የኒዮሊበራሊዝም ቀውስና የአፍሪካ ተስፋ
አፍሪካ ምንም እንኳ ከሃምሳ ዓመታት በፊት ሙሉ ለሙሉ ከቅኝ ግዛት ብትላቀቅም መለያዋ ከሆነው ድህነት ነፃ መውጣት አልተቻላትም፡፡ «በአህጉሪቷ ድህነት ስር ሰዶ ሊነቀል በማይችል መልኩ ተተክሏል» የሚሉት በርካቶች ናቸው፡፡ ያደጉት አገሮችም አህጉሪቷ ከድህነት እንድትወጣ የሚያስችላትን አቅጣጫን ከማመላከት ይልቅ በየጊዜው ዕርዳታ እየሰጡ እጅ በመጠምዘዝ በፈለጉት መንገድ መምራቱን ነው የመረጡት። ያደጉት አፍሪካ አምርታ የምታገኘውን ውጤት ለዓለም ማቅረብ የማትችል እንደሆነች የበለፀጉት አገሮች ያስባሉ፡፡ አፍሪካውያን ለዘላለም ከድህነትና ከተረጂነት መላቀቅ እንደማይችሉ ይገምታሉ፡፡ እነርሱ ሊተገብሩት የሚፈልጉትን ነገር በአፍሪካ መሞከርም ምርጫቸው ነበር። አፍሪካ መሞከሪያ ከተደረገችበት ነገር ውስጥ አንዱ የኒዮሊበራሊዝም የኢኮኖሚ ርዕዮተ ዓለም አንደኛው ነው፡፡ በ1930ዎቹ መገባደጃ መወጠኑ የሚነገርለት ይህ ርዕዮተ ዓለም የሚያጠነጥነው ኢኮኖሚውና ገበያው ሙሉ ለሙሉ ከመንግሥት ውጪ ሆኖ ይንቀሳቀስ በሚለው መስመር ላይ ነው፡፡ በእዚህ አካሄድ ላለፉት ከሦስት ያላነሱ አስርት ዓመታት አፍካውያኑም ሆኑ ያደጉት ሀገራት ተግባራዊ ሲያደርጉት ቆይተዋል፡፡ ይህንን ርዕዮተ ዓለም ተግባራዊ ያደረጉ ሀገራት በተለይም የአፍሪካ ሀገራት ዕድገት ማምጣትም ሆነ ከድህነት መላቀቅ አልቻሉም፡፡ ያደጉት ሀገራትም ቢሆኑ ቀስ በቀስ ሊወጡት በማይችሉት የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ተዘፍቀዋል፡፡በተቃራኒው የኒዮሊበራ ሊዝምን ርዕዮተ ዓለም ከመቀበል የታቀቡ ሀገራት ደግሞ የራሳቸውን መንገድ ቀይሰው በመንቀሳቀሳቸው ከስህተታቸው እየተማሩ ፈጣን እድገት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያዎቹ አስርት ዓመታት ኒዮሊብራሊዝምን በሚከተሉና በማይከተሉ ሀገራት መካከል ግልፅ ልዩነት የታ