Posts

ሁለቱ የሲዳማ ዌይብ ሳይቶች እድሳት ተደርጎላቸው በቅርብ ቀን ኣገልግሎት መስጠት እንደምጀምሩ ተገለጸ

ለሲዳማ ዲያስፖራ ብሎም ሲዳማ ምድር ለሚገኑ የሲዳማ ተወላጆች የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ፤ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ መረጃዎችን በማቀበል የሚታወቁት የሲዳማ ዶት ኦርግ እና ሲዳማኔሽናል ሲላሽ ሊብሬሽን ዶት ኦርግ የተባሉ ዌይብ ሳይቶች ( www.sidama.org and www.sidamanational-liberation.org ) በዚህ ሳምንት ኣገልግሎት የማይስጡ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ውስጥ እድሳት ተደርጎላቸው በኣዲስ መልክ ኣገልግሎት መስጠት እንደምጀምሩ የዌይብ ሳትቶቹ ኣዘጋጆች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ በላኩት መልዕክት ኣስታውቀዋል።

OSU hosts Hawassa University

Image
The Division of International Studies and Outreach recently hosted officials from Hawassa University in Ethiopia who are visiting Oklahoma State University. Read more: http://sois.okstate.edu/newsevents.aspx

የሐዋሳ-ሀገረማሪያም የአስፋልት መንገድ ግንባታን ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው

Image
አዲስ አበባ፣መስከረም 21/2005/ዋኢማ /-የአራተኛው የመንገድ ዘርፍ ልማት ፕሮግራም አካል የሆነውና የ198 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን የሐዋሳ-ሀገረማሪያም የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታን ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ። ግንባታው ወደ ሦስት ቢሊየን ብር ይፈጃል ተብሎ የሚጠበቀው ይኸው የመንገድ ፕሮጄክት የትራንስ አፍሪካን ሃይዌይ መንገድ አካልና የኬንያን ሞምባሳ ወደብ ከአዲስ አበባ ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ ነው። የመንገዱ መገንባት በኢትዮጵያና ኬንያ መካከል ያለውን የንግድና የትራንስፖርት ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ ተናግረዋል። ለዚህ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ማስፈጸሚያ የሚውለውን ወጭ የሚሸፍነው የአፍሪካ ልማት ባንክ መሆኑን አቶ ሳምሶን ተናግረዋል። http://www.waltainfo.com/index.php?option=com_content&view=article&id=5457:2012-10-01-13-54-37&catid=58:2011-08-29-12-55-21&Itemid=383

መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት የሚያደርጉት ጥረት የሚበረታታ እንደሆነ ተገለፀ፡፡

ታቦር የህፃናት ወጣቶች ልማት ድርጅት በሀዋሣ ከተማ በመናኸሪያ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ቀበሌ ለሚገኙ 35 ህፃናት የትምህርት ቁሳቁስ በእርዳታ ሰጥቷል፡፡ በሥነ ሥርዓቱ ላይ በሀዋሣ ከተማ ጤና መምሪያ የኤች አይ ቪ ኤድስ ሚኒስትርሚኒግ ኦፊሠር አቶ መንግስቴ መኮንን እንዳሉት ድርጅቱ አቅመ ደካማ የሆኑ ህፃናትን በትምህርት በማገዝ ያደረገው ጥረት የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ውብሸት ተሠማ በበኩላቸው ድርጅቱ በህፃናት በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ሳቢያ ከትምህርታቸው እንዳይስተጓጐሉ የሚያደርጉትን ጥረት በቀጣይም በሌሎችም ተግባራትም አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ የፒያሳ ቀበሌ ዋና ሥራ አሰኪያጅ አቶ መካሻ ሳሙኤል እንዳሉት ድርጅቱ በወላጆቻቸው ችግር ሳቢያ ትምህርታቸውን መማር ላልቻሉ ህፃናት ያደረገው ተግባር በአርአያነት የሚጠቀስ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የህፃናቱ ወላጆች በተደረገላቸው የትምህርት ቁሳቁስ  ድጋፍ መደሰታቸውን ባልደረባችን ታሪኩ ለገሰ ዘግቧል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/16MesTextN105.html

“መልካም አስተዳደርን ያላካተተ ልማት ልማት አይባልም”

በምሕረት ሞገስ ኢትዮጵያ በልማቱ ዘርፍ የኢኮኖሚ ዕድገት ታስመዝግብ እንጂ ዴሞክራሲን በማስፈን ወደኋላ እንደቀረች የተለያዩ የሰብአዊ መብትተሟጋች ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡ ኢሕአዴግም ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ አንሥቶ ትችት ሲሰነዘርበት የቆየው ዴሞክራሲን ማስፈን ባለመቻሉ ነው፡፡ መንግሥት ዴሞክራሲን ለማስፈን ብዙ ትኩረት ባለመስጠቱ የበላይና የበታች እንዲኖር፣ ፍትሕ እንዲዛባ በአጠቃላይም የመልካም አስተዳደር እጦት በአገሪቷ እንዲስፋፋ አድርጓል በሚልም ይተቻል፡፡  አቶ አሰፋ አደፍርስ በአሜሪካ ለ39 ዓመታት ኖረዋል፡፡ በኢትዮጵያ በልማቱ ዘርፍ ከተሰማሩም ዓመታትን አስቆጥረዋል፡፡ በሥራ አጋጣሚ የሚያስተውሉት የመልካም አስተዳደር እጦት ግን አገሪቷን ወደኋላ የጐተተ፤ እሳቸውና ሌሎች ባለሃብቶችም የተሰማሩባቸውን የተለያዩ የልማት ዘርፎች ከሚፈለገው ደረጃ እንዳይደርስ ማነቆ የሆነ ችግር እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ የመልካም አስተዳደር እጦት በተንሰራፋበት ሁኔታ የሚታይ የኢኮኖሚ ዕድገትም በሕዝቡ ኑሮ ላይ ለውጥ እንደማያመጣም ይናገራሉ፡፡ ከሚኖሩበት አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ በአገሪቱ ለውጥ ማየታቸውን፤ ሆኖም ለውጡ መሳጭ አለመሆኑን የሚናገሩት አቶ አሰፋ “አገር ውስጥ ያለውም ሆነ ከውጭ የሚመጣ ባለሀብት ሕንጻ ሊሠራ ይችላል፡፡ ሕንጻ ስለተደረደረ ግን ልማት ለማ ማለት አይደለም፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ከሕዝቧ በላይ ሊያስተዳድር የሚችል ሀብት አላት፡፡ ሆኖም በየመንገዱ የሚለምን እናያለን፣ ልጃቸውን አዝለው የሚበሉት የሚጠይቁ ይታያሉ፡፡ ይህ የሚሆነው ከመልካም አስተዳደር እጦት በሚመነጭ ችግር ነው፡፡ መልካም አስተዳደርን ያላካተተ ልማት ልማት አይባልም፤” ብለዋል፡፡ በመልካም አስተዳደር እጦት ላይ ያለው ችግር አሁን የመጣ ሳይሆን የቆየ ሊሆን ይችላል፡፡ በደርግ ጊዜ ከነበረው