Posts

በቅርቡ ከእስር የተፈቱት ታዋቂው የሲዳማ መብት ተከራካሪ ካላ ዱካሌ ላሚሶ ፍርድቤት እንድቀርቡ ቀጠሮ ተሰጣቸው፤ ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ውስጥ ኣስራ ሁለት የሹመት መደቦች ሲዳማ ባልሆኑ ግለሰቦች እንዲያዙ ተደረጉ

Image
የሲዳማ መብት ተከራካሪ ካላ ዱካሌ ላሚሶ ከሲዳማ የፊቼ በኣልን ተከትሎ በክልሉ መንግስት መሪነት ከታሰሩት በርካታ የሲዳማ ተወላጆች መካከል የሆኑት እና ከቅርብ ቀናት በፊት የእስር ቤት የተፈቱት ካላ ዱካሌ ሰሞኑን ወደ ፍርድቤት እንድቀርቡ የቀጠሮ ወረቀት ተሰጥቷቸዋል። ስማቸው እንድገለጽ ያልፈለጉ የውስጥ ኣዋቂ ምንጮች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደተናሩት ካለ ዱካሌ ላሚሶ የዩኒቨሪሲቲ ተማሪዎችን በመንግስት ላይ በማነሳሳት፤ ጸረ ኢህኣዴግ / ደኢህዴን ጽሁፎችን በመጻፍ እና በመሳሰሉት ክስ እንደተመረሰረተባቸዋል። እንደእነዚሁ የውስጥ ኣዋቂ ምንጮች ገለጻ ከሆነ፤ የደቡብ ክልል ፕሬዚዴንት ካላ ሽፈራው ሽጉጤ የሲዳማን የክልል ጥያቄ ለመጨፍለቅ በምያደርጉት ጥረት በርካታ የሲዳማ ምሁራንን በማሰር ብሎም በማስፈራራት እያሸማቀቁ የቆዩ ሲሆን፤ ሰሞኑን ከፌደራል እስከ ወረዳ ያሉት የሲዳማ ኣመራሮችን በማሰባሰብ ደኢህዴን ለኣመታት ያልም የነበረውን የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር ከሲዳማ ተወላጆች እጅ የመንጠቅ ህልማቸውን ኣሳክቷል። የሲዳማ ኣመራሮች ያሳለፉትን ውሳኔ ተከትሎ ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ውስጥ ኣስራ ሁለት የሹመት መደቦች ሲዳማ ባልሆኑ ግለሰቦች እንዲያዙ ተደርገዋል። የሲዳማን የክልል ጥያቄ የምደግፉት ሆነ የሃዋሳን ከተማ ከሲዳማ እጅ መውጣቱን የምቃወሙትን የሲዳማ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው የቃላት ዛቻ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፤ ካላ ዱካሌ ፍርድቤት እንድቀርቡ ልደረጉ ያሉት ውስጥ ውስጡን በመቀጣጠል ላይ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመቀልበስ ታስቦ መሆኑን እነዚሁ ውስጥ ኣዋቂ ምንጮች ኣብራርተዋል።

የሀዋሣ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የማስፈፀም አቅሙን ከፍ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጡ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡

Image
የሀዋሣ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የማስፈፀም አቅሙን ከፍ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጡ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡ በ2ዐዐ4 በጀት አመት በከተማ አስተዳደሩ የተሻለ አፈፃፀም ካስመዘገቡ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የሀዋሣ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የአገልግሎት አሰጣጡን ተደራሽ ለማድረግና የተሻሻሉ አሰራሮች ተግባራዊ እንዲሆኑ እስከታችኛው የመስሪያ ቤቱ መዋቅር ድረስ ሂስና ግለሂስ አድርጓል፡፡ በግምገማው ወቅት እንደተጠቆመው ማዘጋጃ ቤት በባህሪው አገልግሎት ሰጪ ተቋም አንደመሆኑ መጠን በሰራተኛው የአመለካከት ችግርና የክህሎት ክፍተት ምክንያት ሙሉ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት አልተቻለም፡፡ እንደ አቶ ዮናስ ዮሴፍ የሀዋሣ ከተማ ከንቲባ ገለፃ ከከተማ ልማት ስራዎቻችን መካከል ተጠቃሹ የከተማ ነዋሪውን የአገልግሎት ፍላጎቶች ተደራሽ ማድረግ ሲሆን ለዚህም የሲቪል ሰርቫንቱን የአፈፃፀም አቅምና አመለካከቱ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ነው ብለዋል፡፡ አቶ ብሩ ወልዴ የሀዋሣ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች ዋና ሥራ አስኪያጅ በበኩላቸው ምንም እንኳን ባለፈው በጀት አመት ማዘጋጃ ቤቱ በተለያዩ የሀገርና ክልል አቀፍ መድረኮች ተሸላሚ ያደረጉትን ስራዎች እንደሰራ ቢታወቅም ይህ ማለት ግን የአገልግሎት አሰጣጡ ሙሉ ነው ማለት አይደለም፡፡ ስለሆነም ያለብንን የአሰራር ክፍተቶች እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በመገምገም የተሸለ አፈፃፀም እንዲኖረን ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ ማዘጋጃ ቤቱ ከዚህ ጐን ለጎን በ2ዐዐ4 በጀት አመት በአገልግሎት አሰጣጣቸው፣ በመረጃ አያያዛቸውና ከዋናው ማዘጋጃ ቤት ጋር ባላቸው የአሰራር ግልፀኝነት በከተማዋ ከሚገኙ 8 ክፍለ ከተሞች የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማን አንደኛ የመናኸሪያ ክፍለ ከተማን ሁለተኛ እንዲሁም የታቦር ክፍለ ከተማን

የፌደራል የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ በሀዋሣ ከተማ ለሚገኙ የጡረተኞች ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡

ኤጀንሲው ድጋፉን ያደረገው ከሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትርና ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በመተባበር መሆኑም ታውቋል፡፡ በኤጀንሲው የሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ራሄል ዘውዴ እንዳሉት የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ህፃናት የነገ ሀገር ተረካቢ መሆናቸውን በውል በመረዳት ከልዩ ልዩ አካላት ስፖርንሰር በማፈላለግ ልዩ ልዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ድጋፍ የተደረገላቸው 169 በሞግዚት የሚተዳደሩ ህፃናት መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡ ለህፃናቱ የዚህን አይነት ድጋፍ ማድረግ ትምህርታቸውን በሚገባ እንዲከታተሉ አስተዋፅኦው የጐላ መሆኑም ተናግረዋል ሲል የዘገባው በኃይሉ ጌታቸው ነው፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/30MesTextN805.html

በፍርድ ቤቶች የሚሰጡ ውሳኔዎች የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶችን ስምምነት ያገናዘቡ ሊሆን እንደሚገባ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሀዋማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አመለከተ፡

ጽህፈት ቤቱ አሥር ዋና ዋና አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነት ያካተተ  4ዐዐጥራዝ ለክለሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስረክቧል፡፡ ኢትዮጵያ ፊርማ ያፀደቀቻቸውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነት በሀገራዊ ቋንቋዎች መተርጐም ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በማቋቋሚያ አዋጅ ከተሰጡት ስልጠንና ተግባራት መካከል አንዱ ነው፡፡ ሰነዶቹ ለትምህርት ቤቶችና ለፍርድ ቤቶች እንዲሁም ለህግ ባለሙያዎች እንዲያገለግሉ ለማድረግ ኮሚሽኑ በአገራዊ ቋንቋዎች የመተርጐምና የማሰራጨት ሥራውን በቀዳሚነት እየሠራ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሀዋሣ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የመምርመራ፣ ጥበቃና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አታሮ እንደገለፁት የአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ሰነዶች በአገራዊ ቋንቋ አለመተርጐምና በስፋት አለመሰራጨት ለሰነዶቹ አለመፈፀም ትልቅ ተግዳሮት ሆኖ ቆይቷል፡፡ ኮሚሽኑ ችግሩን ለመቅረፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት ሁሉን አቀፍ የሰብአዊ መብት መግለጫ፣ የህፃናት  እና የአካል ጉዳተኞችን መብቶችና ደህነንት ስምምነት ጨምሮ የተተረጐሙ አሥር ዋና ዋና አለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነት ሰነዶችን በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ፍርድ ቤቶች አገልግሎት እንዲሰጡ 4ዐዐ ጥራዞችን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስረክበቧለ፡፡ ስምምነቱን በማሳወቅና በሥራ ላይ እንዲውሉ በማድረግ በኩል የፍትህ አካላት የላቀ ሚና መጫወት እንደሚጠበቅባቸው አቶ ብርሃኑ አስገዝንበዋል፡፡ ሰነዶቹን የተረከቡት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዝዳንት ተወካይ አቶ ሲሳይ ገመቹ በበኩላቸው የአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ስምምነቶችና ድንጋጌዎች ተተርጐመው መሠራጨታቸው ዜጐች መብቶቻቸውን በአግባቡ የሚያውቁበትን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ገለፀዋል፡፡ የሰነደቹ ሥርጭት መስፋፋት በተይም በፍርድ ቤቶች

የሲዳማ ዞን ከተማ ልማት መምሪያ በተያዘው የበጀት ዓመት በተለያዩ ከተሞች ከ8ዐ ኪሎ ሜትር በላይ አዲስ የጠጠር መንገድ ግንባታ ከ14 ኪሎ ሜትር በላይ ደግሞ የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ ሥራ ለማከናወን ማቀዱን አስታወቀ፡፡

በሁሉም ማዘጋጃ ቤቶች አማካይነት 9ዐ ኪሎ ሜትር አዲስ የመንግድ ከፈታና ጠረጋ እንዲሁም 92 ኪሎ ሜትር የመንገድ መብራት 74 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ የውሃ መስመር ዝርጋታ ከሚከናወኑ ተግባራት ተጠቃሽ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡ መምሪያው በዞኑ ከሚገኙ 42 ማዘጋጃ ቤቶች ሥራ አስኪያጆችና የስራ ሂደት አስተባባሪዎች ጋር በ2ዐዐ4 በጀት አፈፃፀምና በ2ዐዐ5 እቅድ ዙሪያ በተወያየበት ወቅት የመምሪያው ኃላፊ አቶ ለገሠ ማሬሮ እንዳሉት በተያዘው የበጀት ዓመት ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ የሚያደርጉ፣ ለወጣቱ ደግሞ የሥራ እድል የሚያስገኙ ሥራዎች በተጠናከረ መልኩ ይከናወናሉ፡፡ በዚህም መሠረት 9ዐ ወጪ ቆጣቢ እና ተጀምረው ያልተጠናቀቁ 33ዐ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እንዲሁም በ482 ነባር የመንግስት ቤቶች ላይ የጥገና ሥራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል፡፡ ውይይቱን በንግግር የከፈቱት በዞኑ ዴህኢህዴን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የከተማ ዘርፍ ኃላፊ አቶ በየነ በራስ በበኩላቸው ማዘጋጃ ቤቶች ለኢንድስትሪ መስፋፋት መሠረት በመሆናቸው ለከተሞች እድገት ዋንኛ እንቅፋት የሆነውን የኪራይ ሰብሳቢነት ሰንሰለትን መበጣጠስ አለብን ብለዋል፡፡ የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ዘግቧል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/30MesTextN1005.html