Posts

ፍቼ - ጨምበላላ፣ እሥራቶች፣ ሲአንና የዞኑ አስተዳደር

Image
New አባሎቹና ደጋፊዎቹ እንዲሁም ሌሎችም የሕብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ የሲዳማ ዞን ወረዳዎች ውስጥ እየታሠሩ እንደሚጉላሉ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ አስታወቀ፤ የታሠሩት በሕገወጥ ተግባር ላይ በመሠማራታቸው ነው ሲል ዞኑ ይናገራል፡፡ በሲዳማ ዞን ሃያ አንዱም ወረዳዎች ውስጥና በሃዋሣ ከተማ በርካታ አባሎቻቸው፣ ደጋፊዎቻቸውና ሌሎችም የሕብረተሰብ ክፍሎች እየታሠሩ መሆኑን የነገሩን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶ/ር ሚሊዮን ቱማቶ ናቸው፡፡ ነሐሴ 9 ቀን 2004 ዓ.ም ከተከበረው ፍቼ ተብሎ የሚታወቀው የዘመን መለወጫ በዓልና እርሱንም ተከትሎ በዋለው ጨምበላላ ባሕላዊ ጨዋታ ወቅት እንዲሁም ከዚያም በኋላ እሥራቱ መቀጠሉን የሚናገሩት አቶ ሚሊዮን የፓርቲያቸው ሰዎችና ደጋፊዎችም ሲዳማ ክልል እንዲሆንና ሃዋሣም ቻርተርድ ሜትሮፖሊታን እንድትሆን ጠይቀው እንደነበረ አቶ ሚሊዮን ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ በፍቼ በዓል ወቅት ከድርጅታቸው ሰዎች ወገን የተነሣ አንዳችም ችግር እንዳልነበረ ገልፀዋል፡፡ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ በፍቼ ጨምበላላ በዓል ወቅት የታሠሩ ሰዎች እንደነበሩና ብዙዎቹ በዋስ መለቀቃቸውን አመልክተዋል፡፡ እሥራቱ የተካሄደው ፀረ-ሠላም አድራጎት ሲፈፅሙ በነበሩ ሰዎች ላይ እንደነበረ የጠቆሙት አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ጉዳዩ በፍርድ ቤት የተያዘ ነው በሚል ሰዎቹ የተከሰሱባቸውን ጥፋቶች ለመግለፅ አልፈቀዱም፡፡ አንድ በዞኑ ውስጥ የሚኖሩ የሲአን አባል ግን ሰዎቻቸው ሰው አክባሪና ሰላማዊም እንደነበሩ፤ በበዓሉ ወቅትም የራሣቸውን ባህል በዘፈንና በጭፈራ ከማሞገስ ያለፈ ነገር አለመፈፀማቸውን ገልፀው እንዲህ ዓይነቱ አድራጎት የድርጅታቸው ላይ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ ማዋከብ አካል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ዘገባ

አቶ ኃይለማርያም፤ “ሜዳውም ፈረሱም ያው…” ታድያ በቅጡ ይጋልቡ!

Image
አቤ ቶኪቻው   ኃይለማርያም ደሳለኝ በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ወንበር ላይ ለመቀመጥ ቤተመንግስቱ በራፍ ላይ ቆመዋል። ለነገሩ እንኳ ሰውየው ደጃፍ ላይ ከቆሙ ቆይተዋል። ነገር ግን የኢህአዴግ ሰዎች “አናስገባም ሰርገኛ እደጅ ይቆይ…” ብለው ደጅ ሲያስጠኗቸው ሰነባበቱ። ይገበሉ ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ቢያንስ ኢቲቪ እና የመንግስት “ባሉካዎች” የጠቅላይ ሚኒስሩን ሞት በሰሙ በሁለት እና ሶስት ቀናት ውስጥ ነበር። ነገር ግን ይኸው ዛሬም ገና ፓርላማው ጠቅላይነታቸውን እስኪያፀድቅላቸው እንደ ቆሎ ተማሪ ደጅ መቆም ግዴታቸው ሆኗል። አቶ ሀይለማሪያም የኢህአዴግ ሊቀመንበርነትን ስልጣን ከያዙ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ “ሲሲቲቪ” ለተበለ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል “የእኔ አመራር የጋራ አመራር መርህን የተከተለ ነው” ካሉ በኋላ፤ “እንደሚታወቀው የመለስም አመራር ለግለሰብ የበላይነት ቦታ የማይሰጥ የቡድን ስራ የጎላበት አመራር ነበር” ብለው የማናውቀውን ነገር ነግረውናል። እውነቱን ለመናገር እኛ የምናውቀው አቶ መለስ “ሁሉን ቻይ” የነበሩና ሁልገዜም ብቻቸውን እንጂ በጋራ ሲሰሩ አላየንም። እርግጥ ደንብ ነውና ሙትን ሲያነሱ ደግ ደጉን ነው። ስለዚህ ስለ መለስ የሚያወሩት በሙሉ ፅቡቅ ፅቡቁን ቢሆን ግድ የለም… መምህር ኃይለማሪያም ሆይ መለስን ለአሁኑ እንተዋቸው እና በእርስዎ ጉዳይ እናውጋ… እናልዎ… አሁን ሜዳው ሜዳውም ፈረሱም በእጅዎ ነው። እንግዲህ በቅጡ መጋለብ የእርስዎ ፈንታ ነው። መምህር ሆይ ይቅርታ አንድ ጊዜ ወደ መለስ መለስ እንበልና አንድ ነገር ሹክ ልበልዎትማ ባለፈው ጊዜ የመለስ ለቅሶ ላይ ጥቁር በጥቁር ለብሶ “እንባ የተራጨው” ህዝቡ ሁላ ከኢህአዴግ ጎን ነው ስለዚህ እንዳሻኝ እሆናለሁ ብለው እንዳይሸወዱ… ልብ ያድርጉልኝ “እንባ የተራጨው” የምትለዋ ቃል ራሱ

Berhane back, Sidama needs coach

Image
With less than a month before the new season’s kick-off, Sidama Coffee does not have a coach. Three coaches are said to be on the short list  at Sidama Cofee. After finishing 8th last season, former head coach Zelalem Shiferaw left Sidama Coffee to join National League side Sebeta Town. Now while many teams have already started practicing Sidama must still find a coach.    Meanwhile, Berhane Gebregzabher is back in the picture as head coach of Ethiopian Water Sport club after years of absence from the Ethiopian Premier League The former Rental Houses, Insurance and Ethiopian Coffee clubs’ head coach Berhane G/Egziabher had been out in the woods for years going down to National League sides notably Burayu town and Chefe Donsa. Following Mekonen’s walk out from the club newly promoted to the upper tier Water Sport was looking for an ideal replacement they could afford.   Thus, Berhane landed the job to everyone’s surprise. Known for relying on finesse rather than strengt

ተቃዋሚዎች ኢሕአዴግ ያቀረበው የትብብር ጥሪ አሳታፊ እንዲሆን አሳሰቡ

Image
New በየማነ ናግሽ የኢሕአዴግ ምክር ቤት ባለፈው ቅዳሜ ስብሰባውን አጠናቆ አዲሱን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ከመረጠ በኋላ፣ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ በሰላማዊ መንገድ ከሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎች ጋር መተባበር እንደሚፈልግ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ጥሪውን በበጎ ጎኑ የተመለከቱ ተቃዋሚዎች ለተግባራዊነቱ ኢሕአዴግ ቁርጠኛ እንዲሆንና “የጋራ ምክር ቤት” በሚል ብቻ የተወሰነ እንዳይሆን አሳሰቡ፡፡ ተቃዋሚዎች በታላቁ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈት አብረው ማዘናቸውን የገለጸው የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣ የአገሪቱን የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ለማጠናከር በሚያግባቡ የተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት ጥሪ አቅርቧል፡፡ በተለይ ደግሞ መጪውን የአካባቢና የአዲስ አበባ ከተማ ምርጫ በተመለከተ ሒደቱ ነፃና ፍትሐዊ ይሆን ዘንድ ከተቃዋሚዎች ጋር ለመመካከር ዝግጁ መሆኑን ኢሕአዴግ የገለጸ ሲሆን፣ “በጋራ ምክር ቤቱ” አማካይነት ማለቱ ግን ተቃዋሚዎችን አላስደሰተም፡፡ በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የኢዴፓ ሊቀመንበር አቶ ሙሼ ሰሙ፣ ኢሕአዴግ ያቀረበውን የመነጋገርና የመተባበር ጥሪ በተለይ ተነሳሽነት መውሰዱን አድንቀው፣ ላለፉት 21 ዓመታት ሲታገሉለት የነበረና የሚጠብቁት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ጉዳዩ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውም ጭምር መሆኑን ገልጸው፣ ኢሕአዴግ እንደተለመደው ሰጪና ከልካይ የሚያደርጉ ቅድመ ሁኔታዎችን እንዳያስቀምጥ ግን ይጠይቃሉ፡፡ ሥልጣን ከሕዝብ የሚመነጭ መሆኑን የሚያምኑት አቶ ሙሼ፣ ከኢሕአዴግ ጋር መነጋገር የሚፈልጉት ሥልጣን ለመጋራት ሳይሆን በሕገ መንግሥቱ የተቀመጡ ዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ መሆኑን በዋናነት ይገልጻሉ፡፡ ነፃና ገለልተኛ ተቋማት የሚፈጠሩበት ሁኔታ ማመቻቸት፣ ፖለቲካዊ ምኅዳሩ የሚሰፋበት፣

ኢሕአዴግ የመንግሥት ኃላፊዎችን የሥልጣን ዘመን በአሥር ዓመት ገደበ

Image
New •    አቶ ኃይለ ማርያም ዓርብ በፓርላማ ሹመታቸው ይፀድቃል በዘካሪያስ ስንታየሁ በኢሕአዴግ በወጣው የመተካካት ፖሊሲ መሠረት የመንግሥት ኃላፊዎች የሥልጣን ዘመን በአሥር ዓመት መገደቡ ተገለጸ፡፡ በመሆኑም ኢሕአዴግ ከሁለት ዓመት በፊት ይፋ ባደረገው የመተካካት ፖሊሲው የጠቅላይ ሚኒስትሩና የሚኒስትሮች የሥልጣን ዘመን ሁለት የምርጫ ዘመን መሆኑ ታውቋል፡፡ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት የኢሕአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦን እንዳስታወቁት፣ የመተካካቱን መርሆች መነሻ በማድረግ በኢሕአዴግ የተወሰኑ ውሳኔዎች አሉ፡፡ ‹‹የፓርቲ አመራር ሆኖ ለመቀጠል ዕድሜ ነው ከፍተኛ ጣሪያ የተደረገው፡፡ በፓርቲው ፖሊሲ መሠረት አንድ ሰው እስከ 65 ዓመት ድረስ ቢሠራ ብዙ ችግር የለም ብለን እንስማማለን፤›› ብለዋል፡፡ አንድ የመንግሥት ኃላፊ ሁለት የምርጫ ዘመን የማገልገል ዕድል ቢያገኝ ይጠቅማል ብለን እናምናለን ያሉት አቶ በረከት፣ በሕዝብ ቢመረጥም እንኳን ከሁለት የምርጫ ዘመን በላይ በሥልጣን ላይ መቆየት የለበትም የሚል የፓርቲ ውሳኔ መኖሩን አስታውቀዋል፡፡ በሕገ መንግሥቱ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥልጣን ዘመን ገደብ ባይመቀጥለትም፣ ኢሕአዴግ በመተካካት ፖሊሲው መሠረት ለመንግሥት የሥልጣን ኃላፊነቶች የሥልጣን ዘመን አስቀምጧል፡፡ በተለይም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥልጣን ዘመን ከአሥር ዓመት በላይ እንዳይዘል ኢሕአዴግ መስማማቱን አስታውቋል፡፡ ሆኖም ግን ስምምነቱ ወደፊት በሕግ ደረጃ ስለመውጣቱ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ አቶ በረከት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥልጣን ዘመን በተጨማሪ የሌሎች ሚኒስትሮች የሥልጣን ዘመን በተመሳሳይ በአሥር ዓመት እንዲገደብ ኢሕአዴግ መስማማቱን ገል