Posts

ካላ ደሴ ዳልኬ እና አቶ በረከት ስምኦንን ጨምሮ የመንግሥት ባለሥልጣናት በማስትሬት ዲግሪ ተመረቁ

Image
•    አብዛኞቹ በምረቃው ዕለት አልተገኙም በብርሃኑ ፈቃደ ፕሮፌሰር ባደግ በቀለ በመሠረቱት ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ኢንስቲትዩት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በትናንትናው ዕለት ከተመረቁት መካከል፣ በሚኒስትር ማዕረግ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦንን ጨምሮ በርካታ ባለሥልጣናት በማስትሬት ዲግሪ ተመረቁ፡፡ የማስትሬት ዲግሪያቸውን በትራንስፎርሜሽናል ሊደርሺፕ ዘርፍ የሠሩት አቶ በረከት በምረቃው ሥነ ሥርዓት አልተገኙም፡፡ እንደ አቶ በረከት ሁሉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ አቶ ደሴ ዳልኬ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር አብርሃም ተከስተ መስቀልም ካልተገኙት መካከል ናቸው፡፡ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሞሐመድ ኡመር፣ በመከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ኰማንደር ብርሃኑ ጁላ ገላቻን ጨምሮ በርካታ የመንግሥት ሹማምንት ተመርቀዋል፡፡ አቶ በረከት ለመመረቂያ ያቀረቡት ጽሑፍ እያደጉ ባሉ ልማታዊ መንግሥታት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፣ ‹‹Emerging Developmental States: Transformational Leadership in Governemnt›› በሚል ርዕስ በጻፉት መመረቂያቸው ዲግሪያቸውን እንዳገኙ ከኢንስቲትዩቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡  http://www.ethiopianreporter.com/news/293-news/8093-2012-10-13-14-27-28.html

የሲዳማ ህዝብ ክልል የመሆን ጥያቄ በማይመለከታቸዉ ግለሰቦችና የዉሸት መረጃዎቻቸዉ አይቀለበስም

Image
ከማህበራዊ መረብ ላይ የተገኘ ጽሁፍ በ Giwoommo Gimbi  ተጻፈ !የሲዳማ ህዝብ ክልል የመሆን ጥያቄ በማይመለከታቸዉ ግለሰቦችና የዉሸት መረጃዎቻቸዉ አይቀለበስም በቅርቡ የተካሄደዉ የሲዳማ ዞን አመራሮች ስብሰባ መላዉ የሲዳማ ህዝብ አቋሙን ለይቶ ከምን ጊዜዉም በተለየ መልኩ ራስን በራስ የማስተዳደር ወይም ክልል የመሆን ጥያቄዉን አጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያደርገዉ ነዉ፡፡ ይህ ጉዳይ በሁለት መልኩ ሊታይ ይችላል፡፡  Requests አንደኛዉ ሟቹ ጠቅላይ ሚንስቴር በህይወት በነበሩበት ወቅት ለሲዳማ ህዝብ ቃል የገቡት የክልል ጥያቄ መልስ ሳያገኝ ቢያልፉም የተኳቸዉ ጠቀላይ ሚንስቴር አዎንታዊ ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ የተጠበቀዉ ከንቱ መሆኑ ነዉ፡፡ በአቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ የተመራዉ የሲዳማ አመራሮች ስድስት ቀናት የፈጀዉን ስብስባ ሲያጠናቅቁ የሲዳማ ህዝብ የክልል ጥያቄ አስፈላጊ ያልሆነና የህገወጦች እንደሆነ አስምረዉበታል፡፡ በተጨማሪም የሀዋሳ ከተማ አስተዳደርም በስብጥር እንዲሆን በሙሉ ድምጽ ተስማምተዋል፡፡ ሁለተኛዉ ጉዳይ አቶ ሽፈራዉና ተከታዮቻቸው የሲዳማን ህዝብ እድገትም ሆነ ክልል መሆን የማይቻል እንደሆነ ለማስመሰል የዉሸት መረጃዎቻቸዉን አደራጅተዉ በሁሉም ሀይላቸዉ እንቅስቃሴ መጀመራቸዉ ነዉ፡፡ ለዚህም ባለፈዉ ስብሰባቸዉ ሲዳማ ክልል ከሆነ አሁን ያለዉ የበጀት ድጎማ ይቀንሳል፡ ልማት አይኖርም፡ የስራ አጥነት ይጨምራል ወዘተ በሬ ወለደ መረጃ እያቀረቡ ነበር፡፡ አቶ ሽፈራዉንና ተከታቻቸዉን ግን እረፉ! እዉነት ነጻ ስለምታወጣችሁ እዉነትን ያዙ እንላቸዋለን! ሁሌም የሚቀርቧቸዉ መረጃዎቸ ዉሸት ስለመሆናቸዉ መላዉ የሲዳማ ህዝብ የሚያዉቀዉ ስለሆነ የዚህ ጽሁፍ ዋና አላማ የበጀት ክፍፍሉን ብቻ በሚመለከት አንዳንድ መረጃዎችን

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለተባበሩት መንግስታት እውቅና ያቀረበው ጥያቄ በቅርቡ ምላሽ ያገኛል

Image
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2005/ዋኢማ/  - የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በተባበሩት መንግስታት ያቀረበው የእውቀና ጥያቄ በመጪው ህዳር ወር ምላሽ ሊያገኝ እንደሚችል ኮሚሽኑ አስታወቀ። ኮሚሽነር አምባሳደር ጥሩነህ ዜና በተለይ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት፤ ኮሚሽኑ በመጪው ህዳር ወር ውሳኔ ከሚያገኙ ሀገራዊ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ዝርዝር ውስጥ ይገኛል።  ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ በ2000 ዓ.ም የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የአለም አቀፉ የብሔራዊ የሰብዓዊ መብት ተቋማት መረብ አባል ይሆናል።  የዓለም ዓቀፉ መረብ አባል መሆን የሚያስገኘውን ጠቀሜታ አስመልክተው ኮሚሽነሩ ሲናገሩ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽኑ እንደ የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን ሳይሆን እንደ ባለ ሙሉ መብት አባል በሀገሪቱ ውስጥ ስላለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማቅረብ  እድሉን ይከፍትለታል።  በተባበሩት መንግስታት መድረኮች ላይም ኮሚሽኑ መድረክ ተሰጥቶት አቋሙን ማንፀባረቅ እንዲችል ያደርጋል። ይህም የተቋሙን ተሰሚነት እንደሚያሳድገው ኮሚሽነሩ አክለው ገልፀዋል። ብሄራዊ የሰብዓዊ መብት ተቋማት የአባልነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት የሚያገኘው የፓሪስ መርሆዎች የሚያስቀምጠውን ትንሹን መስፈርት ማሟላት ከቻሉ ነው። በዚህም መሰረት የ’ኤ’ እና ‘ቢ’ ደረጃ ይሰጣቸዋል። የአባልነት ጥያቄ ከማቅረብ በፊት የኮሚሽኑን ተቋማዊ ደረጃ የማሻሻል ስራዎች እንደተሰሩ የገለፁት ኮሚሽነር ጥሩነህ፤ በአሁኑ ወቅትም ኮሚሽኑ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ተደራሽነት በማስፋት፣ አቅሙን በማሳደግና የምርምርና ሪፖርት ስራዎችን በማሳተም ረገድ ብዙ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። የዛሬ አምስት አመት ስራውን በአዲስ አበባ ብቻ የጀመረው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብ

ደኢህዴን ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት ያመራር ሚናውን ከምንግዜውም በላቀ ቁርጠኝነት ለመወጣት መዘጋጀቱን አስታወቀ

Image
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2005 (ዋኢማ) -  የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት ያመራር ሚናውን ከምንግዜውም በላቀ ቁርጠኝነት ለመወጣት መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴው የእድገትና የትራንስፎርሜሸን እቅዱን የሁለተኛ አመት አፈጻጸም ግምገማውን ለታላቁ መሪ አቶ መለስ ዜናዊ የህሊና ጸሎት በማድረግ ጀምሯል፡፡ የደኢህዴን ማዕካላዊ ኮሚቴ በመደበኛ ስብሰባው በታላቁ መሪ የተቀየሱት፣ መላውን ህዝብ ተሳታፊና ተጠቃሚ እያደረጉ የሚገኙት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን በላቀ ቁርጠኝነት በሚፈፀሙበት ሁኔታ ላይ በዝርዝር ተወያይቷል፡፡  በዚህም የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ህልፈት ተከትሎ ህዝቡ ከጫፍ ጫፍ ያሳየውን ቁጭት በተደራጀ መንገድ ለመምራት፣ በየደረጃው የሚገኙ ድርጅታዊ፣ መንግስታዊና ህዝባዊ መዋቅሮችን ተቋማዊ በማድረግ የህዳሴውን ጉዞ ለማፋጠን የሚያስችሉ የአፈጻጻም ስልቶችን በመቀየስ ተግባራዊ እንዲሆኑ ወስኗል፡፡ በገጠር ስራዎች በተለይም በአካባቢ ልማት አና ጥበቃ የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡን የገመገመው ማዕከላዊ ኮሚቴው በበልግ እና በመኸር የግል ማሳ ስራዎች ረገድም በአንዳንድ አካባቢዎች መልካም ውጤት መመዘግቡን አረጋግጧል፡፡ ምርታማነትን ለማሳደግ የቴክኖሎጂ ግብአቶችን በመጠቀም ረገድ የነበሩ ክፍተቶችንም ለይቷል፡፡ ኢሬቴድ እንደዘገበው ማዕከላዊ ኮሚቴው በከተሞች፣ በቤቶች ልማትና በመሰረተ ልማት የተሻሉ ተግባራት ቢከናወኑም በመልካም አስተዳደር ረገድ የሚስተዋሉ ጉደለቶችን ማረም እንደሚገባ ነው ያስገነዘበው፡፡ መስከረም 30/2005 የተጀመረው የማዕከላዊ ኮሚቴው መደበኛ ስብሰባ በ2005 በሁሉም መስኮች የነበሩ ጥንካሬዎችንና ጉድለቶችን በጥልቀት በመገምገም የ2005 እ

ህገ-መንግስቱ ያገሪቱ የበላይ ህግ ነው የተባለው ድንጋጌ ይከበር!!

Image
Sidama times የዜና መጽሔት የተገኘ ህገ - መንግስቱ ያገሪቱ የበላይ ህግ ነው የተባለው ድንጋጌ ይከበር !! ውድ አንባቢዮቻችን እንደ ምን ሰነበታችሁ ? በባለፈው ፁሑፋችን የሲዳማ ህዝብ ክልል የመሆን ጥያቄ በህገ - መንግስቱ እይታ ሲፈተሸ ምን ገፅታ እንዳለው ባጭሩ ለማስቃኘት መመኮራችን ይታወሳል፡፡ በዛሬው አጭር ፁሑፋችን የሲዳማ ህዝብ ክልል ባለማግኘቱ የተጎዳባችሁን ሁኔታዎች እንቃኛለን፡፡ መልካም መቆይታ በቀደመው ፁሑፋችን ለማንሳት እንደሞከርነው የሲዳማ ህዝብ ክልል የመሆን ጥያቄ በቅርብ ጊዜ የተጀመረ እንዳልሆነና ለዘመናት ይህንን ጥያቄ ህዝባች ሲያነሳ የቆየ፡ ነገር ግን ህጋዊ ምላሽ ተነፍጎን እንደኖረ አይተናል፡፡ አንባገነኑ የደርግ ስርዓት እንዲዳከምና በኃላም እንዲንኮታኮት ከፍተኛ የሆነ የትጥቅ ትግል በማድረግ ለሀገሪቱ ነፃነትና ለዲሞክራሲ ማደግ ከፍተኛ ሚና የተጫወት ህዝብ ነው የሲዳማ ህዝብ፡፡ የሀገሪቱ የፖለለቲካ ምህዳር ሲቀየርና የፌደራሊዝም ስርዓት እንደብቸኛ አማራጫ ተደርጎ ሲወሰድ የሀገራችን ለየት ብሎ የጎሳ ፌደራላዊ ስርዓት ሆኖ ተዋቅሯል፡፡ ይህ የፌደራል ስርዓት ለአብዛኞዎቹ ብ / ብ / ሕ በወቅቱ አንግቦት ለነበረው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ታስቦ የተወሰደ እርምጃ ይመስላል፡፡ ይህ በጎሳ የመከፋፈል እርምጃ ከሀገሪቷ አንድነት እይታ ትክክለኛ ነው አይደለም የሚለውን አሁን አንመለከተውም፡፡ የብ / ብ / ሕ ጥያቄው ምላሽ ማግኘት አለበት ሲባልም የተለያየ እንድምታ ያለው ይሆናል፡፡ ግማሾቱ የመገንጠል ጥያቄ፣ ግማሾቹ እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ፣ ለሎቹ ደግሞ ለፖለቲካ መንበረ ስልጣን ወዘተ ጥያቄዎችን አንግበው የሚንቀሳቀሱ ነበሩ፡፡ የሲዳማም ህዝብም ያለውን የቆየ የትግል ታሪክና እምቅ አቅሙን