Posts

በመንግስት ላይ ህዝብን በማነሳሳት ተከሰው በእስር ላይ ከምገኙት የሲዳማ ተወላጆች መካከል ኣራቱ በዋስ መለቀቃቸው ተሰማ፤ የፈዴራል መንግስት የውጭ ዜግነት ላላቸው ጋዜጠኞች ጭምር ምህረት ኣድርጎ ከእስር በመፍታት ላይ ባለበት በኣሁኑ ጊዜ በርካታ ሲዳማዎች የኢትዮጵያን ኣዲስ ኣመት ታስረው እንዲያሳልፉ መደረጋቸው እንዳዛዘናቸው የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ኣስታወቁ

ከሲዳማ ኣዲስ ኣመት ከፊቼ ማዕግስት ጀምሮ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ከስራ መደባቸው እና ከመኖሪያ ቤታቸው ተይዘው ታስረው ከከረሙት ሰዎች መካከል በዛሬው እለት ኣራቱ በዋስ ተለቀዋል። ዛሬ በዋስ የተለቀቁት ካላ ዘገዬ ሃሜሶ፤ ካላ ዘርፉ ዘውዴ፤ ካላ ጥሩነህ ቱካሌ፤ ካላ ካሳ ኦዲሶ ሲሆኑ፤ ካላ ኡጋሞን ጨምሮ ሌሎች ሰዎች እንደታሰሩ ናቸው። ታስረው ስለምገኙት ሰዎች በተመለከተ ያናገርናቸው ኣንዳንድ የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት፤ የፈዴራል መንግስት የውጭ ዜግነት ላላቸው ጋዜጠኞች ጭምር ምህረት ኣድርጎ ከእስር በመፍታት በላበት በኣሁኑ ጊዜ በርካታ ሲዳማዎች የኢትዮጵያን ኣዲስ ኣመት ታስረው እንዲያሳልፉ መደረጋቸው እንዳዛዘናቸው ገልጸው፤ የምመለከታቸው የመንግስት ኣካላት የታስሩ ሰዎችን ከእስር ቤት ፈተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቅሏቸው ጥር ኣቅርበዋል።

የሲዳማን ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ለማደናቀፍ የተነደፈ ሴራ

Image
የደኢህዴን/ኢህኣዴግ ኣመራሮች የሲዳማን ህዝብ እውነታ ገልብጠው ማንበብ ለምን ኣያቆሙም? ኩክሳ ከተባለ ሳምንታዊ “ጋዜጣ” የተገኘ ሁሌም ገልብጠው ነው የሚያነቡት ዛሬ ምን ኣዲስ ነገር ተገኘ ተብለን ልንጠየቅ እንችል ይሆናል፡ ፡ ኣዲስ ነገር ተገኝቶ ሳይሆን ... ተግባራቸው በሲዳማ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው ጫና እየሰፋ መምጣቱ ችላ ሊባል የማይገባውና የመብት ጥያቄያችንን ከመጠየቅ ግን ሊያስተጓጉለን የማይችል መሆኑን ለማሳሰብ ነው፡ ፡ ኩክሳ

የመላው ሲዳማ ሕዝብ ሕገ-መንግስታዊ ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ ትግሉ አይቆምም!!

ስማቸው እንዲገለጽ ካልፈለጉ የሲዳማ ታጋዮች የተላከ ጽሁፍ የመላው ሲዳማ ሕዝብ ሕገ - መንግስታዊ ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ ትግሉ አይቆምም !! ውድ የሲዳማ ሕዝብ ሆይ ! በቀደሙት ሳምንታት በሕዝባችን ላይ የተጫነውን የባርነት ቀንበር ለመታገል እንዲያስችሉ በማሰብ በርካታ መረጃ የሚያስጨብጡ ፅሑፎች ለንባብ መብቃታቸው ይታወሳል፡፡ ፅሑፎችም በይበልጥ ሕዝቡ ለነፃነቱ እንዴት መታገል እንዳለበት አቅጣጫ ከመጠቆም አልፎ የተለያዩ ወቅታዊ መረጃ የመስጠት ትልቅ ሚና ነበራቸው፡፡ የዚህ ፅሑፍ ዓላማም ከዚሁ የዘለለ አይሆንም፡፡ በዚህ መንግስት በሌለበት ሃገር ያለን ብቸኛ ሰላማዊ ትግል የማድረግ አማራጭ ስለሆነ !! የሐዋሳን ከተማ ከሲዳማ ሕዝብ እጅ ለመቀማት ( ወትሮስ የከተማዋን አብዛኛውን ክፍለ - ከተሞች ባለማወቅ ለአውሬዎች አሳልፈን ሰጥተን ነበር ) የተደረገው እኩይና አስነዋሪ የደኢህዴኖች ሴራ በሲዳማና በሲዳማ ሕዝብ ወዳጆች ልብ ውስጥ ከሃምሳ በላይ ወንድሞቻችንን፣ እህቶቻችንን፣ አባቶቻችንን በጠራራ ፀሐይ ካጣንበት የዛሬ 10 ዓመት ዘግናኝ ትዕይንት በላይ የጎዳንና ዛሬም የማይቀዘቅዝ ቁጣው ነግሶ ሰንብቷል፡፡ ለነሱ ሕዝቡ ውስጥ ለውስጥ ( ካድሬዎቻቸውም ጭምር ) እየሰራ ያለውን ስራ እንደቀድሞው የሲዳማ ሕዝብ አንዴ ሞቅ ብሎ ከ 3 ቀናት በኃላ ይቀዘቅዛል ከሚለው አዙሪታቸው ሳይወጡ አንድ ቀን በድንገት ፈንድቶ ታሪክ እንደሚለወጥና ውስጥ ለውስጥ እየሸረሸሩ የወሰዷቸውን በከተማም ሆነ ክልል ደረጃ የሚገኙ ቁልፍ ኃላፊነቶችን ተረክበንና ሕገ - መንግስታዊ መብታችንን አስከብረን በዓይናቸው የምናሳያቸው ቀን ቅርብ ነው፡፡ የጥፋት አጀንዳ አንግበው የመጡት ደኢህዴኖች ከጠበቁት በተቃራኒው የሲዳማ ሕዝብ ለነፃነቱ፣ ለአንድነቱና ለሕልውናው ታሪካዊ ትግል እንዲ

Ethiopia’s Ruling Party to Meet Sept. 16 on Meles’s Successor

Image
By William Davison (Bloomberg) — Ethiopia’s ruling coalition will meet on Sept. 16 to select its chairman, who will replace the late Prime Minister, Meles Zenawi, as the party’s chief and probably succeed him as the Horn of Africa nation’s leader. Addisu Legesse, Hailemariam Desalegn, Bereket simon with their late chairman Meles Zenawi It’s “highly likely” the party chairman will become prime minister, State Minister for Communications Shimeles Kemal said by phone today from the capital, Addis Ababa. Meles, Ethiopia’s leader of 21 years who oversaw one of Africa’s fastest-growing economies, died on Aug. 20 from an infection contracted while recuperating from an undisclosed illness. Hailemariam Desalegn, Meles’s deputy, took over in an acting capacity the next day. “We are expecting the council meeting to be on the 16th,” Seikoture Getachew, the foreign relations head at the Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front’s secretariat, said by telephone. “There will be

ለአህጉራዊ የየብስ ትራንስፖርት ትስስር ኢትዮጵያ የቤት ሥራዋን በማጠናቀቅ ዋዜማ ላይ ትገኛለች ፤ኢትዮጵያም የአፍሪካ አገራትን በየብስ ትራንስፖርት ለማገናኘት እየተገነቡ ካሉት ዘጠኝ ዋና መንገዶች የኬፕታውን-ካይሮ መንገድ ፕሮጀክት አካል የሆነውን የአዲስ አበባ-ናይሮቢ-ሞምባሳ አገናኝ መንገዶች ግንባታ ተያይዛዋለች። በዚህም መሰረት የዚህ ፕሮጀክት አገናኝ ለሆነው አዲስ አበባ-ሐዋሳ-ሀገረማርያም-ያቤሎ-ሜጋ-ሞያሌ መንገድ ግንባታ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡

የአፍሪካ አገራትን የንግድ ልውውጥ ለማፋጠን ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትን የሚያጠናክሩና ድህነትን የሚቀንሱ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡ ይህን የአገራቱን ግንኙነት ለማጠናከርም ለመንገድ ልማት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የ«ትራንስ አፍሪካን ሃይ ዌይስ»ፕሮጀክት ተቀርፆ ተግባራዊ እየሆነ ነው፡፡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ በ«ትራንስ አፍሪካን ሃይ ዌይስ" ፕሮጀክት የአህጉሪቱን ሀገሮች የሚያስተሳስሩ ዘጠኝ ዋና ዋና መንገዶች ይገነባሉ፡፡እነዚህም 56ሺ683ኪሎ ሜትር ይሸፍናሉ፡፡እነዚህ ዋና መንገዶች ከሰሃራ በታች በሚገኙ 41 ከተሞች የሚያልፉ ሲሆን፤ 500 ሚሊዮን ያህል ዜጎችንም ያገናኛሉ፡፡ የመንገዶቹ መገንባት የባህር በር ለሌላቸው አገራት የሚሰጠው ጠቀሜታም እጅግ የላቀ በመሆኑ መንገዱ በሚያልፍባቸው አካባቢዎች የሚገኙ አገራት የመንገዱ አካል የሆኑ መንገዶች በመገንባት ላይ ናቸው። ኢትዮጵያም የአፍሪካ አገራትን በየብስ ትራንስፖርት ለማገናኘት እየተገነቡ ካሉት ዘጠኝ ዋና መንገዶች የኬፕታውን-ካይሮ መንገድ ፕሮጀክት አካል የሆነውን የአዲስ አበባ-ናይሮቢ-ሞምባሳ አገናኝ መንገዶች ግንባታ ተያይዛዋለች። በዚህም መሰረት የዚህ ፕሮጀክት አገናኝ ለሆነው አዲስ አበባ-ሐዋሳ-ሀገረማርያም-ያቤሎ-ሜጋ-ሞያሌ መንገድ ግንባታ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡ የአዲስ አበባ-ናይሮቢ-ሞምባሳ መንገድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የአዲስ አበባ-ሐዋሳ መንገድ በመጀመሪያው የመንገድ ልማት ዘርፍ መርሐ ግብር ከ10 ዓመት በፊት ተገንብቶ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን፣94 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የሃገረማርያም-ያቤሎ መንገድም በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እየተገነባ ይገኛል፡፡ ግንባታውም በግብፁ «ዓረብ ኮንትራክተርስ» እየተከናወነ ሲሆን፣ «ጓፍ ኢንጂነርስ አማካሪ መሐንዲሶች» ደ