የሕግ ፍትህ እና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምን ሠራ?
ባለፈው ዕትማችን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ፍትህ እና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በ2004 ዓ.ም ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ ከኮሚቴው አባል የተከበሩ አቶ ዳዊት ተፈራ ጋር ባደረግነው ቃለ ምልልስ ማስነበባችን ይታወሳል፤ በዚህ እትማችን ደግሞ ቀሪውን ክፍል ይዘን ቀርበናል፡፡ ሕግ ከማውጣት አንፃር ቋሚ ኮሚቴው ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ አምስት ረቂቅ አዋጆችን ከሌሎች ቋሚ ኮሚቴዎች ጋር በመተባበር ሰርቷል፡፡ረቂቅ ሕጎቹ የሕግ አወጣጥ ሥርዓትን በተከተለ ሁኔታ ተረቅቀው የውሳኔ ሃሳብ ሪፖርት ቀርቦባቸው በምክር ቤቱ እንዲፀድቁ ተደርጓል፡፡ ሌላው ቋሚ ኮሚቴው ብቻውን የሚመለከተው እና ኃላፊነቱን ወስዶ በማርቀቅ ለምክር ቤቱ የውሳኔ ሃሳብ በማቅረብ የፀደቀው 'የወሳኝ ኩነት እና ብሔራዊ መታወቂያዎች' የሚለው አዋጅ ነው፡፡ በዚህ አዋጅ መሰረት የእያንዳንዱ ሰው ከልደት እስከ ሞት ያለው መረጃ ይመዘገባል፡፡ ለዚሁ ሥራ ከታች እስከ ላይ መዋቅር ያለው ጽ/ቤት ይቋቋማል፡፡ በአዋጁ መሰረትም እንደ ኢትዮጵያዊነት ለሁሉም ብሔራዊ መታወቂያ ይዘጋጃል፡፡መታወቂያው ሙሉ የማንነት መረጃን የያዘ ሲሆን ፤ለብሔራዊ ደህንነት እንዲሁም መንግሥት ሊዘረጋቸው ለሚፈልጋቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሰረተ ልማቶች ጭምር አጋዥ ነው የሚሆነው፡፡ ምንም እንኳን በበቂ ሁኔታ ተሳትፎበታል ለማለት ባያስደፍርም በረቂቅ አዋጁ ላይ ሕዝቡ ተሳትፎ እንዲያደርግበት ኮሚቴው ጥረት አድርጓል የሚሉት አቶ ዳዊት ረቂቁን ለማዳበር ከሚመለከታ ቸው አካላት ጋር የውይይት መድረክ ተፈጥሮ ጠቃሚ ግብአትም ከመገኘቱም በላይ ለጉዳዩ ቅርበት አላቸው ተብሎ ለሚታሰቡ ወገኖችና ተቋማትም ረቂቁ ላይ የበኩላቸውን ሃሳቦች ሰንዝረዋል። ሌላው ቋሚ ኮሚቴው ከሚያከናውናቸው