Posts

የሀዋሳን ሀይቅ ከጥፋት ለመታደግ ድምፃችንን እናሰማ

Image
ዛሬ መስከረም 1 ቀን 2005 ዓ / ም ሐዋሳ የፍቅር ሀይቅና አሞራ ገደልን የመጎብኘት ዕድል አጋጥሞናል፡፡ ባለፈው ዓመት ሚያዚያ 2004 ዓ / ም የሀዋሳ ሀይቅ ጠንቅ የሆኑ ችግሮች እንዲወገዱ አስተያየት ሰንዝሬ እንደነበር ይታወቃል፡፡ነገር ግን ዘንድሮም ይሄው ተመሳሰይ ችግር ምንም ለውጥ አልታየበትም ለአብነትም ያህል በቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙ መዝናኛ ካፌዎች ዘመናዊ የሚመስል የቆሻሻ ማጠራቀሚያ /Dust Bin/ አስቀምጠዋል፡፡ለኔ የገረመኝ በፍቅር ሀይቅ በኩል በእግረኛ መንገድ አካባቢ ባለ አስር ሊትር ቢጫ የዘይት ጄሪካኖች ወገባቸው ተቆርጦ ለደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚነት ተቀምጠዋል ይህ ሙከራ የማይጠላ ቢሆንም ፋይዳው ሲታሰብ ምንም የጠቀመው ነገር የለም፡፡ለምንድንው ግቢው የልማት ፅ / ቤት አለው ከተባለ ለምን ስርዓት ያለው የቆሻሻ መጣያዎችን በየቦታው ተቀምጠው አገልገሎት እንዲሰጡ የማያደርገው ? በአጠቃላይ እተሰራ ያለው ስራ ሀይቁን አመጥነውም፡፡ በየሀይቁ ዳር ሶስት እና አራት በጥቅም ላይ የዋሉ የውሀ መጠጫ ላስቲኮች፣ የሲጋራና የብስኩት መቅለያዎች፣የጫት ገራባና ጋዜጣዎች በየሀይቁ ዳር ተንሳፈው ታዝቤያለሁ፡፡ አስኪ አስቡት በቀን በትንሹ 20 የውሃ መጠጫ የያዙ ሰዎች የተጠቀሙበትን ላስቲክ በሀየቁ ዳር ቢጥሉ ከበርካታ ዓመታት በኋላ አላሙራ ተራራን የሚያክል ቆሻሻ ሊፈጠር ነው ማለት ነው፡፡ ፎቶ መላኩ ቀጥሎ ውደ አሞራ ገደል ጉዞ በእግር በማቋረጥ የተለመደውን አምስት ብር የደንቧን / የመግቢያ / ልከፍል ለምን ስራ እንደሚውል ስጠይቅ ለልማት ስራ ነው አሉኝ፣ለየትኛው ልማት ? ለአካባቢው ልማት አሉኝ አላለማችሁም ቆሻሻ እየተጣለ በትንሹ እንኳ ነገ ሀይቁ ከተበላሸ እናንተም ሰርታችሁ አትበሉም ሀዋሳም ያላት አይኗ ጠፋ ማለት ነው ስላቸው የሰለቻ

ሀገሪቱን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጋራ ይመሯታል ተባለ

Image
New ኢሳት ዜና:-በመስከረም ወር 2005 ዓ.ም የኢህአዴግ ምክር ቤት በአቶ መለስ ዜናዊ ምትክ በሚያካሂደው ምርጫ የሚመረጠው ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ድርጅቱን ለስድስት ወራት ብቻ በጋራ እንደሚመሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን የግንባሩ ጽ/ቤት ኃላፊ አስታወቁ፡፡ አቶ ሬድዋን ዛሬ ከወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የግንባሩ መተዳደሪያ ደንብ ቀጣዩ ጉባዔ ከሁለት እስከ ሁለት ዓመት ተኩል ባለው ጊዜ ውስጥ ይካሄዳል በሚለው መሰረት ቀጣዩ ጉባዔ ከስድስት ወራት በኃላ እንደሚካሄድ ጠቁመው እስከዚያ ከአራቱም አባል ድርጅቶች 45 ሰዎች በድምሩ 180 አባላት የተወከሉበት የግንባሩ ም/ቤት በተጓደሉት አባላት ምትክ ግንባሩን “በጋራ የሚመሩ” ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ይመርጣል ብለዋል፡፡ “ከስድስት ወራት በኃላ የግንባሩ ጉባዔ ሲካሄድ ሊቀመንበሩና ምክትል ሊቀመንበሩ ብቻ ሳይሆን የሥራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትም ሥልጣናቸውን ያስረክባሉ፡፡ከማንኛውም አባል ጋር ወርዶና የጉባዔው አባል ሆኖ ከተመረጠ ይመረጣል፡፡እስከዚያው ግን የሊቀመንበርነት ቦታ ተጓድሎአል፡፡ተጓደለውን ቦታ የሚመርጠው ጉባዔው ሳይሆን ምክርቤቱ በመሆኑ በዚሁ መሰረት በመስከረም ወር ይመርጣል፡፡ቀጣይ ስድስት ወር ሲሞላ አዲሱ ሊቀመንበር ሌላ የጉባዔ አባላት ይሆኑና እንደገና ምርጫ ተደርጎ የሚመረጡ ከሆነ ይመረጣሉ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሰሞኑን  የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ የሰሞኑ ጉባዔ ስላሳለፈው ውሳኔ ተጠይቀው በሰጡት ምላሸ “…የሁልጊዜም የድርጅቱ መሰረታዊ እምነት ሕዝቡን ወደተሻለ ደረጃ በመውሰድ ላይ ያነጣጠረ ፣የህዝቡን ሕይወት በመቀየር ላይ ያነጣጠረ፣የሕዝቡን ሕይወት በመቀየር መሰረታዊ የሆነውን ለውጥ በሃገሪቱ ለማምጣት መሰዋዕትነት መክፈል ላይ ያተኮረ ነው፡፡በመሆኑም

የአመት በዓል ገበያ ለብዙሀኑ ኢትዮጵያውያን የማይቀመስ ሆኖል

ጳጉሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አመት ዋዜማ አዲስ አበባ የፍርሃትና  የዝምታ ድባብ ሰፍሮባታል:: የአመት በዓል ገበያም ለብዙሀኑ ኢትዮጵያውያን የማይቀመስ ሆኖል:: በመርካቶና  በአዲሱ ገበያ አካባቢ ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ  እንደተመለከተው 50 ኪሎ ማኛ ጤፍ 1200 ብር ኩንታሉ 2400 ብር ጠቆር ያለው ጤፍና ሰርገኛ እንደ ደረጃው ከ1400 ብር እስከ  1800 ብር የኤልፎራ ዶሮ ብር 100 እየተሸጠ ሲሆን የሀበሻ  ዶሮ  በገበያ ላይ እንደ ኪሎው  ከመቶ ሀምሳ  እስከ  210 እየተሸጠ ነው:: አንድ  እንቁላል 2 ብር ከ50 ሳንቲም ሲሆን በግ ከ1300 እስከ  3500 ብር ነገር ግን በመርካቶ አካባቢ ግን ከዚህ ወደድ እንደሚል ዘጋቢያችን ገልፆልናል::  ቅቤ ከብር 150 እስከ 160 ሲሸጥ የሸኖ ለጋ ቅቤ ግን እስከ 200 ብር በመሸጥ ላይ ነው:: በሬ ከ15000 እስከ 20000 እየተሸጥ ነው::

Year of Incongruence

Change is the one theme that I admire devotedly. I often think that the root cause of many of the societal problems that I observe in our society is resistance to change. A person ready to change is a person with a confidence to leap forward in life, I even argue. It was with the sole objective of experiencing change that I get involved in an industry far from my career objective, business advisory. What I have identified in my over one year stay in the media industry is, however, that it is an environment of information but not knowledge, hard work but less recognition, overwork but meagre income, and visibility but not upward mobility. In thinking about the just-ended year, I came across many occasions that I worked hard to break myself. These were times that I had the most satisfaction out of life. Yet, they were all useless for they were accompanied by little more than a good feeling. For a boy who has grown in a family wherein outstanding works are awarded with jovial rec

ኢህአዴግ በአዲሱ ዓመት ያሞላቅቀን!

“የፓርቲዬ ባህል አይፈቅድልኝም” የሚል ሰበብ አንቀበልም! በሀዘን ክፉኛ የጨፈገገንን ደባሪ ዓመት ዛሬ እንሸኘዋለን - እንዲህ ያለ ዓመት ተመልሶ እንዳይመጣ እየተመኘን (ኧረ ፀሎትና ምህላም ያስፈልገዋል!) ግን በ2004 ምን መዓት ነው የወረደው? ብቻ በዚሁ በቃችሁ ይበለን! አሁን ወደ ዕለቱ ወጋችን ልመልሳችሁ፡፡በዛሬዋ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ ሆኜ ምን እንዳማረኝ ታውቃላችሁ? በቃ … መሞላቀቅ፡፡ ግን ደግሞ በወላጅ ወይም በአያት አሊያም በፍቅረኛ አይደለም፡፡ እኔ መሞላቀቅ ያማረኝ በገዢው ፓርቲ ነው፡፡ (አሞላቆን ስለማያውቅ ይሆን?) በርግጥ ይሄ ጥያቄ የእኔ ብቻ አይደለም - የህዝብ ነው፡፡ ማስረጃ ካስፈለገም ፒቲሽን አሰባስቤአለሁ፡፡ እናም ኢህአዴግ እስኪበቃን ድረስ እንዲያሞላቅቀን እፈልጋለሁ፡፡ እየቀለድኩ እንዳይመስላችሁ… ከምሬ ነው፡፡ በቃ በአዲሱ ዓመት ሙልቅቅ ማለት አምሮኛል፡፡ እንደ ቦሌ ልጆች! እኔ የምለው… ኢህአዴግ እኛን ማሞላቀቅ ያቅተዋል እንዴ? ኧረ አያቅተውም፡፡ ዋናው ነገር የልብ መሻት ነው (When there is a will, there is a way እንዲል ፈረንጅ) መቼም አውራ ፓርቲያችን ሰበብ አያጣምና “የፓርቲያችን ባህል፤ ማሞላቀቅ አይፈቅድም” ሊለኝ ይችላል (አልሰማሁም እለዋለኋ!) እርግጥ በኢህአዴግ መዝገበ ቃላት ውስጥ “መሞላቀቅ” የሚል ቃል ላይኖር ይችላል፡፡ ግን ደግሞ የህዝብ ጥያቄ ነው እያልኩት ነው (የህዝብ አጋር ነኝ ይል የለ!) ለህዝብ ጥቅም ሲል ይቸገራ! (ለህዝብ ጥቅም እያለ ስንት ነገር ያደርጋል እኮ) ደሞ እኮ 21 ዓመት ሙሉ ለገዛው ህዝብ ከዚህም በላይ ቢያደርግ አይቆጭም (ገና 30 እና 40 ዓመት ሊገዛን ያስብ የለ!) ስለዚህ ሰበብ መደርደሩን ትቶ ጭክን ብሎ ያሞላቀን - በአዲሱ ዓመት! እንዴት ነው የሚያሞላ