Posts

በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገቱን ሊደግፍ የሚችል የቴክኖሎጂ ሽግግርና አቅም ለመገንባት እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች ውጤት አስገኝቷል ኣቶ ደሴ ዳልኬ

Image
አዲስ አበባ መስከረም 1/2005 በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገቱን ሊደግፍ የሚችል የቴክኖሎጂ ሽግግርና አቅም ለመገንባት እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች ውጤት እያሰገኘ መሆኑን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ገለጹ። ሚኒስትሩ አቶ ደሴ ዳልኬ ለኢዜአ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ውጤታማ የሆኑ የውጭ ቴክኖሎጂዎችን በፍጥነት የመማር የማላማድ እና የመጠቀም አቅሟም በየጊዜው እየተሻሻለ ይገኛል።  የአገሪቱን ልማት ሊደግፍ የሚችል ውጤታማ የሆነ ቴክኖሎጂ በማፈላለግና ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ሂደት እስካሁን የተኙት ውጤቶችም አበረታች መሆናቸውን ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ሳይንስና ቴክኖሎጂ በድህነት ቅነሳና ላይ ያለውን አስተዋጽኦ በመገንዘብ ባለፉት ሁለት አመታት ዘርፉ የአገሪቱን ኢኮኖሚ የሚደግፍ እንዲሆን የተደረገው ጥረትም ስኬታማ እንደነበር ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ለመሰለፍ እያደረገች ካለው ጥረት ጋር የሚጣጣም የሳይንስና ቴክኖሎጂ አቅም እንዲገነባ ልዩ ትኩረት መሰጠቱንም ሚኒስትሩ አስረድተዋል። አዳዲስ ቴክኖሎጂን የማፈላለግ የማስገባትና የመጠቀም አቅምን ለማዳበር የሚያስችሉ የአሰራር ስርዓቶች በመዘርጋታቸው ቴክኖሎጂን በማዛመድ በመቅዳትና ረገድ ጥሩ ጅምሮች እየታዩ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።  እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ በተለይ ባለፉት ሁለት አመታት ቴክሎጂን አስመስሎ በመስራት ከውጭ የሚገቡትን በአገር ውስጥ በማስቀረት ረገድ ጠንካራ አቅም እየተገነባ ነው። የአገሪቱ ኢኮኖሚ የሚፈልገውን የላቀ ክህሎት ያላቸው ቴክኒሻኖች፣መሃንዲሶችና ሳይንቲስቶች ለማፍራት የሚያግዙ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋማት የማደራጀቱ ስራም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የተማሪዎች ቅበላ ከአገሪቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰው ሃይል ልማት

የሀዋሳን ሀይቅ ከጥፋት ለመታደግ ድምፃችንን እናሰማ

Image
ዛሬ መስከረም 1 ቀን 2005 ዓ / ም ሐዋሳ የፍቅር ሀይቅና አሞራ ገደልን የመጎብኘት ዕድል አጋጥሞናል፡፡ ባለፈው ዓመት ሚያዚያ 2004 ዓ / ም የሀዋሳ ሀይቅ ጠንቅ የሆኑ ችግሮች እንዲወገዱ አስተያየት ሰንዝሬ እንደነበር ይታወቃል፡፡ነገር ግን ዘንድሮም ይሄው ተመሳሰይ ችግር ምንም ለውጥ አልታየበትም ለአብነትም ያህል በቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙ መዝናኛ ካፌዎች ዘመናዊ የሚመስል የቆሻሻ ማጠራቀሚያ /Dust Bin/ አስቀምጠዋል፡፡ለኔ የገረመኝ በፍቅር ሀይቅ በኩል በእግረኛ መንገድ አካባቢ ባለ አስር ሊትር ቢጫ የዘይት ጄሪካኖች ወገባቸው ተቆርጦ ለደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚነት ተቀምጠዋል ይህ ሙከራ የማይጠላ ቢሆንም ፋይዳው ሲታሰብ ምንም የጠቀመው ነገር የለም፡፡ለምንድንው ግቢው የልማት ፅ / ቤት አለው ከተባለ ለምን ስርዓት ያለው የቆሻሻ መጣያዎችን በየቦታው ተቀምጠው አገልገሎት እንዲሰጡ የማያደርገው ? በአጠቃላይ እተሰራ ያለው ስራ ሀይቁን አመጥነውም፡፡ በየሀይቁ ዳር ሶስት እና አራት በጥቅም ላይ የዋሉ የውሀ መጠጫ ላስቲኮች፣ የሲጋራና የብስኩት መቅለያዎች፣የጫት ገራባና ጋዜጣዎች በየሀይቁ ዳር ተንሳፈው ታዝቤያለሁ፡፡ አስኪ አስቡት በቀን በትንሹ 20 የውሃ መጠጫ የያዙ ሰዎች የተጠቀሙበትን ላስቲክ በሀየቁ ዳር ቢጥሉ ከበርካታ ዓመታት በኋላ አላሙራ ተራራን የሚያክል ቆሻሻ ሊፈጠር ነው ማለት ነው፡፡ ፎቶ መላኩ ቀጥሎ ውደ አሞራ ገደል ጉዞ በእግር በማቋረጥ የተለመደውን አምስት ብር የደንቧን / የመግቢያ / ልከፍል ለምን ስራ እንደሚውል ስጠይቅ ለልማት ስራ ነው አሉኝ፣ለየትኛው ልማት ? ለአካባቢው ልማት አሉኝ አላለማችሁም ቆሻሻ እየተጣለ በትንሹ እንኳ ነገ ሀይቁ ከተበላሸ እናንተም ሰርታችሁ አትበሉም ሀዋሳም ያላት አይኗ ጠፋ ማለት ነው ስላቸው የሰለቻ

ሀገሪቱን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጋራ ይመሯታል ተባለ

Image
New ኢሳት ዜና:-በመስከረም ወር 2005 ዓ.ም የኢህአዴግ ምክር ቤት በአቶ መለስ ዜናዊ ምትክ በሚያካሂደው ምርጫ የሚመረጠው ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ድርጅቱን ለስድስት ወራት ብቻ በጋራ እንደሚመሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን የግንባሩ ጽ/ቤት ኃላፊ አስታወቁ፡፡ አቶ ሬድዋን ዛሬ ከወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የግንባሩ መተዳደሪያ ደንብ ቀጣዩ ጉባዔ ከሁለት እስከ ሁለት ዓመት ተኩል ባለው ጊዜ ውስጥ ይካሄዳል በሚለው መሰረት ቀጣዩ ጉባዔ ከስድስት ወራት በኃላ እንደሚካሄድ ጠቁመው እስከዚያ ከአራቱም አባል ድርጅቶች 45 ሰዎች በድምሩ 180 አባላት የተወከሉበት የግንባሩ ም/ቤት በተጓደሉት አባላት ምትክ ግንባሩን “በጋራ የሚመሩ” ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ይመርጣል ብለዋል፡፡ “ከስድስት ወራት በኃላ የግንባሩ ጉባዔ ሲካሄድ ሊቀመንበሩና ምክትል ሊቀመንበሩ ብቻ ሳይሆን የሥራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትም ሥልጣናቸውን ያስረክባሉ፡፡ከማንኛውም አባል ጋር ወርዶና የጉባዔው አባል ሆኖ ከተመረጠ ይመረጣል፡፡እስከዚያው ግን የሊቀመንበርነት ቦታ ተጓድሎአል፡፡ተጓደለውን ቦታ የሚመርጠው ጉባዔው ሳይሆን ምክርቤቱ በመሆኑ በዚሁ መሰረት በመስከረም ወር ይመርጣል፡፡ቀጣይ ስድስት ወር ሲሞላ አዲሱ ሊቀመንበር ሌላ የጉባዔ አባላት ይሆኑና እንደገና ምርጫ ተደርጎ የሚመረጡ ከሆነ ይመረጣሉ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሰሞኑን  የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ የሰሞኑ ጉባዔ ስላሳለፈው ውሳኔ ተጠይቀው በሰጡት ምላሸ “…የሁልጊዜም የድርጅቱ መሰረታዊ እምነት ሕዝቡን ወደተሻለ ደረጃ በመውሰድ ላይ ያነጣጠረ ፣የህዝቡን ሕይወት በመቀየር ላይ ያነጣጠረ፣የሕዝቡን ሕይወት በመቀየር መሰረታዊ የሆነውን ለውጥ በሃገሪቱ ለማምጣት መሰዋዕትነት መክፈል ላይ ያተኮረ ነው፡፡በመሆኑም

የአመት በዓል ገበያ ለብዙሀኑ ኢትዮጵያውያን የማይቀመስ ሆኖል

ጳጉሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አመት ዋዜማ አዲስ አበባ የፍርሃትና  የዝምታ ድባብ ሰፍሮባታል:: የአመት በዓል ገበያም ለብዙሀኑ ኢትዮጵያውያን የማይቀመስ ሆኖል:: በመርካቶና  በአዲሱ ገበያ አካባቢ ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ  እንደተመለከተው 50 ኪሎ ማኛ ጤፍ 1200 ብር ኩንታሉ 2400 ብር ጠቆር ያለው ጤፍና ሰርገኛ እንደ ደረጃው ከ1400 ብር እስከ  1800 ብር የኤልፎራ ዶሮ ብር 100 እየተሸጠ ሲሆን የሀበሻ  ዶሮ  በገበያ ላይ እንደ ኪሎው  ከመቶ ሀምሳ  እስከ  210 እየተሸጠ ነው:: አንድ  እንቁላል 2 ብር ከ50 ሳንቲም ሲሆን በግ ከ1300 እስከ  3500 ብር ነገር ግን በመርካቶ አካባቢ ግን ከዚህ ወደድ እንደሚል ዘጋቢያችን ገልፆልናል::  ቅቤ ከብር 150 እስከ 160 ሲሸጥ የሸኖ ለጋ ቅቤ ግን እስከ 200 ብር በመሸጥ ላይ ነው:: በሬ ከ15000 እስከ 20000 እየተሸጥ ነው::

Year of Incongruence

Change is the one theme that I admire devotedly. I often think that the root cause of many of the societal problems that I observe in our society is resistance to change. A person ready to change is a person with a confidence to leap forward in life, I even argue. It was with the sole objective of experiencing change that I get involved in an industry far from my career objective, business advisory. What I have identified in my over one year stay in the media industry is, however, that it is an environment of information but not knowledge, hard work but less recognition, overwork but meagre income, and visibility but not upward mobility. In thinking about the just-ended year, I came across many occasions that I worked hard to break myself. These were times that I had the most satisfaction out of life. Yet, they were all useless for they were accompanied by little more than a good feeling. For a boy who has grown in a family wherein outstanding works are awarded with jovial rec