Posts

ወ/ሮ አዜብ አቶ መለስን ለመተካት እየታገሉ ነው

Image
ነሀሴ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለቤታቸውን በሞት ካጡ በኃላ በእሳቸው እግር ተተክተው የህወሃትን የሊቀመንበርነት ቦታ ተቆናጥጦ ወደ ኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበርነት ለመሳብ ድጋፍ የማሰባሰብ ዘመቻ ላይ መክረማቸውን ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡ በኢህአዴግ 36 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ ብቸኛ ሴት ሆነው በመስከረም ወር 2003 ዓ.ም ከፍተኛውን የፓርቲ ሥልጣን በባለቤታቸው በአቶ መለስ ዜናዊ ልዩ ድጋፍ ማግኘት የቻሉት ወ/ሮ አዜብ የሰሞኑን ሐዘናቸውን ለድጋፍ ማሰባሰቢያ እንደተጠቀሙበት ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ ወ/ሮ አዜብ ለድጋፍ ማሰባሰቢያ ይጠቅሙኛል የሚሉዋቸው የህወሃት ሰዎች ለቅሶ ለመድረስ ቤተመንግስት በሚመጡበት ወቅት አንገታቸውን እያነቁ በማልቀስና በማስለቀስ፣የማይፈልጉዋቸውን ደግሞ ፊት ሲነሱ መቆየታቸው በተለይ በአመራር ላይ ባሉት የብአዴን ሰዎች ዘንድ አልተወደደላቸውም፡፡ ወ/ሮ አዜብ ባለቤታቸው አቶ መለስ በ8ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በጡረታ ያሰናበታቸው አቶ ሥዩም መስፍን፣አቶ አባይ ጸሐዬ፣አቶ አርከበ ዕቁባይ፣አቶ ተፈራ ዋልዋ፣አቶ አዲሱ ለገሰን “የመለስን ራዕይ ለማሳካት” በሚል ስትራቴጂ ከጎንዋ ለማሰለፍ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ መሰንበታቸውን ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡ ወ/ሮዋ በአቶ መለስ ቀብር ፕሮግራም ላይ በወ/ሮ ነጻነት አስፋው የተዘጋጀላቸውን ኦፊሻል ንግግር በመተው የራሳቸውን ኃሳብ ያንጸባረቁበት ንግግራቸው “መለስ የጀመራቸው ፖሊሲና ስትራቴጂዎች እስካልተበከሉና እስካልተበረዙ ድረስ …” የሚለው ንግግራቸው በመለስ ስም ለጀመሩት የድጋፍ ማሰባሰብ ጥረታቸው ይረዳቸው ዘንድ ሆን ብለው ያደረጉት መሆኑን ምንጫችን  አስቀምጦአል፡፡ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ጉባኤያቸ

የሲዳማን የክልል ጥያቄ በማቀጣጠል ይሰሩ ከነበሩት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል ኣንዳንዶቹ ጸረ የሲዳማ ክልል ኣቋም ካላቸው ግለሰቦች ጎራ እየተቀላቀሉ መሆኑ ተሰማ

Image
የሲዳማ የክልል ጥያቄን በተደራጀ መልኩ ለማቅረብ የብሄሩን ሽማግሌዎች በመደራጀት እና የክልል ኣስፈላጊነትን በተመለከተ ለህዝቡ በማስረዳት ከፍተኛ የሆነ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ በዩኒቨርስቲ ተመሪዎች ስሰራ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፤ ግንዛቤ የመፍጠር ኃላፊነት ወስደው በመስራት ላይ ከነበሩት ወጣቶች መካከል ኣንዳንዶቹ በግልጽ ባልታወቀ ምክንያት ቡድኑን በመልቀቅ ላይ ናቸው። ስማቸው እንድገለጽ ያልፈለጉ የሲዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደተናገሩት፤ ጸረ የሲዳማ ክልል ኣቋም ያላቸው ግለሰቦች ኣንዳንድ ተማሪዎችን በገንዘብ በመደለል እና በማስፈራራት በሲዳማ የክልል ጥያቄ ላይ ያላቸውን ኣቋም እንዲቀይሩ በማድረግ ላይ ናቸው። እነዚሁ በገንዘብ ተደልለው ጸረ የሲዳማ ክልል ኣቋም ካላቸው ቡድኖች ጎን የተቀላቀሉት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሌሎች ከዚህ ቀደም ኣብሯቸው ሲታገሉ የነበሩት በማጋለጥ እና በማሳሰር ላይ ናቸው ብለዋል። ለኣብነትም የሲዳማን ሽማግሌዎች በማደረጀት ከፍተኝ ሚና ከተጫዎቱች ተማሪዎች መካከል ሁለቱ በቅርቡ መታሰራቸውን ኣመልከተው፤ የተቀሩትም በመፈለግ ላይ መሆናቸው ተናግረዋል።

በፊቼ ማግስት በወንዶ ገነት ወረዳ ከታሰሩት ወጣቶች መካከል 12ቱ እንደታሰሩ መሆናቸው ተገለጸ

በወንዶ ገነት ወረዳ በፊቼ ማግስት የሲዳማን የክልል ጥያቄ የሚያወድሱ ግጥሞችን እየገጠሙ ቄጣላ የወጡ ወጣቶች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ታፍሰው መታሰራቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ከታሰሩት ወጣቶች መካከል 12 ቱ እስከ ኣሁን ኣልተፈቱም። ወጣቶቹ እስከ ኣሁን ድረስ ለምን እንደታሰሩ የሚገልጽ ምንም መረጃ የሌላቸው ሲሆን፤ የታሰሩበትን ምክንያት በይፋ እንደማያቁ እና ዛሬ ነገ ትፈታላችሁ እየተባሉ በእስር ላይ እንደምገኑ ገልጸዋል።

በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ውስጥ ይሰሩ የነበሩ እና በሙስና ተጠርጥረው ታስረው የተፈቱት ግለሰቦች ተመልሰው ለፍርድ ልቀርቡ መሆኑ ተሰማ

በሙስና ተጠርጥረው ለሰባት እና ስምንት ወራት ከታስሩ በኃላ ባለፈው ወር ውስጥ የተመሰረተባቸው ክስ ውድቅ ተደርገው የተፈቱ ግለሰቦች በክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለፍርድ ልቀርቡ ነው። ጉዳያቸው ያይ የነበረው የከተማዋ ፍርድ ቤት በነጻ የለቀቃቸውን እነዚሁ  የሙስና ተጠርጣሪዎችን በተመለከተ ኣቃቤ ህግ ለክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማስገባቱ የተነሳ መዝጋባቸው ለሁለተኛ ጊዜ ይከፈታል ተብሏል።

መለስ ዜናዊ የሚባል አዲስ ሐይማኖት ተፈጠረ

ጉድ ሳይሰማ መስከረም ኣይጠባ ኣይደለም? መለስ  ዜናዊ  የሚባለውን  ሀይማኖት  አማኖች  ኣይጋ ፎረም ላይ ያወጡትን  መግለጫ  ሙሉ  ቃል  ከዚህ  በታች  ያንቡ I am a born-again believer & my religion is Meles Zenawi Adal Isaw adalisaw@yahoo.com September 2, 2012 By the will of the Goddess of Ethiopia, I believe, Meles Zenawi was born for reasons other than the ordinary ones that you and I were born for.  Meles was born to lead and help build a modern, sovereign, and a free Democratic Republic of Ethiopia. I have a reason to revert back to the religion that I have abandoned early in life.  Things were trite and nothing was out of the ordinary then, and, I had to walk away from my religion as a result.  But now, and after many years of abandoning my religious belief, I am a born-again believer and my religion is Meles Zenawi. I believe in Meles Zenawi and he is my religion from now on till the end of my time.  This I believe is not the result of stretching my emotion.  Instead, it is the result of seeing the tangible change