Posts

በቅርቡ ከእስር ቤት ወደ ሆስፒታል ስወሰዱ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት የመኪና ግጭት ኣደጋ ደርሶባቸው የነበሩት ካላ ዱካሌ ላሚሶ

Image
በኣደጋ ምክንያት በግንባራቸው ላይ የደረሰባቸውን ጉዳት ፎቶውን ኣጉልተው ይመልከቱ የ 55 ዓመት እድሜ ባለበት የሆኑት እና በአሁኑ ወቅት በማረሚያ ቤት ሆነው በስኳርና የደም ግፊት እየተሰቃዩ የሚገኙት ካላ ዱካሌ ላሚሶ ፣ በነሐሴ 10/2004 ዓ . ም ከስራ ቦታቸው ታፍነው እስር ቤት የተወረወሩት፣ እስከዛሬ መስከረም 15/2005 ዓ . ም ድረስ ክስ ሳይመሰረትባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙት እና ለሲዳማ ሕዝብ መብት ሕይወታቸውን ሙሉ ሲታገሉ የኖሩ፣በግብርና ዘርፍ ማስተርሳቸውን በእንግሊዝ ሀገር በ 1980 ዎቹ ያገኙት አቶ ዱካሌ ላሚሶ መስከረም 14/2005 ዓ . ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ በቴክኒክና ሞያ ት / ቤት አካባቢ ከወህኒ ቤት በፖሊስ ታጅበው ለደም ግፊት ህክምና ወደ ሃዋሳ ሬፈራል ሆስፒታል ሄደው ሲመለሱ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከተጫኑበት ባጃጅ ጭምር ታርጋ በሌለው መኪና ተገጭተው 4 ሜትር በሚረዝመው የአስፋልት ጠርዝ ገደል ውስጥ ጥለዋቸው ለጊዜው ተሰውረዋል፡፡በዚህም አደጋው በደረሰበት አካባቢ ህብረተሰብ ርብርብ ሕይወታቸው የተረፈ ሲሆን ታርጋ የሌለው ተሸከርካሪም ለጊዜው ተሰውሯል፡፡ 

ጉዳዩ፡-ስለ ፍትሕ መጓደል አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጠን መጠየቅ

ቀን፡ 15/01/2005 ቁጥር፡ ቄለተድሮ 01/2005 በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞከራሲዊ ሪፐብሊክ ለጠቅላይ ሚኒስተር ጽ / ቤት አዲስ አበባ፡ - ጉዳዩ፡ - ስለ ፍትሕ መጓደል አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጠን መጠየቅ ይሆናል :: ከላይ በመግቢያው ላይ እንደተጠቀሰው በኢ . ፌ . ዴ . ሪ ሕገ - መንግስት አንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ ሕገ - መንግስት የህጎች የበላይ ህግ መሆኑን ይደነግጋል፡፡ ማንኛውም የመንግስት አካል ወይም ባለሥልጣን ውሳኔ ከዚህ ሕገ - መንግስት ጋር የሚቃረን ከሆኔ ተፈፃሚነት እንደማይኖራቸው ይገልፃል፡፡ ( The Constitution is the supreme law of the land. Any law, customary practice or a decision of an organ of state or a public official that contravenes this Constitution shall be of no effect ) ፡፡ በተጨማሪም በዚህ ህገ - መንግስት በአንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ በኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የኢትዮጵያ ሉአላዊ ሥልጣን ባለቤቶች መሆናቸውን ይደነግጋል ( All sovereign power resides in the nations, nationalities and peoples of Ethiopia ) ፡፡ ይሄ ሕገ - መንግስት ከደነገገው ውጪ የደቡብ ብሔሮች በሔረሰቦችና ሕዝቦች ከልል የሚገኙ አንዳንድ ከፍተኛ አመራሮች ለሕዝብ መልካም አስተዳደርና ልማት ማረጋገጥ ካለመቻላቸውም በላይ በሕዝብና በመንግስት መካከል ያለውን አመኔታ የሚሸረሽሩ ድርጊቶችን፣ ክራይ ሰብሳቢነትንና ምግባረ - ብልሹነትን ለረጅም ጊዜያት ከመፈፀማቸው ጋር አያይዞ ሕዝቡ አኝኮ ስለተፋቸው ይህንን ለማስለወጥ የህዝብ አገልጋይ የሚ

የ2005 ምርጫን ነፃ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ ቅንጅታዊ ስራ ተጠየቀ

Image
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2005 ዓ.ም በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎችና በሁለቱ የከተማ መስተዳድሮች የሚካሄደው ምርጫ ነፃ ሰላማዊ ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ ፥የፍትህ አካላት ቅንጅታዊ ስራ ተጠየቀ። የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ለኦሮሚያ ክልል የፍትህ አካላት የተዘጋጀውን ስልጠናውን ሲከፍቱ እንዳስገነዘቡት ፥ በአካባቢ ምርጫ በሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ሊከሰት የሚችለውን ቅሬታ ፍትሀዊ መፍትሔ መስጠት እንዲቻል ፥ ተሻሽሎ የወጣውን የምርጫ ደንብና ህግ ፥ የፍትህ አካላት ጠንቅቀው ማወቅ ይጠበቅባቸዋል። ባለፉት ምርጫዎች እየተሻሻለ የመጣውን ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በያዝነው አመትም ይበልጥ እንከን የለሽ ለማድረግ በየደረጃው የሚገኙ የፍትህ አካላት በቦርዱ የተዘጋጀውን የምርጫ ሕግና ደንብ ተግባራዊ ማድረጋቸው የጎላ ድርሻ ይኖረዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል። http://www.fanabc.com/Story.aspx?ID=26162&K=

ምርጫው ግም አለ፤ተኩላዎቹም የጫጩቶቹን እድሜ እንዲራዘም…

ሕገ-መንግስታዊ መብቶቻችን እንዲከበሩና በተግባር እንዲውሉ ስንጮህ ኖረን ዛሬ ሰሚ ጆሮ በማግኝታችን ጥሪው የሚወደስ ነው፡፡  ይህም ሆኖ   ጅማሮው እንዳይደናቀፍ የዴሞክራሲ ጠላቶች  ጆሮ ይደፈን በሚል መፈክር ሁሉን ዘግቶ ወደ እንቅስቃሴ መሸጋገር ግን የተሟላ መፍትሔ ነው ብዬ አላምንም፡፡ኢህአዴግም ሆነ ተቃዋሚዎችን ጨምሮ መላው ሕብረተሰብ  በችግሮቻችንን መንስኤዎቻቸውንና መፍትሄዎቹ ላይ ዘለቅ ብለን፣ ከተቻለ በጋራ ካልሆነም የተገኘውን መገናኛ ብዙሃን ተጠቅመን መፈተሽ አለብን ብዬ አምናለሁ፡፡ በችግሮቹ ላይ መግባባት ሳይፈጠር በመፍትሔዎቹ ላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ መጣር መፍትሔውን ግማሽ ልጩ ግማሽ ጎፈሬ ከመሆን አያድነውም፡፡የዛሬ ሃያ አንድ ዓመት አካባቢ ተከታታይ ሽንፈቱን ተከትሎ ጥርጣሬ፣ ስጋትና ፍርሃት የገባውን የደርግ ሽለላና ፉከራ አሸንፎ ኢህአዴግ ስልጣንን ከደርግ እጅ ሲረከብ የተገጠመ የማስታውሰው ስነ-ቃል አስታውሳለሁ፡፡ “ኢህአዴጎ ኢህአዴጎ፤ ገና ትበላለህ ወተትና እርጎ፡፡” መባሉን፤ በወቅቱ ኢህአዴግ ንዑስ ከበርቴ ከሚለው ከተሜው ይመንጭ  ወይም ከአርሶ አደሩ እርግጠኛ  አይደለሁም፡፡  ስነ-ቃሉ ተረት ተረት ሊመስል ይችላል፡፡ እውነታው ግን ወዲህ ይመስለኛል፡፡ “እናንተስ ማን ትመስሉ፡፡” የሚል መሰረታዊ ጥያቄን ያቀፈ መሆኑ ግን ጥርጥር የለውም፡፡ በሕዝብ  ጥቅም ስም ተደራጅተናል፣ አምላክ ቀብቶናል፣ በወታደሩ ተወክለናል በማለት ሕዝብን ነጻነቱን ለይስሙላ አረጋግጠው ሚሊኒክ ቤተ መንግስት ከገቡ በኋላ እራሳቸውን ተግተው የሚያገለግሉ በርካታ አምባገነኖችንን መታዘቡ  የፈጠረበት ስጋት እንደሆነ  አምናለሁ፡ ከሃያ አንድ ዓመት በኋላ ጥርጣሬው ጥርጣሬ ሆኖ ቀረ ወይስ የተጠረጠረው ደረሰ ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ወቅታዊ ነው፡፡  እውነቱና

ይድረስ ለኢህአዴግ (ኧረ ንቃ ኢህአዴግ!)

Written by  አለምሰገድ አ. ኢህአዴግና ፌስቡክ የኢህአዴግ ካድሬዎች በተለይ ሚዲያው አካባቢ የተሰማሩቱ እንደ ፌስቡክ “አቢዩዝ” ያደረጉት የቴክኖሎጂ ውጤት ያለ አይመስለኝም፡፡ ፌስቡክን አያውቁትም ግን ይፈሩታል፣ ይሸሹታል፣ ተጠቃሚዎቹንም “አብዮተኞች” በሚል ድፍርስ ስም ይጠራሉ፡፡ ስለዚህ ኢህአዴግ በፌስቡክ አማካኝነት ማግኘት የሚገባውን ጥቅም መቶ በመቶ ሳያገኝ ቀርቷል፡፡  ኢህአዴግ የፌስቡክንና የኢትዮጵያን ዝምድና አያውቅም። በዚህም የተነሳ የፌስቡክ አብዮት ይነሳብኛል ብሎ ሰግቶ ነበር፡፡ (የምዕራብ አፍሪካ ህዝባዊ አብዮት የተቀሰቀሰ ሰሞን) በማህበራዊ  ድረ-ገጾች ላይ በጃሚንግ ዘመተ፡፡ በመጨረሻም “የፌስቡክ አብዮተኞች” ሲል አደገኛ ታፔላ ይለጥፏል፡፡ እስቲ በሞቴ ይታያችሁ… ይቺ ሀገር በፌስቡክ አብዮተኞች ኢህአዴግን ከስልጣን ስታባርር? ይሄ ብዥታ እና የእውቀት ማነስ ኢህአዴግን እንደፓርቲ፣ ኢትዮጵያንም እንደ ሃገር ከማህበራዊ ድረ-ገጾች ማግኘት የሚገባቸውን ጥቅም እንዲያጡ አድርጓቸዋል፡፡ (ወይ ነዶ!) እናም ኢህአዴግን ልመክረው እፈልጋለሁ፡፡ ፌስቡክን እንዳይፈራ! የፌስቡክ አብዮተኞች ከየት? ይኸውልህ ውዱ መንግስታችን… በፍጹም አትስጋ! ኢትዮጵያውን በፌስቡክ አብዮት ያነሳሉ፣ ጐዳናውን በአመጽ ያሸብሩታል ብለህ በአስቂኝ የቀትር ብርድ እራስህን አትምታ፡፡ “አብዛኛው” የፌስቡክ ተጠቃሚ ኢትዮጵያዊ ያንተ ቢጤ ነው። የፌስቡክን ጥቅም በቅጡ አልተረዳም፡፡ ምናልባትም የጅንጀና አብዮት፣ የሽሙጥ አብዮት፣ የወሲብ አብዮት፣ የስድብ አብዮት ወዘተ ከቀሰቀሰ እንጂ የፖለቲካውንስ ነገር ተወው! (ያውም የኢትዮጵያ?) ኢህአዴግ… የምሬን ነው የምነግርህ፡፡ ከፈለግህ እገሌ እባላለሁ ብለህ “ቆንጅዬ” የአራዳ ስም ለራስህ ስጥና (ዴቭ፣ ናሂ፣ ኤቢ፣ ጃ፣ .