Posts

ጉዳዩ፡-ስለ ፍትሕ መጓደል አስቸኳይ መፍትሔ እንድሰጠን ስለማሳሰብ ይሆናል::

ቀን፡-11/01/2005 ቁጥር፡-ድሩ ቄለ01/2005  ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞከራሲዊ ሪፓብልክ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት  አዲስ አበባ ጉዳዩ፡-ስለ ፍትሕ መጓደል አስቸኳይ መፍትሔ እንድሰጠን ስለማሳሰብ ይሆናል:: ከላይ በመግቢያው ላይ እንደተጠቀሰው በኢትዮጵያ ፌ/ዴ/ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 9 በንዑስ አንቀጽ አንድ ላይ የበላይ ህግ ያጎናፀፋቸው መብቶች በሰላማዊ አሰራር የመንግስት አካል ወይም ባለሥልጣን ውሳኔ ከዚህ ሕገ-መንግስት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት እንደማይኖራቸው ይደነግጋል፡፡ ይህ ህገ-መንግስት እንደገና በአንቀጽ 8 በንዑስ አንቀጽ አንድ ላይ በኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የኢትዮጵያ ሉአላዊ ሥልጣን ባለቤቶች መሆናቸውን ይደነግጋል፡፡ ይሄ ሕገ-መንግሰት ከደነገገው ውጪ የደቡብ ብሔሮች በሔረሰቦችና ሕዝቦች ከልል የሚገኙ አንዳንድ ከፍተኛ አመራሮች ለሕዝብ መልካም አስተዳደርና ልማት ማረጋገጥ ካለመቻላቸውም በላይ በሕዝብና በመንግስት መካከል አመኔታ የሚሸረሽሩ ድርጊቶችን ፣ክራይ ሰብሳብነትንና ምግባረ-ብልሹነትን ለረጅም ጊዜያት ከመፈፀማቸው ጋር ተያይዘው ሕዝቡ አንቅሮ ስለተፋቸው ይህንን ለማስለወጥ የህዝቡን ብሶት የሚቀሰቅሱ አጀንዳዎችን አንስተው በሕዝቡ መካከል በመዛት ያንኑ መልሰው ለመሸንገል በሚል አጀንዳ የመንግስትን ታአማንነት ለማግኘት ስሉ የመንግስትን ውስን ሀብት ለማባከን ላይ ታች ሲሉና የሥልጣን ዕድሜ ሲያራዝሙ ቆይተዋል፡፡ በዚህም መነሻ ህገ-መንግስቱ ለሲዳማ ህዝብ ካጎናፀፈለት መብቶች አንዱ የሆነውን ባህሉን ለማሳደግ የፍቼ-ጫምባላላ በዓል ስያከብር እስከ ዛሬ ደርሷል፡፡በነቂስ የሚወጣው ህዝብም በዝህ በዓል እንደባህሉ የሚወደውን አወድሶ፣ያልተመቻቸውንና ህጋዊነቱን ያጎደለውን ነገር ወቅሶ በሰላም ወደቤቱ ይመለሳል፡፡በነሐሴ 8

ጠቅላይ ሚኒስትር ኣቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ እና ሲዳማ

ፉቄ ዲሬሞ ከሃዋሳ የሲዳማ የራስ ገዝ የክልል ኣስተዳደርን በተመለከተ በህዝቡ ዘንድ የምነሱት ጥያቄዎች እድሜ ጠገብ ናቸው። ኣብዛኛዎች እንደምገምቱት በተለይ ከዛሬ ኣስር ኣመት ወዲህ የተጀመረና ከግዜ ወደ ጊዜ በህዝቡ ዘንድ እየሰረጸ የመጣ ጉዳይ ሳይሆን የሲዳማ ህዝብ ላለፉት ከሰላሳ ኣመታት በላይ ለነጻ ዲሞክራሲያዊ የራስ ኣስተዳደር ሲያደርግ የ ነበረው ትግል ኣካል ነው። የሲዳማ ህዝብ ከማንም የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ቀደሞ ለራስ ገዝ ኣስተዳደር እና ለመልካም ኣስተዳደር ብሎም ለዲሞክራሲያዊ ስርኣት መስፈን የታገለ ህዝብ ነው። ይህም ማለት የሲዳማ ህዝብ የ መልካም ኣስተዳደር እና የዲሞክራሲያዊ ስርኣት ግንባታ ኣስፈላግነትን በቅጡ የተ ረዳ ብሎም ሲታገልለት ቆየው ህዝብ ነ ው ፤ ለስኬቱም ብሆን ኣያሌ ውድ የሲዳማ ልጆች መስዋዕት ሆኖለታል እየሆኑም ይገኛል። የሲዳማ የምንም ጊዜ ውድ ልጆቿ የተሰውለት የመልካም ኣስተዳደር እና ዲሞክራሲያዊ የክልል ኣስተዳደር በተለይ ከሃያ ኣመታት በፊት በሲዳማ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላዋ ኢትዮጵያ የነበረው የደርግ ስርኣት ተገርስሰው ኣዲስ ስርኣት ሲቋቋም እውን ሆኖ ነበር ብሆንም ከጥቂት ጊዚያት በኃላ የራስ ክልል ኣስተዳደር መብቱን እንደገና መነጠቁ ይታወሳል። የሲዳማ ህዝብ ከመቶ ኣመታት በላይ ከሌሎች የኣገሪቱ ብሄሮች፤ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ጋር ተፋቅሮ፤ ተቻችሎ በኣንድነት የኖረ ህዝብ ብሆንም ፖለቲካዊ የራስ ገዝ ክልላዊ ኣስተዳደሩን መነጠቁ እና ከሌሎች ኣናሳ ብሄሮች ጋር በስሜ ደቡብ በኣንድ ክልል ውስጥ መጠፈሩን ሳይቀበለው ኖሯል። በኢህኣዴግ የምመራው መንግስት የወሰደውን ይህንን እርምጃ በተመለከተ በወቅቱ ህዝቡ ተቃውሞውን በተለያዩ ኣጋጣሚዎች እና በተለያየ መልኩ የገለጸ ቢሆንም ሰሚ

Historical Foundation of the Sidama Regional Question: Overview

By Hawassa Teessonke, September 23, 2012 I listened to the interviews on VOA by the chairperson of the Sidama Liberation Movement (SLM) and the Sidama EPRDF administrator with curiosity. While the former voiced genuine concerns that the regime is abusing the basic rights of the Sidama people by unlawfully harassing and imprisoning innocent civilians for voicing their basic rights for regional self-administration, the responses provided by the EPRDF administrator are regrettably unbalanced, out of touch with the reality on the ground and are deceitful. We all know that Dukale Lamisso, Abate Kimo Hokola, Iyasu Ragassa, Boshola Gabisso and many other Sidama civilians have never committed any crime except stating publicly that as a nation with 3.4 million people, Sidama has both natural and constitutional right to regional self-administration. The Sidama people have presented a number of reasons why they should be granted regional self-administration with immediate effect. Among

የእናቶችና የህፃናት ሞትን ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት አንድ አካል የሆነው የአቦላንስ አገልግሎት በክልሉ በሁሉም ወረዳዎች ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው  በ2ዐዐ4 በጀት ዓመት በክልሉ የሚገኙ 77 ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች የምቦላንስ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስቻለ ሲሆን በቀሪዎቹ 8ዐ በቀጣይ 4 ወራት ጊዜ ውስጥ የማዳረስ ስራ እንደሚሰራ በቢሮው የህክምናና ታህድሶ የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ሀብታሙ ገልፀዋል፡፡ አምቦላንሶቹ ከአርግዝናና ከወሊድ ጋር በተያያዘ  የሚከሰቱ የእናቶችን ሞት ፣  በአጣዳፊ፣ በሽታዎች እንዲሁም በተለያዩ አደጋዎች የሚከሰቱ ጉዳቶችን ለመግታት ጥቅም ላይ መዋል እንዳለባቸው አመልክተዋል፡፡ የወረዳና የከተማ አስተዳዳሪዎች እንዲሁም የጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ እንዳለባቸውም በመጠቆም፡፡ ይህን ተግባራዊ ለማድረግም በክልል ደረጃ  የአንቡላንስ አገልግሎት አጠቃቀምና አስተዳደር መመሪያ መውጣቱንና በሁሉም ተቋማት ውስጥ ተግባራዊ እንደሚደረግ መናገራቸውን ባልደረባችን ወንድወሰን ሽመልስ ከዲላ ከተማ ዘግቧል፡፡

በኢትዮጵያ ከ20 ሚሊዮን የሚበልጡ ጎልማሶች የመሰረተ ትምህርት ፕሮግራም

Image
አዋሳ መስከረም 12/2005 በኢትዮጵያ ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ከ20 ሚሊዮን የሚበልጡ ዜጎችን በተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት መርሃ ግብር ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ተስጥቶ እየሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ አለም አቀፍ የመሰረተ ትምህርት ቀን በዓል በሀገር አቀፍ ደረጃ " የጎልማሶች ትምህርት ለዘላቂ ሰላም " በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ ከትናንት ጀምሮ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡ በበአሉ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፉአድ ኢብራሂም እንደገለጹት ጎልማሶች ከዕለት ተዕለት ስራቸውና ህይወታቸው ጋር የተያያዘ ጤናቸውን በመጠበቅ ምርታማነታቸውን እንዲያሻሻሉ ትምህርትና ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም፡፡ የምዕተ አመቱን የልማትና የትምህርት ግቦችን ከዳር ለማድረስ በተለይም የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን ለማሳካት ጎልማሶች ከፍተኛ አስተዋጾኦ እንደሚያበርክቱ አስረድተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በአለማችን 796 ሚሊዮን በሀገራችን ደግሞ 20 ነጥብ 4 ሚሊዮን ጎልማሶች ማንበብና መጻፍ እንደማይችሉ አመልክተው በተለይ በትራንስፎርሜሽን እቅዱ አመት መጨራሻ ሁሉንም ጐልማሶች ለማብቃት ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡ ለዚህም የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት መርሀ ግብር ተዘጋጅቶ ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ ለድህነት መወገድና ለሀገራችን ዕድገት በጽኑ ይመኙና ለስኬታማነቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ቀያሽ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ " ሁሉም ትምህርት ቤቶች ፣ የገበሬ ማሰልጠኛ ጣቢያዎችና የጤና ኬላዎች ማንበብና መጻፍ ለማይችሉ የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት ለማዳረስ ከፍተኛ አስተዋጾኦ