናገረው መንገሻ አገለለጹና ገጽታው ይህ ታሪክ እንኳን 28 ዓመታት ቀርቶ አሥር ዓመት የሞላው አይመስልም፡፡ በነዚያ ዘመናት ውስጥ እነ መንገሻ ከሚኖሩበት ከተማ አልፎ በድፍን ቦሎሶ ሶሬ በጉብዝናውና በቀለም ትምህርት አያያዙ “ያሳድግህ” ተብሎ