Posts

ክልል ለምን?

Image
(ከማህበራዊ መረብ ላይየተገኘ ጽሁፍ) ለአለቆቻቸው የኖሩ ጥቂት የሲዳማ ኢህአዴግ ካድሬዎች በእነርሱ አመራር የሲዳማ ሕዝብ ኑሮ አሻሽለናል፣ ልማትና ዕድገት አምጥተናል ብለው ሕዝቡን የሚያታልሉበትን ሁኔታ ውስጥ ገብተን ስንመለከት ተቃራኒውን ሆኖ ነው የምናገኘው፡፡ ለምሳሌ በሐዋሳ ከተማ የታየው ዕድገትና ለውጥ የሲዳማን ሕዝብ ለውጥ ያሳያል ማለት በድሀው ሕዝባችን ማላገጥ ነው፡፡ ልመና ነውር የሆነበትን የሲዳማን ባህል፣ ችግሩ ከአቅም በላይ ሆኖበት በከተማው እየተበራከተ የመጣውን የሲዳማ ለማኝ መቁጠር ይቻላል፡፡ የሕዝባችንን ዕድገትና ኑሮ ለማወቅ እነዚህን በልመና የተሰማሩ ወገኖችንና በከተማው የተበራከቱ የሲዳማ ጎዳና ተዳዳሪ ልጆችን ታርክ እንዲሁም ከከተማው ዙርያ ጀምሮ የገጠሩ ሕዝብ ያለበትን የኑሮ ሰቆቃ ማየት ይበቃል፡፡ ሲዳማ ከ90% በላይ በገጠር የሚኖር ሕዝብ እንደሆነ መዘንጋት የለብንም፡፡ ከሕዝቡ ቁጥር መጨመር ጋር የመሬት ጥበት እና የምግብ ዋስትና አለመረጋገጥ በልቶ ለማደር፣ ልጆቹን ለማስተማር እንዲሁም አስፈላጊውን ቁሳቁስ ለመግዛት ከዋጋ ንረት የተነሳ ለሕዝቡ የሚቀመሱ አልሆኑም፡፡ 60 ከመቶ የሚሆነው ሕዝባችን ከድህነት ወለል በታች ሲሆን ከዚህ ውስጥ 20 ከመቶው ራሱን መመገብ የማይችል ሲሆን የቀረው ድሀው ሕዝብ በቀን ከአንድ ዓይነት ምግብ (ደረቅ ዋሳና ቅጠላቅጠል) በመመገብ በዚህ ዓለም ኑሮውን ለማርዘም የሚጥር ነው፡፡ በሃዋሳ ከተማ የጎዳና ተዳዳሪ ቤተሰብ ዕድገት ማለት ሁለንተናዊ እና ሕዝቡን ያማከለ እንጂ የጥቂት ሰዎች (በስልጣን ላይ ያሉት፣ የት/ት ዕድል አግኝተው በከተሞች የተሻለ ስራ ያላቸውን እንዲሁም እጅግ ጥቂት ነጋዴዎችን) ኢኮኖሚ መዳበር አይደለም፡፡ ሕዝቡ ከድህነት ወለል በታች ባለበት፣ የምግብ ዋስትና ባልተረጋ

ዕውቀት እንረዳለን

Image
አራተኛ   ክፍል   እያለሁ   የሂሳብ   መጽሐፍ   ለአራት   ነበር   የሚታደለን፡፡   ታድያ   የቤት   ሥራ   የተሰጠ   ቀን መጽሐፉን   ለመውሰድ   ተረኞች   ያልነበርነው   ሦስታችን   የቤት   ሥራውን   ስንገለብጥ   ከተማሪው   ሁሉ ወደ   ኋላ   እንቀር   ነበር፡፡   ሕፃናት   ስለ   ነበርን፣   ከዚያም   የተሻለ   ስላላየን   መጽሐፍን   ለአራት   ለአምስት መውሰድ   የዓለም   ሥርዓት   መስሎን   ነበር   ያደግነው፡፡   የመጽሐፍ   ኮንደሚኒየም   አትሉም፡፡ የሚገርመው   ነገር   ይህ   አሠራር   በሁለተኛ   ደረጃም   ሆነ   በኮሌጅ   ደረጃ   ሳይሻሻል   ነው   እኛ   ትምህርት « ጨርሰን »   የወጣነው፡፡   በተለይ   አዲስ   አበባ   ዩኒቨርሲቲ   ስድስት   ኪሎ   እያለሁ   እንድናነብ የሚሰጠንን   መጽሐፍ   ቤተ   መጻሕፍት   ሄዶ   ማግኘት   አስቸጋሪ   ነበር፡፡   አንዳንድ   ጊዜ   ሌላ   ሰው   ቀድሞ ያወጣውና   ወረፋ   ያዙ   እንባላለን፡፡   ወረፋው   ሳይደርሰን   ፈተናው   ቀድሞ   ይደርሳል፡፡   አንዳንድ   ጊዜ ደግሞ   ከነ   አካቴው   መጽሐፉ   አይኖርም፡፡   ምነው ?   ስንል  « መምህሩ   አውጥቶታል »   እንባላለን፡፡   ሌላ ጊዜ   ደግሞ   « በኮርስ   አውት   ላይኑ »   ላይ   ያለው   የመረጃ   መጻሕፍት   ዝርዝር   ከሌላ   የተገለበጠ   ይሆንና ቤተ   መጻሕፍቱ   እንኳን   ሊኖረው   ሰምቷቸውም   አያውቅ፡፡   እንዲህ   እኛ   መጽሐፍ   ብርቅ   ሆኖብን   አድገን   በኋላ   ገዝታችሁ   አንብቡ   ስንባል   ውቃቤ   ሊቀርበን አልቻለም፡፡   እኛ   በመጽሐፍ   መከራ   እንጂ   መች   ደስታ   አይተን