Posts

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የተጀመሩ የልማት ተግባራት ከግብ እንዲደርሱ ከመንግስት ጐን በመሆን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንደሚወጡ የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች ተናገሩ፡፡

Image
 ከማህበራዊ መረብ የተገኘ ፎቶ ሲዳማ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሲያለቅስ በሲዳማ ህዝብ አንድ ጀግና ወይም የጐሳ መሪ ህይወት ሲያልፍ የሚደረገው ባህላዊ የለቅሶ ስርዓት ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስሩ ተደርጓል፡፡ ባህላዊ የለቅሶ ስርዓቱን የሚገልፀውና ዶሬ በመባል የሚታወቀው እንጨት ከተተከለ ከዘጠኝ ቀናት ቆይታ በኋላ እንዲወድቅ የተደረገ መሆኑን የተናገሩት የሀገር ሽማግሌዎቹ  ስርዓቱ ከተጠናቀቀ በኃላ  ሁሉም የብሔሩ ተወላጆች ወደ ልማት ማተኮር እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ የሲዳማ ህዝብን ጨምሮ የመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች መብት እንዲረጋገጥ ያደረጉ ታላቅ መሪ መሆናቸውን የገለፁት የሀገር ሽማግሌዎቹ ለእርሳቸው ያለንን አክብሮትና ፍቅር በልማቱ ጠንክረን በመሳተፍ እንገልፃለን ነው ያሉት፡፡ የሲዳማ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ በበኩላቸው የሲዳማ ህዝብን ከጭቆና እንዲወጣ ያደረጉት የአቶ መለስን ህልፈት አስመልክቶ የዞኑ ህዝብ በከፍተኛ ሁኔታ ሀዘኑን እየገለፀ የቆየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እንደ ምክትል አስተዳዳሪው ህዝቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለልማት ተነሳስቷል፡፡ ባህላዊ የለቅሶ ስርዓት የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀብር ስነ ስርዓት ከተፈፀመ ከአንድ ቀን በኃላ መሆኑን ባልደረባችን በኃይሉ  ጌታቸው ዘግቧል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/28NehTextN104.html

የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ስምና ታሪክ ከመቃብር በላይ ሲታወስ እንዲኖር የሚደረጉ ተግባራትን እንደሚያከናውኑ በሲዳማ ዞን የዳራ ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

Image
በተለያዩ የልማት ሥራዎች የተሰማሩ አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ህልፈተ ህይወት ምክንያት የደረሰብንን ቁጭት የምንወጣው የሳቸው ግብና ራዕይ ስናሳካ ነው ብለዋል፡፡ በምናስመዘግበው ውጤት ለዘላለም በሰማዕትነት እንዘክራቸዋለን ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ መጪው ትውልድ የእሳቸውን የሥራ ባህል እንዲወርስም ጥረት እንደሚያደርጉ መናገራቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ዘግቧል፡፡

የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ መልካም እድል ለሲዳማ ልጆች

New አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 28 (ኤፍ ቢ ሲ) የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል። ከዛሬ ጀምሮ በኢንተርኔት ድረ ገጽ  www.nae.gov.et  መመልከት እንደሚችሉ የሀገር አቀፈ ፈተናዎች ኤጀንሲ ለፋና በሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቋል። የተማሪዎች ውጤት በቀጣይ 10 ቀናት ውስጥ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የሚሰራጭ ሲሆን ፥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም እና የመሰናዶ መግቢያ ውጤትም በቀጣይ ሁለት ቀናት ይፋ እንደሚሆን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሄር ተናግረዋል። በዘንድሮው አመት ፈተናውን የወሰዱ የመደበኛ ተማሪዎች ቁጥር 519,948 ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ 283,712 ወንድ እና 236, 236 ሴቶች ናቸው። የዚህን ዓመት የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን ስንመለከትም ፥ 67 ነጥብ 23 በመቶ የሚሆኑ መደበኛ ተማሪዎች ከ2 ነጥብ በላይ አስመዝግበዋል። ፈተናውን ከወሰዱ ተፈታኞች ውስጥ 1 ነጥብ 7 በመቶ የሚሆኑት 8 ሺህ 849 ተማሪዎች 4 ነጥብ ማምጣት የቻሉ ናቸው ተብሏል። ከእነዚህም ውስጥ 6 ሺህ 441 የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ ሴቶች ደግሞ  የቀረውን 2 ሺህ 408 ቁጥር እንደሚይዙ ባህሩ ይድነቃቸው ዘግቧል። http://www.fanabc.com/Story.aspx?ID=25767&K=

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢሕአዴግ/ ሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ ነገ ይሰበሰባል

Image
አዲስ አበባ ነሐሴ 28/2004 የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢሕአዴግ/ ሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ ነገ ማክሰኞ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡ በነገው ዕለት በሚከፈተው የግንባሩ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃጸምን ይዳስሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ኮሚቴው የ2004 በጀት ዓመት አፈፃጸሞችን በጥልቀት በመፈተሽ የግንባሩ ሊቀመንበር የነበሩትና የባለ ራዕዩና ታላቁ መሪ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ህልፈት ተከትሎ በሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተስተጋባውን ቁጭትና እልህ በልማት ላይ በሚቻልበት ሁኔታ እንደሚነጋገር ለማወቅ ተችሏል፡፡ የታላቁን መሪውና በእሳቸው የተገነባውን የግንባሩና የአገሪቱ ልማታዊ መንግሥት ራዕይ ሁሉም በየተሰማራበት የስራ መስክ በመረባረብ ለማስቀጠል የገባውን ቃልና መነሳሳት የሚመጥን ዝግጅት ማድረግ በሚቻልባቸው ዙሪያም ኮሚቴው ይመክራል፡፡ በተጨማሪም ከኮሚቴው አባላት በሚነሱ አጀንዳዎች ዙሪያ በመምከር ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል ሲል ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡ http://www.ena.gov.et/story.aspx?ID=2329

Desecuritising quest for regional self-administration in Sidama-land

BY  Mulugeta Daye 8 hours ago  · (ከማህበራዊ መረብ ላይ የተገኘ ጽሁፍ) I am learning form the reports from the Sidama-land the reason Iyasu Ragaasa, Dukk’ale Lamiso, Boshla Gabiso, Abate Kimmo, et al jailed, they are alleged to mobilise people against government. If the allegations are correct, and even if those jailed people involved in mobilization of the Sidama-for regional self- administration. The commitment of late Prime-Minster Meles Zenawi to give constitutional guarantee to the Nations, Nationalities, and Peoples, to opt out from the Union which they are uncomfortable with as it is enshrined in article 39 of Ethiopian constitution, has become invalid while this visionary is in hospital bed. In the movement of 2005-2006 he legitimised the Sidama’s quest for regional autonomy. However he come down to the Sidama-land, capital and politely advised the nation to choose regional autonomy or development. For the Sidama both Regional autonomy and Development are the same thing. Because withou