በብአዴን እና በህወሃት ያገረሸው የውስጥ ሽኩቻ የሃይል አሰላለፍ
በገዢው ሰፈር ጎራ ለይቶ ከተለኮሰው የቡድን ፖለቲካዊ ፍጥጫ እና ሴራ ጀርባ አገር እና ህዝብን የሚጎዳ አደገኛ ተግባር በግልጽ እና በስውርእየተካሄደ እንዳለ ከተለያዩ የፓርቲው ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ። በተለይ በብአዴን እና በህወሃት ቱባ አመራሮች መካከል ስር ሰዶ የቆየው እና የአቶ መለስን ህልፈት ተከትሎ ያገረሸው የውስጥ ሽኩቻ ሁለት ቡድኖች የሃይል አሰላለፋቸውን ለማጠናከር «ይረዱናል » የሚሏቸውን የሌሎች ፓርቲ ሹማምንት እና የመከላከያ የጦር አዛዦች ከጎን የማሰለፉን ተግባር ቀጥለውበታል።ለግንዛቤ እንዲረዳ የሃይል አሰላለፉን በጥቂቱ በመዳሰስ ወደ ዋናው ነጥብ እናምራ። ከበረከት እና ዓዜብ ጎን በመሰለፍ ቀዳሚ የሆኑት አቶ ተፈራ ዋልዋ እና አዲሱ ለገሰ ናቸው።አቶ አዲሱ በይፋ ከሚታወቀው የአየር መንገድ የቦርድ ሃላፊነታቸው ባሻገር ኮተቤ መስመር በሚገኘው እና «የአቢዮታዊ ዲሞክራሲ ማኔጅመንት ት/ቤት »ተብሎ በተከፈተው ተቋም ዋና ሃላፊ እና ለባለስልጣናት እንዲሁም ካድሬዎች መምህር ጭምር ናቸው። ከመለስ መታመም ወዲህ የህወሃት ካድሬ ላልሆኑ በአቶ አዲሱ እየተሰጠ ያለው ፖለቲካዊ ትምህርት ሳይሆን የበረከትን አቋም የሚያቀነቅን እና ህወሃትን የሚያጥላላ ቅስቀሳ ሆኖአል። በሌላ በኩል ዓዜብ ከጎኗ ማሰለፍ የቻለችው ጄነራል ሰአረ መኮንን እና እንዲሁም በእርሳቸው የሚመራውን ጦር ነው ።በተጨማሪም ቴዎድሮስ ሃጎስ ይገኛሉ ።የዓዜብ አስገራሚ “አቋም” በሶፊያን አህመድም ላይ ተንጸባርቋል።”ለኤርትራ ካሳ “በሚል 2.1 ቢሊዮን ብር ለሻብያ በሚስጥር እንዲሰጥ በፊርማቸው ጭምር ከወሰኑት መካከል አቶ መለስ ዜናዊ፣ሙሉጌታ አለም ሰገድ ፣ሟቹ አቃቤ ህግ መስፍን እና ሶፊያን አህመድ ይገኙበታል።ዓዜብ ከዚህ በመነሳት “መለስን የማይክዱ ታማኝ “ካለቻ