Posts

የ2005 ምርጫን ነፃ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ ቅንጅታዊ ስራ ተጠየቀ

Image
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2005 ዓ.ም በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎችና በሁለቱ የከተማ መስተዳድሮች የሚካሄደው ምርጫ ነፃ ሰላማዊ ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ ፥የፍትህ አካላት ቅንጅታዊ ስራ ተጠየቀ። የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ለኦሮሚያ ክልል የፍትህ አካላት የተዘጋጀውን ስልጠናውን ሲከፍቱ እንዳስገነዘቡት ፥ በአካባቢ ምርጫ በሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ሊከሰት የሚችለውን ቅሬታ ፍትሀዊ መፍትሔ መስጠት እንዲቻል ፥ ተሻሽሎ የወጣውን የምርጫ ደንብና ህግ ፥ የፍትህ አካላት ጠንቅቀው ማወቅ ይጠበቅባቸዋል። ባለፉት ምርጫዎች እየተሻሻለ የመጣውን ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በያዝነው አመትም ይበልጥ እንከን የለሽ ለማድረግ በየደረጃው የሚገኙ የፍትህ አካላት በቦርዱ የተዘጋጀውን የምርጫ ሕግና ደንብ ተግባራዊ ማድረጋቸው የጎላ ድርሻ ይኖረዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል። http://www.fanabc.com/Story.aspx?ID=26162&K=

ምርጫው ግም አለ፤ተኩላዎቹም የጫጩቶቹን እድሜ እንዲራዘም…

ሕገ-መንግስታዊ መብቶቻችን እንዲከበሩና በተግባር እንዲውሉ ስንጮህ ኖረን ዛሬ ሰሚ ጆሮ በማግኝታችን ጥሪው የሚወደስ ነው፡፡  ይህም ሆኖ   ጅማሮው እንዳይደናቀፍ የዴሞክራሲ ጠላቶች  ጆሮ ይደፈን በሚል መፈክር ሁሉን ዘግቶ ወደ እንቅስቃሴ መሸጋገር ግን የተሟላ መፍትሔ ነው ብዬ አላምንም፡፡ኢህአዴግም ሆነ ተቃዋሚዎችን ጨምሮ መላው ሕብረተሰብ  በችግሮቻችንን መንስኤዎቻቸውንና መፍትሄዎቹ ላይ ዘለቅ ብለን፣ ከተቻለ በጋራ ካልሆነም የተገኘውን መገናኛ ብዙሃን ተጠቅመን መፈተሽ አለብን ብዬ አምናለሁ፡፡ በችግሮቹ ላይ መግባባት ሳይፈጠር በመፍትሔዎቹ ላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ መጣር መፍትሔውን ግማሽ ልጩ ግማሽ ጎፈሬ ከመሆን አያድነውም፡፡የዛሬ ሃያ አንድ ዓመት አካባቢ ተከታታይ ሽንፈቱን ተከትሎ ጥርጣሬ፣ ስጋትና ፍርሃት የገባውን የደርግ ሽለላና ፉከራ አሸንፎ ኢህአዴግ ስልጣንን ከደርግ እጅ ሲረከብ የተገጠመ የማስታውሰው ስነ-ቃል አስታውሳለሁ፡፡ “ኢህአዴጎ ኢህአዴጎ፤ ገና ትበላለህ ወተትና እርጎ፡፡” መባሉን፤ በወቅቱ ኢህአዴግ ንዑስ ከበርቴ ከሚለው ከተሜው ይመንጭ  ወይም ከአርሶ አደሩ እርግጠኛ  አይደለሁም፡፡  ስነ-ቃሉ ተረት ተረት ሊመስል ይችላል፡፡ እውነታው ግን ወዲህ ይመስለኛል፡፡ “እናንተስ ማን ትመስሉ፡፡” የሚል መሰረታዊ ጥያቄን ያቀፈ መሆኑ ግን ጥርጥር የለውም፡፡ በሕዝብ  ጥቅም ስም ተደራጅተናል፣ አምላክ ቀብቶናል፣ በወታደሩ ተወክለናል በማለት ሕዝብን ነጻነቱን ለይስሙላ አረጋግጠው ሚሊኒክ ቤተ መንግስት ከገቡ በኋላ እራሳቸውን ተግተው የሚያገለግሉ በርካታ አምባገነኖችንን መታዘቡ  የፈጠረበት ስጋት እንደሆነ  አምናለሁ፡ ከሃያ አንድ ዓመት በኋላ ጥርጣሬው ጥርጣሬ ሆኖ ቀረ ወይስ የተጠረጠረው ደረሰ ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ወቅታዊ ነው፡፡  እውነቱና

ይድረስ ለኢህአዴግ (ኧረ ንቃ ኢህአዴግ!)

Written by  አለምሰገድ አ. ኢህአዴግና ፌስቡክ የኢህአዴግ ካድሬዎች በተለይ ሚዲያው አካባቢ የተሰማሩቱ እንደ ፌስቡክ “አቢዩዝ” ያደረጉት የቴክኖሎጂ ውጤት ያለ አይመስለኝም፡፡ ፌስቡክን አያውቁትም ግን ይፈሩታል፣ ይሸሹታል፣ ተጠቃሚዎቹንም “አብዮተኞች” በሚል ድፍርስ ስም ይጠራሉ፡፡ ስለዚህ ኢህአዴግ በፌስቡክ አማካኝነት ማግኘት የሚገባውን ጥቅም መቶ በመቶ ሳያገኝ ቀርቷል፡፡  ኢህአዴግ የፌስቡክንና የኢትዮጵያን ዝምድና አያውቅም። በዚህም የተነሳ የፌስቡክ አብዮት ይነሳብኛል ብሎ ሰግቶ ነበር፡፡ (የምዕራብ አፍሪካ ህዝባዊ አብዮት የተቀሰቀሰ ሰሞን) በማህበራዊ  ድረ-ገጾች ላይ በጃሚንግ ዘመተ፡፡ በመጨረሻም “የፌስቡክ አብዮተኞች” ሲል አደገኛ ታፔላ ይለጥፏል፡፡ እስቲ በሞቴ ይታያችሁ… ይቺ ሀገር በፌስቡክ አብዮተኞች ኢህአዴግን ከስልጣን ስታባርር? ይሄ ብዥታ እና የእውቀት ማነስ ኢህአዴግን እንደፓርቲ፣ ኢትዮጵያንም እንደ ሃገር ከማህበራዊ ድረ-ገጾች ማግኘት የሚገባቸውን ጥቅም እንዲያጡ አድርጓቸዋል፡፡ (ወይ ነዶ!) እናም ኢህአዴግን ልመክረው እፈልጋለሁ፡፡ ፌስቡክን እንዳይፈራ! የፌስቡክ አብዮተኞች ከየት? ይኸውልህ ውዱ መንግስታችን… በፍጹም አትስጋ! ኢትዮጵያውን በፌስቡክ አብዮት ያነሳሉ፣ ጐዳናውን በአመጽ ያሸብሩታል ብለህ በአስቂኝ የቀትር ብርድ እራስህን አትምታ፡፡ “አብዛኛው” የፌስቡክ ተጠቃሚ ኢትዮጵያዊ ያንተ ቢጤ ነው። የፌስቡክን ጥቅም በቅጡ አልተረዳም፡፡ ምናልባትም የጅንጀና አብዮት፣ የሽሙጥ አብዮት፣ የወሲብ አብዮት፣ የስድብ አብዮት ወዘተ ከቀሰቀሰ እንጂ የፖለቲካውንስ ነገር ተወው! (ያውም የኢትዮጵያ?) ኢህአዴግ… የምሬን ነው የምነግርህ፡፡ ከፈለግህ እገሌ እባላለሁ ብለህ “ቆንጅዬ” የአራዳ ስም ለራስህ ስጥና (ዴቭ፣ ናሂ፣ ኤቢ፣ ጃ፣ .

የፖለቲካ ባህላችንን እንፈትሽ

በበላይ ዓለሙ ይህችን አጭር ጽሑፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ ጳጉሜን 3 ቀን 2004 ዓ.ም. ማታ በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጣቢያ የተላለፈው የአቶ ተስፋዬ ሐቢሶና የቅንጅት አባል የሆኑ ግለሰብ ውይይት ነው፡፡ ከጳጉሜን 3 ቀን በፊት ሁለት ግለሰቦች ያደረጉት ውይይት ካለ አልሰማሁምና አስተያየት መስጠት አልችልም፡፡ በዕለቱ በተደረገው ውይይት ሁለት ተፃራሪ ስሜቶች ናቸው የተሰሙኝ፡፡ አንደኛው መልካም ስሜት ሲሆን፣ ሌላኛው ግን ተቃዋሚዎቻችን እነዚህ ናቸው? እነዚህ ናቸው የአገራችን ተስፋዎች? የሚል የተስፋ መቁረጥ ስሜት ነው፡፡ በእርግጥ የቅንጅቱ አባል የተናገሩት የግል አቋማቸውን ይሁን የድርጅታቸውን መለየት ቢያስቸግርም፣ የሳቸውን የሚመስል ተመሳሳይ አቋም ከሌሎችም አንቱ ከተሰኙ ተቃዋሚዎች የሰማሁ ስለሆነ፣ የድርጅቱ አቋም ሊሆን ይችላል የሚል ኃይለኛ ጥርጣሬ ጭሮብኛል፡፡ የምሽቱ ውይይት ያተኮረው በቅርቡ በሞት የተለዩንን የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን አመራርን በተመለከተ ነበር፡፡ በእርግጥ አቶ መለስ ዜናዊን የሚያደንቋቸው ብዙ ኢትዮጵያውያንና የውጭ አገር ዜጎች እንዳሉ ሁሉ፣ በኃይለኛ የሚነቅፏቸውም በርካቶች ናቸው፡፡ በእነዚህ ሁለት ጽንፎች መሀል ያሉም አሉ፡፡ በምሽቱ በተደረገው ውይይት አቶ ተስፋዬ የኢሕአዴግ አባልና ደጋፊ ሳይሆኑ ስለ አቶ መለስ የሰጡት አስተያየት እጅግ አስደምሞኛል፡፡ በአንፃሩ የቅንጅት አባሉ የሰጡት አስተያየት እኚህ ሰው በእውነት የኢትዮጵያን ሁኔታ የተረዱ ሰው ናቸው ወይ? በእንደዚህ ዓይነት የተሳሳተ አመለካከት ነው ወይ አገርን መምራትና ሕዝብን ማሰለፍ የሚቻለው? አስብሎኛል፡፡ የጠራ የፖለቲካ መስመር ተጨባጩን አገር አቀፋዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታን በትክክል ከመገንዘብ ስለሚመነጭ፣ ምን ዓይነት መስመር ይሆን እነዚህ የተቃዋሚ ድርጅቶች የሚቀ

ሲዳማን ጨምሮ ቀይ መስቀል በደቡብ ክልል ለአምስት ዞኖች አምቡላንስ አከፋፈለ

Image
አዋሳ መስከረም 21/2005 የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የደቡብ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ አምቡላንሶችን ለአምስት ዞኖች አከፋፈለ። በክልሉ ከሚገኙ ቅርንጫፍ ማህበራት አምስቱ ከህብረተሰቡ ባሰባሰቡት ገንዘብና ከማህበሩ ከ18 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ እንዲገዙ ከታዘዙት 20 አምቡላንሶች የአስሩ ትናንት ርክክብ ተደርጓል። በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የደቡብ ክልል ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የቦርድ ሰብሳቢና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታመነ ተሰማ እንዳሉት መንግስት በነደፈው ዕቅድ መሰረት የእናቶችና ህጻናት ሞትን ለመቀነስ ለሁሉም ወረዳዎች እንዲዳረስ እያደረገ ነው። መንግስት እየተገበረ ያለውን የጤና ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ እያደረገ ያለውን ጥረት መንግስታዊ ያልሆኑ ማህበራትና ህብረተሰቡ እያደረጉ ያለው ተግባር የሚያበረታታ መሆኑን ጠቁመው የደቡብ ቀይ መስቀል ማህበር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የገዛቸው አምቡላንሶች የእናቶችና ህጻናትን ሞት ለመቀነስ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል። አምቡላንሶቹ ለታለመላቸው አገልግሎት ብቻ እንዲውሉ በማድረግ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡና የወረዳዎቹ ማዘጋጃ ቤቶች የነዳጅና አስፈላጊ ወጪያቸውን በመሸፈን ድጋፍ እንዲያደርጉ አቶ ታመነ አሳስበዋል። በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የደቡብ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መኮንን ፋራ አዲስ የተገዙት አምቡላንሶች በክልሉ የነበረውን የአምቡላንሶች ጣቢያ ከ22 ወደ 44 የሚያሳድገው መሆኑን ጠቁመው የጋሞጎፋና ደቡብ ኦሞ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን 944 ሺህ ብር ወጪ በማድረግ ለደቡብ ኦሞ ዞን ሀመር ወረዳ አንድ አምቡላንስ መግዛታቸውን ተናግረዋል። አምቡላንሶቹ በዝቅተኛ የኑሮ ደረ