Posts

ኢህአዴግ “የፓርቲውን ሊ/መንበር በምስጢር መያዝ ባህሌ ነው!” እንዳይለን

“የስዊድን ጋዜጠኞችስ ተፈቱ! የእኛስ?” (የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኛ) “ጠ/ሚኒስትር ለመሾም ምህላ እንጂ ስብሰባ ምን ይሰራል?” (ሽማግሌ ጐረቤቴ) አዲስ ዓመት እንዴት ነበር? (ከዋጋ ንረቱ ውጭ ማለቴ ነው) እኔ የምለው … ለአውዳመቱ  በግ ስንት እንደገባ ሰማችሁ አይደል? … በግ ነጋዴውን ጠጋ ብላችሁ ስትጠይቁት ምን ይላችኋል መሰላችሁ? “24 ውሰደው!” ግራ ይገባችሁና “ምንድነው የምትለው?” ስትሉት “ሰምተሃል!” ብሎ ሊያሾፍባችሁ ይሞክራል፡፡ (“ሼፉ” ፊልም ላይ እንዳለችው ገፀባህርይ) “አትሸጥም እንዴ?” ትሉታላችሁ ኮስተር ብላችሁ! “በቃ ከ23 ውሰደው!” ይላችኋል - ፍርጥም ብሎ፡፡ ምን ማለት መሰላችሁ? 2300 ብር ማለቱ ነው፡፡ ይታያችሁ … አንድ በግ በ2300 ብር! ለነገሩ በጉ እንኳን ሊቀር ይችላል፡፡ የማይቀረው ምን መሰላችሁ? የጤፉ ነገር ነው፡፡ ጤፉ ሊቀር ይችላል የሚባል አይደለም (አበሻ ምን ሊበላ?) በአሁኑ አካሄድ ግን ለእነ ጤፍ ምትክ ካልፈጠርንላቸው የምንከርም አልመሰለኝም! ከእነሩዝ ጋር ዝምድና ብንፈጥር ነው የሚሻለን፡፡ (የቻይና ደጀ-ጠኚ አደረግኸን ካላላችሁኝ በቀር) መቼም ጤፍ ተወደደ ብለን የረሃብ አድማ አናደርግም! ሳንነጋገር እየራበን? የምን አድማ! ይሄን ፅሁፍ እያጠናቀርኩኝ ሳለ በኢቴቪ “ሥነፆታ” በተባለ ፕሮግራም በዓሉን አስመልክቶ ተሞክሮአቸውን የሚያጋሩ ዘመናዊ ባልና ሚስት ቀርበው ነበር፡፡ ሚስት ሲናገሩ፤ ዳቦውንም ጠላውንም ራሳችን ካላዘጋጀነው ልንል አይገባንም፤ ሲሉ በሰጡት ምክራዊ አስተያየት “እኛ ለምሳሌ ዳቦ አንጋግርም… outsource ነው የምናደርገው… ለሌላው ሰው የሥራ እድል መፍጠር አለብን” ብለዋል፡፡ (ውጭ አስጋግረን ነው የምናመጣው ማለታቸው መሰለኝ) ያለው ማማሩ አሉ! ዕድሜ ለNGO! ያልፈጠረልን ቃል

የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተቀዛቅዝዋል

ከጠ/ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ዜና ዕረፍት ወዲህ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ስራ  እንደተቀዛቀዘ ባለጉዳዮች የተናገሩ ሲሆን፤ከፍተኛ ባለስልጣኖች ለስብሰባ አዲስ አበባ መምጣታቸው እና የተተኪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሹመት ሳይካሄድ መቆየቱ ተጨማሪ ምክንያቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ በየመስሪያ ቤቱ የመንግስት ስራ መቀዛቀዙን የሚገልፁ ባለጉዳዮች፤ በተለይ የከፍተኛ ባለስልጣናትንና የቢሮ ሃላፊዎችን ውሳኔ የሚጠይቁ ጉዳዮች በቀጠሮ እንደተጓተቱባቸው ተናግረዋል፡፡ የጠ/ሚኒስቴር መለስ ዜና እረፍት ከተሰማበት ወቅት አንስቶ እስከ እለተ ቀብር ድረስ በአገሪቱ የነበረው የሀዘን ስሜትና ድባብ ከፍተኛ ቢሆንም፤ የመንግስት ሥራ ሳይቋረጥና ቢሮዎች ሳይዘጉ ቀጥለዋል፤ ሆኖም ስራዎች መቀዛቀዛቸው አልቀረም ይላሉ ባለጉዳዮች፡፡ በቀብር ስነስርዓቱ ማግስት ጊዜያዊ ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በሰጡት መግለጫ፤ ሁሉም ሰው በቁጭትና በተጨማሪ ብርታት ወደ ስራ እንዲመለስ ማሳሰባቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በበርካታ ቦታዎች መደበኛ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ይሁንና በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ የመንግስት ቢሮዎች፤ ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩ ጉዳዮች ውሳኔ ሳያገኙ በቀጠሮ እንደተራዘሙባቸው የሚገልፁ ባለጉዳዮች፤ በርካታ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቢሮዋቸው እንደማይገኙ ተናግረዋል፡፡ በርካታዎቹ ባለሥልጣናት ሰሞኑን የኢህአዴግ ምክር ቤት ለሚያካሂደው ስብሰባ አዲስ አበባ መግባታቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ በዚህ ምክንያት ብዙ ባለስልጣናት በቢሯቸው እንዳይገኙ አንድ ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብሏል፡፡ 180 አባላትን የያዘው የኢህአዴግ ምክር ቤት የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱን በ

ምክር ቤቱ የሕዳሴ ጉዞን በሚያስቀጥሉ አቅጣጫዎችና ስልቶች ላይ ከስምምነት ደረሰ

Image
አዲስ አበባ፡- የኢህአዴግ ምክር ቤት ሕዝቡን በማሳተፍ የተጀመረውን ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ የሕዳሴ ጉዞ ለማስጠቀል በሚያስችሉ አቅጣጫዎችና ስልቶች ላይ ከስምምነት ላይ ደረሰ። የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ለዝግጅት ክፍላችን እንዳስታወቀው፤ የሕዳሴውን ጉዞ መላው የግንባሩ አባላትና የትግሉ ደጋፊዎች እንዲሁም የለውጡ ባለቤቶችና ተጠቃሚዎች የሆኑት መላው ኢትዮጵያውያንን በማሣተፍ ማስቀጠል እንደሚገባ ምክር ቤቱ ስምምነት ላይ ደርሷል። ትናንት የተጀመረው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ለታላቁ የድርጅቱ ሊቀመንበር ለክቡር አቶ መለስ ዜናዊ የሕሊና ፀሎት በማድረግ ተከፍቷል። ከአራቱ ብሔራዊ ድርጅቶች በእኩል ድምፅ የሚወከሉት የምክር ቤቱ አባላት ምልዓተ ጉባኤ መሟላት መሠረት በማድረግ ከሕሊና ፀሎቱ በኋላ ለምክር ቤቱ በመወያያነት በቀረቡት አጀንዳዎች ዙሪያ ተወያይቶ በማፅደቅ ሥራውን ጀምሯል። በዚሁ መሠረት በሁለቱ ቀናት ምክር ቤቱ ለመወያየት ከያዛቸው አጀንዳዎች መካከል በቅድሚያ፡-የሚመክረው የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ተግባራዊ ልዕልናን በማረጋገጥ የመለስ/ኢህአዴግን ራዕይ ለማሳካት እንረባረብ በሚል ርዕስ የተዘጋጀና በታላቁ መሪና በድርጅቱ አመራር የተገኙትን ስኬቶች ማስቀጠል በሚቻልባቸውና ቀጣይ ፈተናዎችን ለመቋቋም በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ነው። ከዚህ በማስቀጠልም ታላቁ መሪ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ ተዘጋጅቶ በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውይይት ተደርጎበት የነበረው የአመራር ግንባታና የሕዳሴው ጉዞ በሚል ርዕስ ኪራይ ሰብሳቢነትን ከምንጩ ለማድረቅና የሕዝቡን ዘላቂ ጥቅምና ተጠቃሚነት በሕዝቡ የተደራጀና ቀጣይነት ያለው ንቅናቄና ተሣትፎ ማረጋገጥ ይቻል ዘንድ እና ከዚሁ ሂደት ጠንካራ የድርጅትና መንግሥት አመራር መፍጠር በሚቻልባቸው የአሠራር የአደረጃ

የኢህአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳች ላይ እየመከረ ነው

አዲስአበባ፣መስከረም4 2005 (ኤፍቢሲ) ምክር ቤቱ  በመጀመሪያ  ቀኑ  የጉባኤው ውሎ ከጠቅላይ  ሚኒስትር  መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ በአገራችንና  በአከባቢው እንዲሁም በሌሎች የዓለም ክፍሎች የተፈጠረውን ሁኔታ  ገምግሟል ። ከዚህ በመነሳትም በአገራችን መካሄድና ይበልጥ መጠናከር ያለበትን የልማታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት  ግንባታን አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ መክሯል ። መላውን የድርጅቱን አባላትና የትግሉን ደጋፊዎች እንዲሁም የለውጡ ባለቤቶች እና ተጠቃሚዎች የሆኑትን መላውን የኢትዮጵያ ህዝቦችን በማሳተፍ የተጀመረውን ልማታዊና ዲሞክራሲያዊ የህዳሴ ጉዞ ለማስቀጠል በሚያስችሉ አቅጣጫዎችና ስልቶች  ዙሪያም በመወያየት ከስምምነት ደርሷል ። የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ ምክር ቤት እስከ ነገ  በሚቆየው ስብሰባ የድርጅቱን ሊቀመንበር ይሰይማል። በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ያካሄደውን አጭር ግምገማና የ2005 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫዎች የሚመለከት ሰነድ በመመርመር ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ታውቋል። ምክር ቤቱ በአቶ መለስ ዜናዊ አመራርና በድርጅቱ የተጀመረውን የኢትዮጵያ ህዳሴ አጠናክሮ ለማስቀጠል የድርጅቱን የአመራር ግንባታ በተመለከተ የተዘጋጀውን ሰነድ በመመርመር መሰረታዊ አቅጣጫዎችን እንደሚያመላክትም የምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት  ለፋና ብሮድካሲትንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ላይ ጠቅሷል ። የኢሕአዴግ ምክር ቤት ከአራቱ አባል ድርጅቶች በእኩል የተሰየሙ 180 አባላት ያሉት ሲሆን በሁለት ጉባዔዎች መካከል የግንባሩ ከፍተኛ የሥልጣን አካል ሆኖ ያገለግላል ።

The Political Economy of the Sidama Regional Question-Overview

Image
By Hawassa Teessonke September 13, 2012 Today, the Sidama people are at a crossroads. Structural economic weaknesses and lack of economic transformation amid massive over population has left the majority of the population in abject poverty. Unemployment, particularly among the youth, and rural underemployment remain rampant. The continued economic marginalization amid relative improvements in political space since 1991 has been worsened by lack of capacity and good governance, corruption, and above all disempowering administrative arrangement that denied political voice to the majority of the population. The country has adopted bicameral administrative system since 1993. While the majority of the country is organized in a federal system in line with ethno-linguistic affiliations and delineations; over 45-50 ethnic groups in the South are forcefully lumped together under the Southern Ethiopia Peoples’ Region. Accordingly to the July 1,  2012 population estimate by t