ሲዳማን ማነው የወከለው?
ስሞኑን ከፌደራል እስከ ወረዳ ደረጃ የምገኙ የሲዳማ ኣመራር ኣባላት በሃዋሳ ከተማ በሲዳማ የወደፊት እጣ ፋንታ ላይ መክረው ባለ ዘጠኝ ነጥብ የኣቋም መግለጫ በማውጣት ኣጠናቀዋል። ኣንዳንዶች እንደምሉት ከሆነ የሲዳማ ኣመራሮች ዳግመኛ በሃዋሳ ከተማ ላለመሰባሰብ የወሰኑ ይመስላል፤ ምክንያቱም የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር በሌሎች በሳል በምባሉ ብሄሮች እንድተዳደርላቸው ተሰማምተዋል እና ሃዋሳ ከእንግድህ የሲዳማ ኣስተዳደር ኣካል ባለመሆኑ በሃዋሳ ከተማ በሲዳማ ስም የመሰባሰብ እድል የላቸውም ይህንን እንኳን ኣርቆ ማየት ብሳናቸውም። ወደ ቁምነገሩ ስንመለስ የሲዳማ ህዝብ ኢህኣደግ ይጠቅመኛል በመልካምኣስተዳደር በኩል ያለብኝን ችግር ይፈታልኛል በማለት በተደጋጋሚ በችግሩ ጊዜ ፈጥኖ በመድረስ ሲመርጠው ብቆይም፤ ደኢህዴን / ኢህኣዴግ የሲዳማን ህዝብ ሲያሳዝን የሰሞኑ ክስተት የመጀመሪያው ኣይደለም። የዛሬ ኣስር ኣመት ደምኣፍሳሹ የደኢህዴን መንግስት የጸጥታ ኃይሎቹን ኣሰማርቶ በንጽሃን የሲዳማ ተወላጆችን ላይ በጠራራ ጸህይ የጥይት መዓት ኣውርዶ በርካታዎቹን በመግደል ሌሎቹን ኣቁስለዋል ፤ በድርግቱም የሲዳማ ህዝብ ክፉኛ ኣዝኗል፤ ሆኖም ከስህተቱ ይማራል ዳግመኛ መሰል ተግባር ኣይደግምም በማለት በባለፈው ምርጫ በነቅስ ወጥቶ እንደመረጠው ይታወሳል። ሰሞኑን ደግሞ ከባለፈው ስህተቱ ያልተማረው ደኢህዴን የሲዳማ ህዝብ ላሳየው ክብር እና ፍቅር የፓርቲው ኣመራሮች የሰጡት ምላሻ ራስን በራስ የማስተዳደር መብቱን በመንጠቅ የራሱን ከተማ በተቀጣሪዎች እንዲያስተዳድር ማድረግ ሆኗል። የምገርመው ደግሞ የሲዳማ የክልል ጥያቄን የሚያነሱ ኣካላት የሲዳማን ህዝብ የማወክሉ ናቸው ብለዋል። ለሲዳማ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ መብት መከበር ሲሉ በደኢህዴን እስር ቤቶች የሚማቅቁት ብሎም ተሰደው