Posts

Ethiopians in New York hold the first rally against Hailemariam Desalegn

Image
Tedla Asfaw The rainy cloudy Sept. 28, 2012 was not a welcome weather for anyone. It was raining hard from early morning and we followed the weather hour by hour fearing for a washout of our rally scheduled for 3pm at 47 Street and 2nd Avenue at UN. Rain started to tamper down at noon but still the cloud was threatening. Hailemariam Desalegn might have liked the rainy day to avoid any protest after he gave a very unwelcome interview to VOA’s Peter Heinlein yesterday which angered most of us.  Our protest rally was not organized to unwelcome or welcome Hailemariam. It was a Freedom rally which was dubbed as May 18 the Freedom rally which forced the late Meles Zenawi to bow his head in front of his foreign supporters at Regan Building in DC on May 18 this year. The slogan we prepared were calling for all political prisoners to be released and the backers of the Ethiopian regime to stop financing dictatorship that violated civil rights of its citizens. However, after the Sept

Any Decision on the status of Hawassa Administration and the Sidama Regional Question without Referendum will remain Illegal

By Hawassa Teessonke 28 September 2012 The ongoing meeting in Hawassa called by the EPRDF President of Southern region about which our various reporters have provided an excellent account is said to have continued as misguided as ever. Reports indicate that the meeting has discussed the following five agenda during the past three days: 1) How the development of Sidama can be sustained. 2) Why the people of Sidama do not accept the concept of EPRDF/SEPDM. The Oromo people are more numerous than the Sidama people but they are under the EPRDF/ OPDO rule. 3) As long as the Sidama people are forced to be under SEPDM rule, they would be forced to allow joint administration of the Hawassa town. The Sidama cadres should apologize for not letting that happen up till now. 4) The question of regional self-administration is not possible for now and for ever. 5) Anybody who is interested to fight for the freedom of the Sidama people can continue to fight but the members of the SEPD

የሕግ ፍትህ እና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምን ሠራ?

Image
ባለፈው ዕትማችን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ፍትህ እና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በ2004 ዓ.ም ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ ከኮሚቴው አባል የተከበሩ አቶ ዳዊት ተፈራ ጋር ባደረግነው ቃለ ምልልስ ማስነበባችን ይታወሳል፤ በዚህ እትማችን ደግሞ ቀሪውን ክፍል ይዘን ቀርበናል፡፡   ሕግ ከማውጣት አንፃር ቋሚ ኮሚቴው ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ አምስት ረቂቅ አዋጆችን ከሌሎች ቋሚ ኮሚቴዎች ጋር በመተባበር ሰርቷል፡፡ረቂቅ ሕጎቹ የሕግ አወጣጥ ሥርዓትን በተከተለ ሁኔታ ተረቅቀው የውሳኔ ሃሳብ ሪፖርት ቀርቦባቸው በምክር ቤቱ እንዲፀድቁ ተደርጓል፡፡ ሌላው ቋሚ ኮሚቴው ብቻውን የሚመለከተው እና ኃላፊነቱን ወስዶ በማርቀቅ ለምክር ቤቱ የውሳኔ ሃሳብ በማቅረብ የፀደቀው 'የወሳኝ ኩነት እና ብሔራዊ መታወቂያዎች' የሚለው አዋጅ ነው፡፡ በዚህ አዋጅ መሰረት የእያንዳንዱ ሰው ከልደት እስከ ሞት ያለው መረጃ ይመዘገባል፡፡ ለዚሁ ሥራ ከታች እስከ ላይ መዋቅር ያለው ጽ/ቤት ይቋቋማል፡፡ በአዋጁ መሰረትም እንደ ኢትዮጵያዊነት ለሁሉም ብሔራዊ መታወቂያ ይዘጋጃል፡፡መታወቂያው ሙሉ የማንነት መረጃን የያዘ ሲሆን ፤ለብሔራዊ ደህንነት እንዲሁም መንግሥት ሊዘረጋቸው ለሚፈልጋቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሰረተ ልማቶች ጭምር አጋዥ ነው የሚሆነው፡፡  ምንም እንኳን በበቂ ሁኔታ ተሳትፎበታል ለማለት ባያስደፍርም በረቂቅ አዋጁ ላይ ሕዝቡ ተሳትፎ እንዲያደርግበት ኮሚቴው ጥረት አድርጓል የሚሉት አቶ ዳዊት ረቂቁን ለማዳበር ከሚመለከታ ቸው አካላት ጋር የውይይት መድረክ ተፈጥሮ ጠቃሚ ግብአትም ከመገኘቱም በላይ ለጉዳዩ ቅርበት አላቸው ተብሎ ለሚታሰቡ ወገኖችና ተቋማትም ረቂቁ ላይ የበኩላቸውን ሃሳቦች ሰንዝረዋል። ሌላው ቋሚ ኮሚቴው ከሚያከናውናቸው

መረጃ:- የግልጽነትና የተጠያቂነት ቁልፍ መሳሪያ

ከኢፌዲሪ ህገ- መንግስት አምስት መሰረታዊ መርሆዎች ውስጥ የመንግስት አሰራርና ተጠያቂነት አንዱ ነው፡፡ የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህ በመንግስት ሀላፊዎች የሚወሰዱ ውሳኔዎችና የስራ እቅስቃሴዎች ለህዝቡ ግልጽ መሆናቸውንና ህዝቡም ይህንን በተመለከተ ያሉትን መረጃዎች ለማግኘት ያለውን መብት የሚያረጋግጥ መርህ ነው፡፡ የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህ የዲሞክራሲ ዋልታ በመሆኑም ከመርሁ ተግባራዊነት ውጪ ዲሞክራሲን ማስፈን የማይታሰብ ነው፡፡ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት መጎልበት ትልቁን ድርሻ የሚይዘውን የህዝቦች ተሳትፎና የስልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥም ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመንግስት አሰራርን እውን ማድረግ የግድ ይላል፡፡ ዜጎች በፖለቲካና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግና የመንግስት ሀላፊዎች ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ መሆኑን ለመመርመር ተገቢውን መረጃ ሊያገኙ ይገባል፡፡ ግልጽነትም ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ሲሆን ለተጠያቂነትም እንደ ቅድመ ሁኔታ ይቀመጣል፡፡ በመሆኑም የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህ የህዝቦችን ተሳትፎ ከማሳደጉም በላይ የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ዜጎች መረጃ የመጠየቅ፣ የማግኘትና የማስተላለፍ መብታቸው መከበሩ አንድም ተሳትፎአቸውን ለማሳደግ ሌላም የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህን በመተግበር የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ተግባራዊነትን ለማረጋገጥ የሚኖረው ድርሻ የጎላ ነው፡፡፡ ዜጎች መረጃ ለማግኘት በራሳቸው ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ በተጨማሪም ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን በመፈለግና ለህዝቡ ተደራሽ በማድረግም የመገናኛ ብዙሀን ጉልህ ሚና አላቸው፡፡ የመገናኛ ብዙሀንና የመረጃ ነጻነት አዋጅ ቁጥር 590/2000 የመደንገጉ ምክንያትም የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብትንና የመገ

በቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባና ሌሎች የከተማዋ አስተዳደር ሃላፊዎች ላይ ፍርድ ቤት ትእዛዝ አስተላለፈ

Image
አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2005  (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የቀድሞውን የሀዋሳ ከንቲባ ጨምሮ በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች ላይ በነበሩ የከተማዋ አስተዳደር ሃላፊዎች በተከሰሱበት በእነ አቶ እንድርያስ ኦሌሳ መዝገብ የተለያዩ ትአዛዞችን አስተላለፈ፡፡  ከመሬት ጋር በተያያዘ ያልተገባ ጥቅም ለራሳቸውና ለቤተሰቦቿቸው ለማስገኘት በማሰብ ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም የተከሰሱት እነዚሁ የከተማዋ አስተዳደር የተለያዩ ሃላፊዎች የፍርድ ሂደት የሀዋሳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲመለከተው ቢቆይም በነጻ አሰናብቷቸው ነበር፡፡ የከልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ጉዳዩን ማየት ከጀመረ በኋላ ግን ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ያልቻሉትን 1ኛ ተከሳሽ እንድሪስ አሎሳና 2ኛ ተከሳሽ ጉደታ ጎምቢ በፖሊስ ተፈልገው ሊገኙ ስላልቻሉ ስማቸውና ምስላቸው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ እንዲፈለጉ ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡ ፍርድ ቤቱ በዚሁ መዝገብ የተከሰሱ የሌሎች 4 ተከሳሾች የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ትእዛዝ ማስተላለፉን ነብዩ ይርጋአለም ዘግቧል። http://www.fanabc.com/Story.aspx?ID=26121&K=