Posts

ኢህአዴግ አጣብቂኝ ውስጥ

የኢህአዴግ ስራአስፈፃሚ ማክሰኞ፣ መሰከረም 4፣ 2012 ተሰብስቦ ውሎአል። ስብሰባውን ባለማጠናቀቁም ዛሬ መስከረም 5 ቀጥሎ እንደሚውል መረጃዎች ይጠቁማሉ። የስራአስፈፃሚው አባላት በጥቅሉ 36 ሲሆኑ፣ በመለስ መሞት ምክንያት ተሰብሳቢዎቹ 35 ናቸው።     ህወሃትን ወክለው በስብሰባው ላይ የተገኙት 8 ሰዎች፣ ፀጋይ በርሄ፣ አባይ ወልዱ፣ አባዲ ዘሙ፣ ቴዎድሮስ ሃጎስ፣ ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ ደብረፅዮን፣ በየነ እና አዜብ መስፍን ሲሆኑ፣ ነባሮቹ እና አንጋፋዎቹ የህወሃት  አመራር  አባላት ከስብሰባው ውጭ በመሆናቸው ኢህአዴግ በብአዴን እጅ ላይ መውደቁ ይነገራል። ከብአዴን በረከት ስምኦን እና አዲሱ ሲገኙ  ከኦሮሚያና ከደቡብ ግርማ ብሩ እና ሬድዋን ሁሴን  ተገኝተዋል።  8ቱ የህወሃት አባላት መለስን የሚተካ አንድ ሰው ወደ ስብሰባው ለመጨመር ጠይቀው  የአመራሩ አባላት አሰራሩን በመጥቀስ ሳይፈቅዱላቸው ቀርተዋል።  ትናንት በዋለው ስብሰባ ላይ ሙሉ መግባባት ላይ ሊደርሱ ባለመቻላቸው፣ አጀንዳቸውን ለማሳደር ተገደዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የስራአስፈፃሚው ስብሰባ ላይ መሳተፍ ያልቻሉት አንጋፋዎቹ የህወሃት አመራር አባላት ድርድር ጠይቀዋል። እነዚህም፣ ስዩም መስፍን፣ አርከበ ኡቅባይ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ፣ ስብሃት ነጋ እና ሳሞራ የኑስ ናቸው። አከራካሪው አጀንዳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የምክትሉ ሹመት ጉዳይ ሲሆኑ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታም እንዲሁ እያወዛገበ ይገኛል።  http://minilik-salsawi.blogspot.com/2012/09/blog-post_4779.html?spref=fb

የሲዳማ ቋንቋ ትምህርት ደረጃ ኣንድ

Image
Tutorial for Sidama language level one course. To fully benefit from this tutorial, you have to visit " Sidama Language Level One (WIKI page)

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የተጀመሩ የልማት ተግባራት ከግብ እንዲደርሱ ከመንግስት ጐን በመሆን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንደሚወጡ የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች ተናገሩ፡፡

Image
 ከማህበራዊ መረብ የተገኘ ፎቶ ሲዳማ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሲያለቅስ በሲዳማ ህዝብ አንድ ጀግና ወይም የጐሳ መሪ ህይወት ሲያልፍ የሚደረገው ባህላዊ የለቅሶ ስርዓት ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስሩ ተደርጓል፡፡ ባህላዊ የለቅሶ ስርዓቱን የሚገልፀውና ዶሬ በመባል የሚታወቀው እንጨት ከተተከለ ከዘጠኝ ቀናት ቆይታ በኋላ እንዲወድቅ የተደረገ መሆኑን የተናገሩት የሀገር ሽማግሌዎቹ  ስርዓቱ ከተጠናቀቀ በኃላ  ሁሉም የብሔሩ ተወላጆች ወደ ልማት ማተኮር እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ የሲዳማ ህዝብን ጨምሮ የመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች መብት እንዲረጋገጥ ያደረጉ ታላቅ መሪ መሆናቸውን የገለፁት የሀገር ሽማግሌዎቹ ለእርሳቸው ያለንን አክብሮትና ፍቅር በልማቱ ጠንክረን በመሳተፍ እንገልፃለን ነው ያሉት፡፡ የሲዳማ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ በበኩላቸው የሲዳማ ህዝብን ከጭቆና እንዲወጣ ያደረጉት የአቶ መለስን ህልፈት አስመልክቶ የዞኑ ህዝብ በከፍተኛ ሁኔታ ሀዘኑን እየገለፀ የቆየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እንደ ምክትል አስተዳዳሪው ህዝቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለልማት ተነሳስቷል፡፡ ባህላዊ የለቅሶ ስርዓት የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀብር ስነ ስርዓት ከተፈፀመ ከአንድ ቀን በኃላ መሆኑን ባልደረባችን በኃይሉ  ጌታቸው ዘግቧል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/28NehTextN104.html

የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ስምና ታሪክ ከመቃብር በላይ ሲታወስ እንዲኖር የሚደረጉ ተግባራትን እንደሚያከናውኑ በሲዳማ ዞን የዳራ ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

Image
በተለያዩ የልማት ሥራዎች የተሰማሩ አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ህልፈተ ህይወት ምክንያት የደረሰብንን ቁጭት የምንወጣው የሳቸው ግብና ራዕይ ስናሳካ ነው ብለዋል፡፡ በምናስመዘግበው ውጤት ለዘላለም በሰማዕትነት እንዘክራቸዋለን ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ መጪው ትውልድ የእሳቸውን የሥራ ባህል እንዲወርስም ጥረት እንደሚያደርጉ መናገራቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ዘግቧል፡፡

የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ መልካም እድል ለሲዳማ ልጆች

New አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 28 (ኤፍ ቢ ሲ) የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል። ከዛሬ ጀምሮ በኢንተርኔት ድረ ገጽ  www.nae.gov.et  መመልከት እንደሚችሉ የሀገር አቀፈ ፈተናዎች ኤጀንሲ ለፋና በሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቋል። የተማሪዎች ውጤት በቀጣይ 10 ቀናት ውስጥ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የሚሰራጭ ሲሆን ፥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም እና የመሰናዶ መግቢያ ውጤትም በቀጣይ ሁለት ቀናት ይፋ እንደሚሆን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሄር ተናግረዋል። በዘንድሮው አመት ፈተናውን የወሰዱ የመደበኛ ተማሪዎች ቁጥር 519,948 ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ 283,712 ወንድ እና 236, 236 ሴቶች ናቸው። የዚህን ዓመት የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን ስንመለከትም ፥ 67 ነጥብ 23 በመቶ የሚሆኑ መደበኛ ተማሪዎች ከ2 ነጥብ በላይ አስመዝግበዋል። ፈተናውን ከወሰዱ ተፈታኞች ውስጥ 1 ነጥብ 7 በመቶ የሚሆኑት 8 ሺህ 849 ተማሪዎች 4 ነጥብ ማምጣት የቻሉ ናቸው ተብሏል። ከእነዚህም ውስጥ 6 ሺህ 441 የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ ሴቶች ደግሞ  የቀረውን 2 ሺህ 408 ቁጥር እንደሚይዙ ባህሩ ይድነቃቸው ዘግቧል። http://www.fanabc.com/Story.aspx?ID=25767&K=