Posts

የሲዳማ የፖለቲካ ፓርቲዎች

ከታዛቢው ሲኣን በሲዳማ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ከመስጠት ያለፈ ስራ ስሰራ ኣይታይም የሲዳማ ዲያስፖራ የፖለቲካ ድርጅቶች የኢንተርኔት ላይ ኣንበሶች ናቸው ይሄ ቀጥዬ የማቀረበው ኣስተያየት የእኔ የግሌ ኣስተያየት ነው። ምናልባት በእኔ ማንነት ላይ ጥርጣሬ ቢኖር እኔ የመንግስት ደጋፊ ወይም ተቃዋሚም ኣይደለሁ፤ እንዲሁም የተቃዋሚዎች ደጋፊም ሆነ የተቃዋሚዎች ተቃዋሚም ኣይደለሁ። እኔ የሲዳም ህዝብ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መብቶች ስከበሩ ማየት የምሻ የሲዳማ ህዝብ ተቆርቋር ነኝ። እባካችሁ ከዚህ ባለፈ ሌላ ስም ኣትለጥፉብኝ ኣደራ። ስለ እራሴ ይህንን ያህል ካልኩ ወደ ጉዳዬ ልለፍ፦ በተለይ ካለፉት ሶስት ወራት ወዲህ ሲዳማ በፖለቲካ ትኩሳት ውስጥ ናት ማለት ይቻላል። በተለይ ከክልል ጥያቄ እና ከሃዋሳ ከተማ የወደፊት እጣ ፋንታ በምወሰኑ ጉዳዮች ላይ ህዝቡ ከመንግስት ጋር ተፋጦ መክረሙ ይታወሳል። ታዲያ ይህ ፍጥጫ ከፍጥጫነት ኣልፎ ወይም ኣፍትልኮ የወጣበትም ኣጋጣም ተከስቶ ነበረ በተለይ በወረዳዎች ኣከባቢ። የሆነ ሆኖ ዛሬ ግን ፍጥጫው እየረገበ ያለ ይመስላል። ይህንን ያነሳሁት ያለፈ ታሪክ ልተርክላችሁ ብዬ ኣይደለም፤ ያነሳሁበት ዋናው ምክንያት ስለ ሲዳማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የታዘብኩትን ጀባ ልላችሁ ብየ ነው። ምን ታዘብክ ብላችሁ ጠይቁኝ ታዲያ ! ኣዎን የሲዳማ የፖለቲካ ድርጅቶችን ብዙ እየታዘብኩ ነው። ለመሆኑ የሲዳማ የፖለቲካ ፓርቲዎች እነማናቸው ? ይመስለኛል ስለ ፓርቲዎቹ ማውራታችን ካልቀረ ስለ ማንነታቸው በስሱ ማንሳቱ የግድ ይመስለኛል። እኔ ከልጅነተ ጀምሮ የማውቀው ኣንዳንዴ ስለው ተቃዋሚ ስለው ደግሞ የመንግስት ደጋፊ እየሆነ ሁለት መልክ የሚይዘው የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ( ሲኣን ) ከቀድሞው ሲ

በሲዳማ ዞን የአማራጭ ኢነርጂ ልማት በመጠናከር ላይ ነው

Image
ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ በተካሄደው የደቡብ ክልል የውሃ ጉባኤ የቀረበው የ 2004 ኣ / ም የመምሪያው የስራ ኣፈጻጸም የተመለከተው ኣንድሪፖርት እንዳመለከተው በዞኑ ውስጥ በኣማራጭ ኢነርጂ ልማት ዘርፍ ኣበራታች ስራዎች ተከናውነዋል። መምሪያው በባጀት ኣመቱ ለማከናወን ካቀዳቸው 19 አዲስ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አምራቾች ማህበራት እንዲቋቋሙ በማድረግ ለ 3- ማህበራት ፕሬስና ሞልድ ተገዝቶ ድጋፍ ማድረጉ የተገለጸ ሲሆን፤ በ 19 ወረዳዎች በ 38 አማካይ ቦታዎች የማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ላይ ለሕ ብረተ ሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በመስጠት ከእቅዱ በላይ በመስራት 4500 የተሻሻሉ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎ አንዲሰራጩ በማድረግ በርካታ የዞኑን ነዋሪዎች ተጠቃሚ  ኣድርጓል ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሁሉም ወረዳዎች 100 የሚሆኑ የቤተሰብ የሶላር ተጠቃሚ ማህበራት መደራጀታቸው ሲገለጽ፤ የኃይል አማራጭ ኢነርጂ አጠቃቀም ላይ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል። እንደሪፖርቱ ከሆነ የሶላር ኢነርጂ ተከላ እና የባዮ ጋዝ ግንባታ በተለያዩ ወረዳዎች የተካሄደ ሲሆን፤ ኣራት የአማራጭ ኢነርጂ ዳሰሳ ጥናት ም ተከናውነዋል።

ዘንድሮ ለሚካሄደው የአካባቢ ምርጫ ዝግጅት እየተደረገ ነው

Image
አዲስ አበባ ጥቅምት 9/2005 (ዋኢማ)  - ዘንድሮ የሚካሄደውን የአካባቢ ምርጫ ግልጽ፣ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ዝግጅቶች እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የቦርዱ ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ይስማ ጅሩ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለጹት ምርጫውን ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ  ለማድረግ የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች ከወዲሁ እየተከናወኑ ነው። በተለያየ ደረጃ የነበሩ የምርጫ ጣቢያዎችን በአዲስ መልክ በማደራጀት በኦሮሚያ፤ በትግራይ፤ በአማራና በደቡብ ክልሎች ለሚገኙ የምርጫ አስፈጻሚ አባላት  የአቅም ግንባታ ስልጠናመሰጠቱን  የገለጹት አቶ  ይስማ ለፖለቲካ ፓርቲዎችም በእጩዎች አቀራረብ ዙሪያ  ስልጠና ተሰጥቷል ብለዋል። የእጩ ተመራጮችና የመራጮች  ምዝገባ እንደዚሁም  ምርጫው የሚካሄድበት የጊዜ ሰሌዳ ከፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር በመወያየት  ወደፊት እንደሚወሰን አቶ ይሰማ ገልጸዋል። በአካባቢ ምርጫው የወረዳ፤ የቀበሌ ፤የማዘጋጃ ቤት፤ የከተማ አስተዳደርና የዞን ምክር ቤቶች አባላት እንደሚመረጡ የገለጹት አቶ ይስማ  ምርጫውን በስኬት ለማጠናቀቅ መላው ህብረተሰብ  የበኩሉን ተሳትፎ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

በሀገሪቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የውጭና የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች በማዕድን ፍለጋና ልማት ላይ ተሰማርተዋል

Image
ሃዋሳ ጥቅምት 09/2005 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቱ በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የውጭና የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች በማዕድን ፍለጋና ልማት ላይ መሰማራታቸውን የማዕድን ሚኒስትሯ ገለጹ፡፡ ስለማዕድን ኢንዱስትሪ ግልጽነት ኢኒሼቲቭ አሰራር ለበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ግንዛቤ ለማስጨበጥ በሀዋሳ ከተማ ትናንት በተዘጋጀው አውደ ጥናት ላይ ሚኒስትሯ ወይዘሮ ስንቅነሽ እጅጉ እንደገለጹት ባለሀብቶቹ በዑጋዴን፣ በመቀሌ፣ በአባይ፣ በኦሞና በጋምቤላ በርካታ ኩባንያዎች በማዕድን ቆፋሮ ላይ ተሰማርተዋል፡፡ ማዳበሪያ፣ መስተዋት፣ ሳሙናና ሌሎችን ለማምረት በግብዓትነት የሚጠቅሙ በርካታ የማዕድን ሃብቶች እንዳሉ ያስረዱት ሚኒስትሯ በነዳጅ ዘርፍም በተለያዩ ሥፍራዎች ፍለጋው መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡  ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልካቸው የምርት ዓይነቶች የማዕድን ሃብት 20 በመቶውን እንደሚይዝና ለሀገሪቱ ዘላቂ ልማት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ለማጎልበት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ብቻ የወርቅ ፣ የታንተለም፣ የጌጣጌጥና የመሳሰሉት የማዕድን ጥሬ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ ከ460 ሚልዮን በላይ ዶላር የውጭ ምንዛሬ መገኘቱንና በዚሀ ዓመትም ይህንን በእጥፍ ለማሳደግ እየሰሩ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ኢትዮጵያ በማዕድን ፍለጋና ምርመራ ስራ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያላት ሀገር ናት ያሉት ሚኒስትሯ የማዕድን ሃብት አለኝታ ጥናት በተለያዩ ወቅቶች በውጭና በሀገር ውስጥ የስነ ምድር ባለሙያዎች ሲከናወን መቆየቱን ተናግረዋል፡፡ እስከአሁን በተደረጉ ጥናቶች የኢንዱስትሪ፣ የኮንስትራክሽን፣ የጌጣ ጌጥ ፣ የወርቅ፣ የብረታ ብረት፣ የሃይድሮ ካርቦን ክምችትና የጂኦተርማል ማዕድናት መኖራቸው መረጋገጡን ጠቁመዋል፡፡  የማዕድን ኢንዱስትሪ

የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል

ሃዋሳ ጥቅምት 09/2005 የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የድርሻቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለፀ፡፡ በሀዋሳ ሲካሄድ የቆየው የክልሉ ትምህርት ቢሮ የ2004 አጠቃላይ የትምህርት ጉባዔ ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል፡፡ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች፣ ባለድርሻ አካላትና የትምህርት አመራሮች ማበረታቻ ሽልማትና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ መሃመድ አህመዲን በዚሁ ወቅት እንደገለጹት የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ ሁሉም የህብረተሰብ ከፍልና ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል፡፡ ክልሉ ከፍተኛ በጀት በመመደብ የሳይንስ ዘርፍ ትምህርትን ለማጠናከር ኮምፒዩተሮች እንደሟሉና የቤተ ሙከራ ግብአቶችን በማቅረብ አበረታች ስራ እያከናወነ ነው ብለዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመስራት ለትምህርቱ ጥራት ልዩ ትኩረት በመስጠትና በአግባቡ እንዲመራ በማድረግ በኩል ለሌሎች አርአያ እንዲሆን የሚያስችል ስራ ማከናወኑን አመልከተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ከ30 ሺህ በላይ የወላጅና የመምህራን ህብረት አመራሮች በትምህርት ቤቶች በመደራጀት በየጊዜው የተለያየ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጣቸው መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል ለትምህርት ቤቶች ድጋፍና ክትትል በማድረግ የትምህርት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ በማድረግ በኩል አበረታች ሥራ መከናወኑን ገልጸዋል፡፡ በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት ካመጡት ተማሪዎች መካከል ተማሪ ቤተልሄም ታሪኩ፣ ገዛህኝ አበራ፣ ኢዩኤል ተከተልና ተማሪ ዲቦራ አበራ በሰጡት አስተያየት በትምህርት ቤቶች የተፈጠሩ አደረጃጀቶች፣ የመምህራን የዕለት ተዕለት ክትትልና አስፈላጊ የትምህርት ግ