Posts

ሰሞኑን በመንግስት መገናኛ ብዙሃን የሲዳማ ክልል ጥያቄን እና የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደርን በተመለከተው በሲዳማ ኣመራር ስም በተሰጠው የኣቋም መግለጫ ኣብዛኛዎቹ ኣመራሮች ማዘናቸው ተገለጸ

ከኣመራር ኣባላቱ መካከል ስማቸው እንዲገለጸ ያልፈለጉት ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደተናገሩት፤ ከፌደራል እስከ ወረዳ ያሉት የሲዳማ ኣመራሮች ኣሳላፉ ተብሎው በመንግስት መገናኛ ብዙሃን የተሰራጨም የኣቋም መግለጫ የብዙዎቹን ኣመራር ኣቋም የማያንጸባርቅ እና በብዙሃኑ የሲዳማ ኣመራር ስም ጥቂቶች የግል ፖለቲካ ማስፈጸሚያነት ያስተላለፉት የ ኣቋም መግለጫ መሆኑን ተናግረዋል። ሰሞኑን በሲዳማ ክልል ጥያቄ እና በሃዋሳ ከተማ ኣሰተዳደር የወደፊት እጣ ፋንታ ላይ ብሎም የኣመራር ኣባላቱን ኣቋም በገመገመበት በዚህ ወቅት፤ የሲዳማ ክልል ጥያቄ የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ኣይደለም ካለመባሉ በላይ የክልል ጥያቄውን ያነሱ ኣካላት ጸረ ሲዳማ ናቸው ሲዳማን ኣይወክሉም ኣልተባለም ብለዋል። ምንም እንኳን መድረኩን ይመሩ የነበሩት የኣመራሩ ኣባላት በሲዳማ ክልል ጥያቄ ላይ ኣሉታዊ ኣመለካከት እንዲያዝ ከፍተኛ ግፊት ያደረጉባቸው ቢሆንም ቤቱ ግን በክልል ጥያቄ ኣስፈላጊነት ላይ የሞቀ ክርክር በማድረግ ተጋፍጧቸዋል ያሉ ሲሆን፤ በርካታ ሰኣት ከወሰደው ክርክር በኃላ የክልል ጥያቄው እንዲቆይ መስማማታቸውን እነዚሁ ኣስተያዬት ሰጪዎች ኣብራርተዋል። የኣገሪቷ መንግስት የጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ኣቶ መለስ ዜናዊ ሞትን ተከትሎ በሽግግር ላይ የምገኝ በመሆኑ የክልል ጥያቄው ለጊዜው እንዲዘገይ ለመደረጉ እንደ ዋነኛ ምክንያትነት መነሳቱን ኣስረድተዋል። ነገር ግን ጉባኤው ከተጠናቀቀ በኃላ በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን በተላላፈው ዜና ላይ የሲዳማ ክልል ጥያቄ ኣግባቢነት የሌለው መሆኑን እና የክልል ጥያቄውን ያነሱ ኣካላት ጸረ ሰላም ኃይሎች እንዲሁም የሲዳማን ህዝብ የማይወክሉ ተብለው መነቀፋቸው እንዳሳዘናቸው ገልጸው፤ በኣጠቃላይ የሲዳማ ኣመራር ስም በተሰጠውን ኣቋም

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከ31 አመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈ

Image
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ)  የኢትዮጵያ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለ2013ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ዛሬ ከሱዳን አቻው ጋር ባደረገው  የመልስ ጨዋታ ሁለት ለባዶ በማሸነፍ ከ31 አመታት ቆይታ በኋላ የአፍሪካ ዋንጫን ተቀላቀለ። 10 ሰአት ላይ በተጀመረው በዚህ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ65ኛው እና በ70ኛው ደቂቃ በአዳነ ግርማ እና ሳላዲን ሰኢድ ባስቆጠራቸው  ጎሎች ሁለት ለባዶ በማሸነፍ በደቡብ አፍሪካ ለሚካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን አረጋግጧል። በዛሬው ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በርካታ የግብ ማግባት እድሎችን ቢፈጥርም ሳይጠቀምባቸው ቀርቷል። በመጀመሪያ ጨዋታው ሱዳን ላይ 5 ለ3  ቢሸነፍም  በድምር  ውጤት 5 እኩል  ሆነው ከሜዳው ውጭ ባገባው ጎል አላፊ ሆኗል። ሰሞኑን ልምምዱን በኬኒያ ሲያደርግ የቆየው የሱዳን ብሄራዊ ቡድንም አርብ ምሽት አዲስ አበባ በመግባት ትናንት ቀለል ያለ ልምምድ ሲያደርግ ነበር። በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በኩል ግብ ጠባቂው ጀማል ጣሰው ተጎድቶ በመውጣቱ እና ቡድኑ ተቀያሪ ተጫዋቾችን በሙሉ ተጠቅሞ በመጨረሱ ፥ ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው አማካዩ አዲስ ህንጻ  የጀማልን ቦታ ሸፍኖ ቡድኑ በ10 ልጅ ጨዋታውን ለመጨረስ ተገዷል።

ካላ ደሴ ዳልኬ እና አቶ በረከት ስምኦንን ጨምሮ የመንግሥት ባለሥልጣናት በማስትሬት ዲግሪ ተመረቁ

Image
•    አብዛኞቹ በምረቃው ዕለት አልተገኙም በብርሃኑ ፈቃደ ፕሮፌሰር ባደግ በቀለ በመሠረቱት ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ኢንስቲትዩት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በትናንትናው ዕለት ከተመረቁት መካከል፣ በሚኒስትር ማዕረግ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦንን ጨምሮ በርካታ ባለሥልጣናት በማስትሬት ዲግሪ ተመረቁ፡፡ የማስትሬት ዲግሪያቸውን በትራንስፎርሜሽናል ሊደርሺፕ ዘርፍ የሠሩት አቶ በረከት በምረቃው ሥነ ሥርዓት አልተገኙም፡፡ እንደ አቶ በረከት ሁሉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ አቶ ደሴ ዳልኬ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር አብርሃም ተከስተ መስቀልም ካልተገኙት መካከል ናቸው፡፡ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሞሐመድ ኡመር፣ በመከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ኰማንደር ብርሃኑ ጁላ ገላቻን ጨምሮ በርካታ የመንግሥት ሹማምንት ተመርቀዋል፡፡ አቶ በረከት ለመመረቂያ ያቀረቡት ጽሑፍ እያደጉ ባሉ ልማታዊ መንግሥታት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፣ ‹‹Emerging Developmental States: Transformational Leadership in Governemnt›› በሚል ርዕስ በጻፉት መመረቂያቸው ዲግሪያቸውን እንዳገኙ ከኢንስቲትዩቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡  http://www.ethiopianreporter.com/news/293-news/8093-2012-10-13-14-27-28.html

የሲዳማ ህዝብ ክልል የመሆን ጥያቄ በማይመለከታቸዉ ግለሰቦችና የዉሸት መረጃዎቻቸዉ አይቀለበስም

Image
ከማህበራዊ መረብ ላይ የተገኘ ጽሁፍ በ Giwoommo Gimbi  ተጻፈ !የሲዳማ ህዝብ ክልል የመሆን ጥያቄ በማይመለከታቸዉ ግለሰቦችና የዉሸት መረጃዎቻቸዉ አይቀለበስም በቅርቡ የተካሄደዉ የሲዳማ ዞን አመራሮች ስብሰባ መላዉ የሲዳማ ህዝብ አቋሙን ለይቶ ከምን ጊዜዉም በተለየ መልኩ ራስን በራስ የማስተዳደር ወይም ክልል የመሆን ጥያቄዉን አጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያደርገዉ ነዉ፡፡ ይህ ጉዳይ በሁለት መልኩ ሊታይ ይችላል፡፡  Requests አንደኛዉ ሟቹ ጠቅላይ ሚንስቴር በህይወት በነበሩበት ወቅት ለሲዳማ ህዝብ ቃል የገቡት የክልል ጥያቄ መልስ ሳያገኝ ቢያልፉም የተኳቸዉ ጠቀላይ ሚንስቴር አዎንታዊ ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ የተጠበቀዉ ከንቱ መሆኑ ነዉ፡፡ በአቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ የተመራዉ የሲዳማ አመራሮች ስድስት ቀናት የፈጀዉን ስብስባ ሲያጠናቅቁ የሲዳማ ህዝብ የክልል ጥያቄ አስፈላጊ ያልሆነና የህገወጦች እንደሆነ አስምረዉበታል፡፡ በተጨማሪም የሀዋሳ ከተማ አስተዳደርም በስብጥር እንዲሆን በሙሉ ድምጽ ተስማምተዋል፡፡ ሁለተኛዉ ጉዳይ አቶ ሽፈራዉና ተከታዮቻቸው የሲዳማን ህዝብ እድገትም ሆነ ክልል መሆን የማይቻል እንደሆነ ለማስመሰል የዉሸት መረጃዎቻቸዉን አደራጅተዉ በሁሉም ሀይላቸዉ እንቅስቃሴ መጀመራቸዉ ነዉ፡፡ ለዚህም ባለፈዉ ስብሰባቸዉ ሲዳማ ክልል ከሆነ አሁን ያለዉ የበጀት ድጎማ ይቀንሳል፡ ልማት አይኖርም፡ የስራ አጥነት ይጨምራል ወዘተ በሬ ወለደ መረጃ እያቀረቡ ነበር፡፡ አቶ ሽፈራዉንና ተከታቻቸዉን ግን እረፉ! እዉነት ነጻ ስለምታወጣችሁ እዉነትን ያዙ እንላቸዋለን! ሁሌም የሚቀርቧቸዉ መረጃዎቸ ዉሸት ስለመሆናቸዉ መላዉ የሲዳማ ህዝብ የሚያዉቀዉ ስለሆነ የዚህ ጽሁፍ ዋና አላማ የበጀት ክፍፍሉን ብቻ በሚመለከት አንዳንድ መረጃዎችን

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለተባበሩት መንግስታት እውቅና ያቀረበው ጥያቄ በቅርቡ ምላሽ ያገኛል

Image
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2005/ዋኢማ/  - የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በተባበሩት መንግስታት ያቀረበው የእውቀና ጥያቄ በመጪው ህዳር ወር ምላሽ ሊያገኝ እንደሚችል ኮሚሽኑ አስታወቀ። ኮሚሽነር አምባሳደር ጥሩነህ ዜና በተለይ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት፤ ኮሚሽኑ በመጪው ህዳር ወር ውሳኔ ከሚያገኙ ሀገራዊ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ዝርዝር ውስጥ ይገኛል።  ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ በ2000 ዓ.ም የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የአለም አቀፉ የብሔራዊ የሰብዓዊ መብት ተቋማት መረብ አባል ይሆናል።  የዓለም ዓቀፉ መረብ አባል መሆን የሚያስገኘውን ጠቀሜታ አስመልክተው ኮሚሽነሩ ሲናገሩ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽኑ እንደ የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን ሳይሆን እንደ ባለ ሙሉ መብት አባል በሀገሪቱ ውስጥ ስላለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማቅረብ  እድሉን ይከፍትለታል።  በተባበሩት መንግስታት መድረኮች ላይም ኮሚሽኑ መድረክ ተሰጥቶት አቋሙን ማንፀባረቅ እንዲችል ያደርጋል። ይህም የተቋሙን ተሰሚነት እንደሚያሳድገው ኮሚሽነሩ አክለው ገልፀዋል። ብሄራዊ የሰብዓዊ መብት ተቋማት የአባልነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት የሚያገኘው የፓሪስ መርሆዎች የሚያስቀምጠውን ትንሹን መስፈርት ማሟላት ከቻሉ ነው። በዚህም መሰረት የ’ኤ’ እና ‘ቢ’ ደረጃ ይሰጣቸዋል። የአባልነት ጥያቄ ከማቅረብ በፊት የኮሚሽኑን ተቋማዊ ደረጃ የማሻሻል ስራዎች እንደተሰሩ የገለፁት ኮሚሽነር ጥሩነህ፤ በአሁኑ ወቅትም ኮሚሽኑ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ተደራሽነት በማስፋት፣ አቅሙን በማሳደግና የምርምርና ሪፖርት ስራዎችን በማሳተም ረገድ ብዙ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። የዛሬ አምስት አመት ስራውን በአዲስ አበባ ብቻ የጀመረው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብ