Posts

Colorado State University’s(CSU) delegates

Image
Colorado State University’s(CSU) delegates продвижение сайтов Category:  News Published on Friday, 05 October 2012 15:55 Hits: 216 A team of 7 delegates from Colorado State University’s(CSU)Agricultural  Science College have convened here at Hawassa University’s  (HwU) Agricultural College  on 01/10 /2012 .According to Dr.Yibra, DeanHwU’s College of Agriculture, his College has started collaboration with CSUon small projects and now the aim of the delegates visit is to scale up this collaboration.   He noted that the new collaboration framework mainly focuses on teaching learning, capacity building, agricultural extension and research.  He added,they will have five days stay in his College and in their stay,introduction between schools and departments of the two sister colleges will be held;strategies will be developed on how and which area to work together to contribute to the development of Ethiopia ,and finally action plan/roadmap  will be prepared. Then,in a

ሃዋሳ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹመት

Image
ከወሰንሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ) እንደመነሻ “አዳራሽ ተቀምጣ ስታበላ ሥጋ ስታጠጣ ጠጅ  ስዕል ትመስላለች የምኒሊክ ልጅ”        እንዲህ ሆነ፡-  ዕለተ እሁድ መስከረም 27 ቀን 2005 ዓ.ም ረፋዱ ላይ ድንገት ብድግ ብዬ ወደ ሃዋሳ መረሽኩ፡፡ የሁለት ቅን እና ትንታግ ወጣቶች (መስከረም እና ፍፁም) ደግነት ነው ወደ ሃዋሣ ያንደረደረኝ፡፡ የእንዳልክና የፀሃይም ደግነት የጉድ ነው፡፡ እነሆ ሃዋሳን ለሁለተኛ ጊዜ ረገጥኳት፡፡ ድንቅ ከተማ ናት፡፡ አውራጎዳናዎቿ የተወለወሉ ይመስላሉ፡፡ አንድ ወጥ የሆነ መልክና ፋት አላቸው፡፡ እንደእኔ ዓይነቱን አልፎሂያጅ መንገደኛ “ሊያምታቱ” ይችላሉ፡፡ አቀያየሳቸውም አነጣጠፋቸውም ፍፁም ተመሳሳይ ለሆነ ወደሌላ ቦታ መሄድ ያሰበ ሰው ተጉዞ ተጉዞ ራሱን እዚያው የተነሳበት ቦታ ሊያገኘው ይችላል፡፡ ስለዚህ ከከተማዋ አንድ ጥግ ወደሌላ ጥግ መሄድ የፈለገ ሰው፣ ጉዞ ከመጀመሩ በፊት ቆም ብሎ እንደአሸን እየፈሉ ካሉት ትልልቅ ሕንፃዎች መሃል አንዱን በምልክትነት ማስተዋል አለበት፡፡ የሃዋሣ መንገዶች ፍፁማዊ አንድወጥነት አስገርሞኝ ዋዘኛ ጥያቄ የሰነዘርኩለት ወዳጄ “ሃዋሣ አዙሪት ነገር አለባት የሚባለው ለዚህ ነው” የሚል ምላሽ ነበር የሰጠኝ፡፡ የሆኖ ሆኖ ሃዋሳ አ/አበባን የምትስንቅ ፅዱና ውብ ከተማ ናት፡፡ ሙሉ ጽሁፉን እዚህ ላይ ያንቡ

ዋልያዎቹ ቃል የተገባላቸውን ማበረታቻ ነገ ይቀበላሉ

Image
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 5 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋልያዎቹ ቃል የተገባላቸውን የማበረታቻ ሽልማት ነገ በኤድናሞል ህንጻ በሚከናወን ስነ ስርአት ይቀበላሉ።  የኢትዮጽያ ብሄራዊ ቡድን ለ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሚያልፍ ከሆነ የተለያዩ ድርጀቶችና ግለሰቦች የማበረታቻ ሽልማት እንደሚሰጡ ቃል መግባታቸው ይታወሳል። ከነዚህ መሀልም የኤድናሞል ባለቤት አቶ ተክለብርሀን አምባዬ ፥ የብሄራዊ ቡድኑ የልምምድ ሜዳ በመገኘት ለእያንዳንዱ ተጫዋች ለመስጠት ቃል የገቡትን ፥ የ25 ሺህ ብር ሽልማት ነገ ከ5 ሰአት ጀምሮ በኤድናሞል በሚከናወነው ስነ ስርአት ያበረክታሉ።  በነገው እለት በሚከናወነው በዚህ የማበረታቻ ፕሮግራም ከገንዘብ ሽልማቱ በተጨማሪ ፥ ለቡድኑ አባላት በሙሉ የምሳ ግብዣ እንደሚደረግላቸው ባልደረባቸን አራያት ራያ ዘግባለች።  ድሉን ተከትሎ የሚድሮክ ባለቤት ሼክ ሙሀመድ አሊ አላሙዲ ለብሄራዊ ቡድኑ በአጠቃላይ የአምስት ሚሊየን ብር የማበረታቻ ሽልማት እንደሚሰጡ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።

አዲሱ የዓለም ኢኮኖሚ ጨዋታ ለአፍሪካና ለምዕራቡ ዓለም ስጋት

Image
በብርሃኑ ፈቃደ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደ ፖለቲካው ሁሉ በኢኮኖሚ ባለሙያዎችም ዘንድ የሚወናጨፍ ፖለቲካ ቀድ አገላለጽ መንሰራፋት ይዟል፡፡ በተለይ የኃይል ሚዛኑ በእስያዎቹና በምዕራባውያኑ ዘንድ በሚያሻኩትበት በዚህ ዘመን፣ አፍሪካና ደቡብ አሜሪካ፣ በኢኮኖሚ ኒዮ ኢምፔሪያሊዝም አዙሪት እየተናጡ መሆናቸውን ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ይህንን ርዕሰ ጉዳይ አንስተው ሞቅ ያለ ውይይት የሚያነሱና ጣት የሚቀስሩ ዲፕሎማቶች (ያውም ከእስያውያኑ ጎራ ሆነው) ሩቅም ሳይኬድ እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ ማግኘት ይቻላል፡፡ አንዳንዶች  ደግሞ የ‹‹ጂኦ ኢኮኖሚክስ›› ንድፈ ሐሳብን ቀምረው ቱባ መጻሕፍትን እያወጡ በማስነበብ ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ባለንበት የነጮቹ ዓመት ተጽፎ ለንባብ የበቃውና ክላውስ ሶልበርግ ሶይለን በተባሉ የኢኮኖሚ አዋቂ የተጻፈው መጽሐፍ የመግቢያ ቅኝቱን ከጂኦ ፖለቲካ ወደ ጂኦ ኢኮኖሚ የተደረገውን ጉዞ የሚያመላክት ነው፡፡ እንደ ጸሐፊው ገለጻ፣ ጂኦ ኢኮኖሚክስ በባህል፣ በቦታ እንዲሁም በውሱን ሀብቶች ስትራቴጂካዊነት ላይ የሚያነጣጥርና ለዚሁም ዓላማው በዘላቂነት ላይ የተመሠረተና ተወዳዳሪ ጥቅምን ለማግኘት ሲባል የሚካሄድ ድርጊትን የሚያጠና ክፍል ነው፡፡ በጂኦ ፖለቲካዊ ጽንሰ ሐሳብ ላይ ተንጠላጥሎና በዘመነ ግሎባላይዜሽን እየተተገበረ ያለ የኢኮኖሚክስ ዘርፍ እንደሆነም ይናገሩለታል፡፡ ይህም ሲባል ግን ከጂኦ ፖለቲካ የሚለይባቸው ሁለት መሠረታዊ መስኮች አልታጡም፡፡ እንደ ርዕሰ ጉዳዩ ሲያዩት ፖለቲካና ወታደራዊ ኃይል ላይ ከማተኮር ይልቅ ኢኮኖሚያዊ ኩነቶችን መምረጡ ከጂኦ ፖለቲካዊ እንዲለይ ያደርገዋል፡፡ ከዚህ ባሻገር ተውኔቱን የሚከውኑት ተዋንያኑ አገርን የሚወከሉ ግለሰቦች ሳይሆኑ የግል ዘርፉ ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩና ጅማሬም ፍጻሜያቸውም ለሚሠሩበት ተቋ

ሰሞኑን በመንግስት መገናኛ ብዙሃን የሲዳማ ክልል ጥያቄን እና የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደርን በተመለከተው በሲዳማ ኣመራር ስም በተሰጠው የኣቋም መግለጫ ኣብዛኛዎቹ ኣመራሮች ማዘናቸው ተገለጸ

ከኣመራር ኣባላቱ መካከል ስማቸው እንዲገለጸ ያልፈለጉት ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደተናገሩት፤ ከፌደራል እስከ ወረዳ ያሉት የሲዳማ ኣመራሮች ኣሳላፉ ተብሎው በመንግስት መገናኛ ብዙሃን የተሰራጨም የኣቋም መግለጫ የብዙዎቹን ኣመራር ኣቋም የማያንጸባርቅ እና በብዙሃኑ የሲዳማ ኣመራር ስም ጥቂቶች የግል ፖለቲካ ማስፈጸሚያነት ያስተላለፉት የ ኣቋም መግለጫ መሆኑን ተናግረዋል። ሰሞኑን በሲዳማ ክልል ጥያቄ እና በሃዋሳ ከተማ ኣሰተዳደር የወደፊት እጣ ፋንታ ላይ ብሎም የኣመራር ኣባላቱን ኣቋም በገመገመበት በዚህ ወቅት፤ የሲዳማ ክልል ጥያቄ የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ኣይደለም ካለመባሉ በላይ የክልል ጥያቄውን ያነሱ ኣካላት ጸረ ሲዳማ ናቸው ሲዳማን ኣይወክሉም ኣልተባለም ብለዋል። ምንም እንኳን መድረኩን ይመሩ የነበሩት የኣመራሩ ኣባላት በሲዳማ ክልል ጥያቄ ላይ ኣሉታዊ ኣመለካከት እንዲያዝ ከፍተኛ ግፊት ያደረጉባቸው ቢሆንም ቤቱ ግን በክልል ጥያቄ ኣስፈላጊነት ላይ የሞቀ ክርክር በማድረግ ተጋፍጧቸዋል ያሉ ሲሆን፤ በርካታ ሰኣት ከወሰደው ክርክር በኃላ የክልል ጥያቄው እንዲቆይ መስማማታቸውን እነዚሁ ኣስተያዬት ሰጪዎች ኣብራርተዋል። የኣገሪቷ መንግስት የጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ኣቶ መለስ ዜናዊ ሞትን ተከትሎ በሽግግር ላይ የምገኝ በመሆኑ የክልል ጥያቄው ለጊዜው እንዲዘገይ ለመደረጉ እንደ ዋነኛ ምክንያትነት መነሳቱን ኣስረድተዋል። ነገር ግን ጉባኤው ከተጠናቀቀ በኃላ በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን በተላላፈው ዜና ላይ የሲዳማ ክልል ጥያቄ ኣግባቢነት የሌለው መሆኑን እና የክልል ጥያቄውን ያነሱ ኣካላት ጸረ ሰላም ኃይሎች እንዲሁም የሲዳማን ህዝብ የማይወክሉ ተብለው መነቀፋቸው እንዳሳዘናቸው ገልጸው፤ በኣጠቃላይ የሲዳማ ኣመራር ስም በተሰጠውን ኣቋም