Posts

Beauties in South Ethiopia, Sidama Zone

Image
This week I have been to Bensa Daye Woreda in Sidama Zone and I took some pictures (Even though I am not a professional photographer,I tried my best to do it). Bensa Daye is some 135 km far away from Awassa. Naturally Bensa Daye is the source of Ethiopian coffee and other beautiful fruits like banana etc. Tabour Terara ( Mount Tabour) just 5 km away from Awassa Large Cattle field near Aleta Wondo, about 50 km away from Awassa Sidama Cultural Hats. According to the experts these hats have 50 up to 100 years life span. Surprising!!! Inset (False Banana) is the main edible plant in the whole parts of Southern region. It is evergreen plant. If a family has no any of it in its garden, that family is said to be  extremely poor in our culture. In my experience, I know many families who have no any  “Inset”  in their garden, that mean there are many poor families in the region. I am not talking about the poorness relative to the world but about the poorness of the people am

Tesfaye's story

Image
His Story Sidama, Soccer, and Chickens (watercolor crayon) Over the Summer, Tesfaye has been sharing his story. We've heard snippets since he's come home, but over the course of two months, we took the time to be intentional about officially documenting his memories. Some memories have sadly already been forgotten.  It is important to preserve as much as we can about his early years and his first home.  A year ago, he would have remembered more, but he lacked the language to communicate and he wasn't emotionally ready to share.  He is sadly realizing he is starting to forget.  He is mature enough to recognize the importance of capturing his memories in a book.  He desperately wants to remember. This Summer he has been pouring out his heart, and very proudly telling his tale.  His story is told in snippets, captured in his voice - a sweet broken English - him talking while I frantically type, wanting to capture each tale in his own voice.  The more

አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ

Image
New አዲስአበባ፣መስከረም5 2005 (ኤፍቢሲ) የኢህአዴግ ምክር ቤት አርብና  ቅዳሜ  ባደረገው መደበኛ  ሰብሰባው የግንባሩን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር መረጠ ። ምክር ቤቱ   አቶ  ሀይለማሪያም ደሳለኝን  የግንባሩ ሊቀመንበር አድርጎ  የመረጠ  ሲሆን ፥  አቶ  ደመቀ መኮንንን  ደግሞ በምክትል ሊቀመንበርነት መርጧል ። የምክር ቤቱ መደበኛ ሰብሰባ ውሳኔዎችን በተመለከተ ፓርቲው  ማምሻውን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ  ቅዳሜ ከሰዓት  በኋላ  በተደረገው  የአመራር  ምርጫ  አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ከቀረቡት ሶሰት እጩዎች  መካከል ሙሉ  ድምፅ  በማግኘት ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል ። በመግለጫው ላይ እንደተመለከተውም የአመራር  ምርጫው ከመካሄዱ በፊት  የኢህአዴግ ምክር ቤት አባላት ቀደም ሲል ፓርቲው ባስቀመጠው የመተካካት እቅድ መሰረት ምርጫው እንዲካሄድ  ተስማምተዋል ። በቀደመው አመራር የተጀመረው  ትግል የሚቀጥለው የተለያዩ  ትውልዶች ተቀበብለውት እንደሆነ በማስመርም  የህዳሴው አመራር ሙሉ  በሙሉ  ከአዲሱ  ትውልድ  እንዲሆን  በመወሰን እጩዎች እንዲቀርቡ መደረጉን ነው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና  የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ በረከት ስምዖን ያስረዱት  ። አቶ በረከት በኢህአዴግ አሰራርም  አሁን በሊቀመንበርነትና በምክትል ሊቀመንበርነት የተመረጡት አመራሮች የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና ምክትል  ጠቅላይ ሚኒስትር  እንደሚሆኑም አመልክተዋል ። አዲሱ ጠቅላይ  ሚኒስትርም በአገሪቱ  ህገ በመንግሰት መሰረት  ካቢኒያቸውን ማዋቀር እንደሚችሉ የገለፁት አቶ በረከት ፥  አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝም ከፓርቲያቸው ጋር በመመካከር ካቢኒያቸውን መልሰው ሊያዋቅሩም ሆነ ሊያስቀጥሉ እንደሚችሉ ነ

ኢህአዴግ “የፓርቲውን ሊ/መንበር በምስጢር መያዝ ባህሌ ነው!” እንዳይለን

“የስዊድን ጋዜጠኞችስ ተፈቱ! የእኛስ?” (የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኛ) “ጠ/ሚኒስትር ለመሾም ምህላ እንጂ ስብሰባ ምን ይሰራል?” (ሽማግሌ ጐረቤቴ) አዲስ ዓመት እንዴት ነበር? (ከዋጋ ንረቱ ውጭ ማለቴ ነው) እኔ የምለው … ለአውዳመቱ  በግ ስንት እንደገባ ሰማችሁ አይደል? … በግ ነጋዴውን ጠጋ ብላችሁ ስትጠይቁት ምን ይላችኋል መሰላችሁ? “24 ውሰደው!” ግራ ይገባችሁና “ምንድነው የምትለው?” ስትሉት “ሰምተሃል!” ብሎ ሊያሾፍባችሁ ይሞክራል፡፡ (“ሼፉ” ፊልም ላይ እንዳለችው ገፀባህርይ) “አትሸጥም እንዴ?” ትሉታላችሁ ኮስተር ብላችሁ! “በቃ ከ23 ውሰደው!” ይላችኋል - ፍርጥም ብሎ፡፡ ምን ማለት መሰላችሁ? 2300 ብር ማለቱ ነው፡፡ ይታያችሁ … አንድ በግ በ2300 ብር! ለነገሩ በጉ እንኳን ሊቀር ይችላል፡፡ የማይቀረው ምን መሰላችሁ? የጤፉ ነገር ነው፡፡ ጤፉ ሊቀር ይችላል የሚባል አይደለም (አበሻ ምን ሊበላ?) በአሁኑ አካሄድ ግን ለእነ ጤፍ ምትክ ካልፈጠርንላቸው የምንከርም አልመሰለኝም! ከእነሩዝ ጋር ዝምድና ብንፈጥር ነው የሚሻለን፡፡ (የቻይና ደጀ-ጠኚ አደረግኸን ካላላችሁኝ በቀር) መቼም ጤፍ ተወደደ ብለን የረሃብ አድማ አናደርግም! ሳንነጋገር እየራበን? የምን አድማ! ይሄን ፅሁፍ እያጠናቀርኩኝ ሳለ በኢቴቪ “ሥነፆታ” በተባለ ፕሮግራም በዓሉን አስመልክቶ ተሞክሮአቸውን የሚያጋሩ ዘመናዊ ባልና ሚስት ቀርበው ነበር፡፡ ሚስት ሲናገሩ፤ ዳቦውንም ጠላውንም ራሳችን ካላዘጋጀነው ልንል አይገባንም፤ ሲሉ በሰጡት ምክራዊ አስተያየት “እኛ ለምሳሌ ዳቦ አንጋግርም… outsource ነው የምናደርገው… ለሌላው ሰው የሥራ እድል መፍጠር አለብን” ብለዋል፡፡ (ውጭ አስጋግረን ነው የምናመጣው ማለታቸው መሰለኝ) ያለው ማማሩ አሉ! ዕድሜ ለNGO! ያልፈጠረልን ቃል

የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተቀዛቅዝዋል

ከጠ/ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ዜና ዕረፍት ወዲህ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ስራ  እንደተቀዛቀዘ ባለጉዳዮች የተናገሩ ሲሆን፤ከፍተኛ ባለስልጣኖች ለስብሰባ አዲስ አበባ መምጣታቸው እና የተተኪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሹመት ሳይካሄድ መቆየቱ ተጨማሪ ምክንያቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ በየመስሪያ ቤቱ የመንግስት ስራ መቀዛቀዙን የሚገልፁ ባለጉዳዮች፤ በተለይ የከፍተኛ ባለስልጣናትንና የቢሮ ሃላፊዎችን ውሳኔ የሚጠይቁ ጉዳዮች በቀጠሮ እንደተጓተቱባቸው ተናግረዋል፡፡ የጠ/ሚኒስቴር መለስ ዜና እረፍት ከተሰማበት ወቅት አንስቶ እስከ እለተ ቀብር ድረስ በአገሪቱ የነበረው የሀዘን ስሜትና ድባብ ከፍተኛ ቢሆንም፤ የመንግስት ሥራ ሳይቋረጥና ቢሮዎች ሳይዘጉ ቀጥለዋል፤ ሆኖም ስራዎች መቀዛቀዛቸው አልቀረም ይላሉ ባለጉዳዮች፡፡ በቀብር ስነስርዓቱ ማግስት ጊዜያዊ ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በሰጡት መግለጫ፤ ሁሉም ሰው በቁጭትና በተጨማሪ ብርታት ወደ ስራ እንዲመለስ ማሳሰባቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በበርካታ ቦታዎች መደበኛ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ይሁንና በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ የመንግስት ቢሮዎች፤ ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩ ጉዳዮች ውሳኔ ሳያገኙ በቀጠሮ እንደተራዘሙባቸው የሚገልፁ ባለጉዳዮች፤ በርካታ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቢሮዋቸው እንደማይገኙ ተናግረዋል፡፡ በርካታዎቹ ባለሥልጣናት ሰሞኑን የኢህአዴግ ምክር ቤት ለሚያካሂደው ስብሰባ አዲስ አበባ መግባታቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ በዚህ ምክንያት ብዙ ባለስልጣናት በቢሯቸው እንዳይገኙ አንድ ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብሏል፡፡ 180 አባላትን የያዘው የኢህአዴግ ምክር ቤት የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱን በ