Posts

በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ የኑራ ቆራቴ አገልግሎት ህብረት ሥራ ማህበር በ7 ቀበሌያት ለሚገኙ 11 አንደኛ ደረጃ 1ኛና 2ኛ...፡፡

በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ የኑራ ቆራቴ አገልግሎት ህብረት ሥራ ማህበር በ7 ቀበሌያት ለሚገኙ 11 አንደኛ ደረጃ  1ኛና 2ኛ ሳይክል ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ከ1ዐዐ ሺህ ብር በላይ ወጪ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ የትምህርት ቁሳቁስ ተገዝቶ የተሰጣቸው ወላጆቻቻው የማህበሩ አባላት ለሆኑ ተማሪዎች ነው ተብሏል፡፡ የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ማቴዎስ ዲጋሳ በዚህን ወቅት እንዳሉት ተገዝቶ በተበረከተው የትምሀርት ቁሳቁስ 4 ሺህ 554 ተማሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች ለሚማሩ በርካታ ተማሪዎች የትራንስፖርትና የትምህርት ወጪ መሸፈኑንም ገልፀዋል፡፡ የወረዳው ግበይትና ህብረት ስራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘማች እርጥባ በበኩላቸው ማህበሩ እያደረገ የሚገኘው በጎ ተግባር አርሶ አደሩ የማህበሩ አባል በመሆኑ ብቻ ከራሱ አልፎ ቤተሰቡም ጭምር ተጠቃሚ መሆኑን ማረጋገጫ እንደሚሆን አመልክተዋል፡፡ ሌሎች ማህበራትም ይህን አርያ እንዲከተሉ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳይ ጽህፈት ቤት ዘግቧል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/26MesTextN205.html

በሲዳማ ዞን በአዲሱ በጀት ዓመት 3 መቶ ሚሊዮን የሚጠጋ ገቢ የመሰብሰብ እቅዱን ለማሳካት እየሠራ እንደሚገኝ የዞኑ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ጽህፈት ቤቱ ከ2 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የንግዱ ማህበረሰብ ክፍሎችና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት በገቢ ግብር አዋጆች፣ ደንቦች እንዲሁም መመሪያዎችና በሂሳብ አያያዝ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰሞኑን ሰጥቷል፡፡ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ተሻለ ቡላዶ እንደገለፁት ሥልጠናው ቀደም ሲል በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ ይታዩ የነበሩ የግንዛቤ ክፍተቶችን ለመቅረፍና በዘንድሮው የበጀት ዓመት ከአምናው የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ የበለጠ አቅም ለመፍጠር የሚያስችል ነው፡፡ በተጨማሪ እሴትና ተርን ኦቨር ታክስ እንደዚሁም በገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ላይ የሚስተዋሉ የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሥልጠናው ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡ በመንግስት ታትመው የሚሰራጩ ደረሰኞችን ወደ ጎን በመተው ህገ ወጥ ደረሰኞችን የሚጠቀሙ አንዳንድ ነጋዴዎች መኖራቸው እንደተደረሰባቸው የጠቆሙት ኃላፊው እንዲህ አይነት ድርጊት እስከ አስራ አምስት ዓመት በሚደርስ እስራት እንደሚያስቀጣም አስታውቀዋል፡፡ በጽህፈት ቤቱ የገቢ ጥናት ትምህርትና ሥልጠና ዋና ሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ደሳለኝ ጋንጌ በበኩላቸው የንግዱ ማህበረሰብ ግብሩን በወቅቱ በመክፈል የዜግነት ግዴታውን መወጣት እንዳለበት አሳስበው ለዚህም የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መስጠት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ ዘገባው የሲዳማ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነው፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/26MesTextN305.html

የሀዋሣ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በ13 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ወጪ በከተማው ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ክፍት የሆኑ የጐርፍ መውረጃ ቦዮችን በኘሪካስት ለመሸፈን የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡

Image
የሀዋሣ ከተማ ማዘጋጃ ቤት  በ13 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ወጪ  በከተማው ውስጥ  በተለያዩ አካባቢዎች ክፍት የሆኑ የጐርፍ መውረጃ ቦዮችን በኘሪካስት ለመሸፈን የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡ ለማህበራት ፣ ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንት እንዲሁም ለተለያዩ ተቋማት  ግንባታ ለጨረታ የሚቀርብ ከ4ዐዐ ሄክታር በላይ መሬት መዘጋጀቱንም አመልክቷል፡፡ ማዘጋጃ ቤቱ በ2ዐዐ4 አፈፃፀምና በ2ዐዐ5 የሥራ እቅድ ላይ የጋራ ውይይት አካሂዷል፡፡ የሀዋሣ ከተማ ውብ እና ፅዱ ሆና ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንት እንዲሁም የቱሪስት መዳረሻነቷን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የከተማው አስተዳደር የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በተለይም በማዘጋጃ ቤቱ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተጀመረው መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ማጠናከር አንዱ ነው፡፡ ማዘጋጃ ቤቱ በ2ዐዐ4 የሥራ ዘመን በከተማ ኘላን ዝግጅት፣ በመሬት አስተዳደር፣ በየክፍለ ከተማው የተገኙትን ሠነድ አልባ ፋይሎችን በካዲስተር በማደራጀት ፣ በመሠረተ ልማት  አቅርቦት እንዲሁም በፅዳትና ውበት፣ መናፈሻ አገልግሎት በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፡፡ የከተማው ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ብሩ ወልዴ እንደገለፁት በከተማው ከ2 ዓመት በላይ ሳይለሙ የቆዩ 7 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት በከተማው አስተዳደር ውሳኔ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ ተወስኖል፡፡ ከ27 ኪሎ ሜትር በላይ አዲስ የጐርፍ መውረጃ ቦይ ቁፋሮ ስራና  19 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር ነባር ቦይ መገንባቱንም አመልክተዋል፡፡ በከተማው ውበት ፣ ልማትና መናፈሻ አገልግሎት ዘመቻ ከ48 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ በድንጋይ ንጣፍ ሥራ በተለያዩ ዘርፎች ለተሰማሩ ከ5 ሺህ 2ዐዐ በላይ ዜጐች የሥራ እድል ተፈጥሮል፡፡ በቀበሌና ቁጠባ ቤቶች እ

በሲዳማ ዞን በይርጋለም ከተማ የኤች አይ ቪ ኤድስን ስርጭት ለመግታት በህብረተሰቡ በየጊዜው በተሠጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት የአመለካከት ለውጥ ማሳየቱ ተገለፀ፡፡

በይርጋለም ከተማ ቤዛ የወጣቶች ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ ሞላልኝ ሀያሉ ማዕከሉ በዋናነት ትኩረት አድርጎ የሚሠሩት በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ዙሪያ በኤች አይ ቪ ኤድስ እንዲሁም ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ነፍሰጡር እናቶችና ህፃናት ላይ መሆኑን ጠቅሰው ወጣቶች ለኤድስ ተጋላጭ የሚሆኑት ምቹ የመዋያ አካባቢ ባለመኖሩ ነው ብለዋል፡፡ በቤዛ የወጣቶች ማዕከል ቫይረሱ በደማቸው የሚገኙ ህፃናትና ነፍሰጡር እናቶች አስተባባሪ ወዘሪት ልሳነወርቅ ተስፋዬ በበኩላቸው ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ወገኖች ቁጥር በአሁኑ ጊዜ 32 መድረሱን ገልፀው ሁሉም የማህበሩ አባላት እንደየአቅማቸው በመቆጠብ የኢኮኖሚ አቅማቸውን እያሳደጉ እንደሚገኙ አስታውቃለች፡፡ በቤዛ ወጣቶች ማዕከል የቡና ጠጡ ኘሮግራም አዘጋጅና አሳታፊ ወይዘሮ ጥሩነሽ ፀጋዬ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ያለባቸው ወገኖችን ማቅረብና የመድሀኒት አጠቃቀማቸውን መከታተል ተገቢ  መሆኑን ገልፀው በማህበር ያልተደራጁ ወደ ማህበሩ መጥተው ተገቢውን ድጋፍና እርዳታ እንዲያገኙ አስገንዝበዋል፡፡ አዳነ አለማየሁ ከበንሳ ቅርንጫፍ ጣቢያ እንደዘገበው፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/25MesTextN605.html

ባለፉት ሁለት ዓመታት የአምስት ዓመቱ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም ስኬታማ ነበር-ፕሬዚዳንት ግርማ

Image
አዲስ አበባ መስከረም 28/ 2005 ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የአምስት ዓመቱ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ያለፉት ሁለት ዓመታት ዕቅድ አፈጻጸም ስኬታማ እንደነበር ገለጹ። አራተኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽ ምክር ቤቶች 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ ስብሰባ የተከፈተው በቅርቡ ከዚህ ዓለም በድንገት በሞት ለተለዩት ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የህሊና ፀሎት በማድረግ ነበር። ለሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ግርማ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ተግባራዊ መሆን ከመጀመረ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ አገሪቱ ከ11 በመቶ በላይ ፈጣን ዕድገት ተመዝግቧል። ኢትዮጵያ ለ9ኛ ጊዜ ባለሁለት አሃዝ እድገት በማስመዝገብ ፈጣኑን እድገት ለማስቀጠል መቻሏንም ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ እንዳሉት ልክ እንደ ኢኮኖሚው ሁሉ በዴሞክራሲና ማህበራዊ ልማትን ከማስፈን አኳያ ከፍተኛ መሻሻልና እድገት ተመዝግቧል። ባለፈው ዓመት የማዳበሪያና ምርጥ ዘር ተጠቃሚዎች ቁጥር ከፍ እንዲል በመደረጉና አርሶ አደሩ ዘመናዊ የግብርና ዘዴዎችን በተሻለ ደረጃ በመጠቀሙ የተሻለ ምርት እንደሚጠበቅም ጠቅሰዋል። በ2004 በጀት ዓመት በተለያዩ የስራ ፈጠራ ስልቶች በመታገዝ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዚያዊ የስራ እድሎች መፈጠራቸውንም ለምክር ቤቱ ገልጸዋል። በከተሞች የቤቶች ልማትን አጠናከሮ ለማስቀጠል ጥረት መደረጉን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ 100 ሺህ መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች ቤቶችን የመገንባት እንቅስቃሴ በመካሄድ ላይ መሆኑን አመልክተዋል። በፌዴራልና በክልሎች የተጀመሩ የቤቶች ግንባታን በጥራት ለማጠናቀቅ ጥረት እንደሚደረግም አስረድተዋል። ፕሬዚዳንት ግርማ የታላቁ