Posts

THIS UNIVERSAL DECLARATION OF HUMAN RIGHTS

Image
THIS UNIVERSAL DECLARATION OF HUMAN RIGHTS as a common standard of achievement for all peoples and all nations, to the end that every individual and every organ of society, keeping this Declaration constantly in mind, shall strive by teaching and education to promote respect for these rights and freedoms and by progressive measures, national and international, to secure their universal and effective recognition and observance, both among the peoples of Member States themselves and among the peoples of territories under their jurisdiction. Universal declaration of HR

Neoliberalism Brings Dead Ends

Image
By Meles Zenawi Meles Zenawi served as President and Prime Minister of Ethiopia between 1991 and 2012. This commentary is extracted from a draft research paper presented at Columbia University, United States, titled, Africa Development: Dead Ends and New Beginnings. The neo-liberal paradigm which suggests a non-activist and non-interventionist state, a night watchman state, as conducive to economic growth bases such conclusions on two pillars. One pillar has to do with the assertion that competitive markets are both pervasive and efficient. The second pillar has to do with a political economy based on the theory of socially wasteful rent-seeking activities and the rational choice theory of solely self-interest maximizing individuals.    Government created rent does not necessarily have to be socially wasteful.  It becomes wasteful only if solely self-interest maximizing individuals use it to create wealth at the expense of society and only if the state is incapable of imp

መለስ ዜናዊ ሲዘከሩ

Image
New የኢትዮጵያን የአምስት ሺሕም ሆነ የሦስት ሺሕ ዓመታት የመንግሥትነት ታሪክን አቆይተን ከ19ኛው ምእት ዓመት ብንነሣ፣ ጎልቶ የሚታየን ለ86 ዓመታት በመሳፍንት ተከፋፍላ ለነበረችው ኢትዮጵያ “ዘመነ መሳፍንት” ማብቃቱ በዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ መበሰሩ ነው፡፡ በተከታታይ የመጡት ነገሥታት አፄ ተክለ ጊዮርጊስ፣ አፄ ዮሐንስ፣ አፄ ምኒልክ፣ ልጅ ኢያሱ፣ ንግሥት ዘውዲቱና ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እንደየዘመናቸው ይብዛም ይነስ ተልዕኮቻቸውን ፈጽመው አልፈዋል፡፡ ተፍጻሜተ ዘውድ የሆኑትን የአፄ ኃይለ ሥላሴ ሥርዓት ለመገርሰስ የተነሣውና የፈነዳውን የየካቲት አብዮትን ተከትሎ ሥልጣኑን የተቆናጠጠው በወቅቱ ጥሪው “ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ” በኋላም ወደ ኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) በመለወጥ 17 ዓመት አገሪቱን መርቷታል፡፡ ይህ ከሆነም በኋላ ገና ሥልጣኑን በጨበጠ በመንፈቁ የትጥቅ ትግል የጀመረው የትግራይ ብሔር ድርጅት ሌሎች አጋሮቹ ከጎኑ አሰልፎ ለ17 ዓመት ያከናወነው ውጊያ በድል መጠናቀቁ ሌላኛው የታሪክ ምዕራፍ ነው፡፡ የታሪክ ፕሮፌሰሩ ባሕሩ ዘውዴ “የኢትዮጵያ ታሪክ ከ1847 እስከ 1983” ብለው ባሳተሙት መጽሐፋቸው ፍፃሜውን እንዲህ ገልጸውታል፡፡ “የኢሕዲሪ ምስረታን ያጀበው ሽብርቅና ሽርጉድ የደርግ ሥርዓት የተጠናወተውን መሠረታዊ ችግር ደብቆት ነበር፡፡ አራት ዓመትም ሳያስቆጥር፣ እንዲያ በረቀቀ ጥበብና በአያሌ ደምና ዕንባ የተገነባው ሥርዓት እንደ አሸዋ ክምር ተናደ፡፡ ደርግ ውስጥ የነበሩትን ባላንጣዎቹንና የከተሜውን ግራ ክንፍ ኃይል የሸወደው አምባገነን፣ የገጠር ሽምቅ ተዋጊዎቹን ምሕረት የለሽ የጥይት ውርጅብኝ መቋቋም አቅቶት ወደቀ፡፡ ደርግ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን ብሔርተኛ አመፅ ለመግታት ከዐሥር ዓ

ሕዝብ ለመንግሥት የቤት ሥራ ሰጥቷል ተግባራዊ ምላሽ ይጠበቃል!

ውል ክፍል መሄድ ሳያስፈልግና ቃለ ጉባዔ መፈራረም ሳይጠይቅ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመንግሥት የቤት ሥራ ሰጥቷል፤ አደራ አቅርቧል፡፡ ተግባራዊ አዎንታዊ ምላሽም ከመንግሥት ይጠብቃል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈት የተሰማውን ሐዘን በሚያስገርም፣ በሚያስመካና ታሪካዊ በሆነ ሁኔታ ከልብ ገልጿል፡፡ ታሪክም ለዘለዓለም ሲዘግበው ይኖራል፡፡ በክብር መዝገብ አስፍሮታል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ሐዘኑን ብቻ አይደለም የገለጸው፡፡ የተጀመረውን የልማት ሒደት ዳር ለማድረስም ቃል ገብቷል፡፡ አሁንም በሕገ መንግሥታችን የሰፈሩትን መብቶችና ጥቅሞች እውን ለማድረግና የኢትዮጵያን ራዕይ ዳር ለማድረስ ዝግጁነቱን ገልጿል፡፡ በእንባም፣ በቃላትም፣ በፀሎትም፣ በሠልፍም፡፡ ሕዝብ መንግሥትን ‹‹ምራ እንከተልሃለን›› ብሏል፡፡ አደራውና የቤት ሥራውም ይኼው ነው፡፡ መንግሥት ይህንን የሕዝብ አደራና የቤት ሥራ በተገቢው መንገድ በተግባር ለመመለስ መንቀሳቀስ ይጀምር፡፡ መንግሥት ይህን የሕዝብ አደራና የቤት ሥራ የሚመልሰው እንዴት ነው? ለመመለስስ ይችላል ወይ? ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግና መንግሥት ይህን የሕዝብ አደራና የቤት ሥራ በሚገባ ከተገነዘቡትና መመለስ አለበት ብለው ካመኑበት ተገቢ ምላሽ ለመስጠት ምንም አያዳግታቸውም፡፡ ይቻላል፡፡ ለመመለስ ግን የሚከተሉትን መፈጸም አለባቸው፡፡ 1.    ቀጣይነት ሕገ መንግሥቱን መንግሥትም እንደ መንግሥት ኢሕአዴግም እንደ ገዥ ፓርቲ ያመኑበትና የተቀበሉት ብቻ ሳይሆን፣ እነሱ ሥልጣን ይዘው ባሉበት ጊዜ በራሳቸው ተነሳሽነት እውን የሆነ ነው፡፡ ስለሆነም ለቀጣይነቱ ችግር የለውም፡፡ የአምስት ዓመቱ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድም ባለው መንግሥትና ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ የታቀደና የፀደቀ ነው፡፡ ለተግባራዊነቱ ችግር የለ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ከተሰማ ጀምሮ መግለጫ ከሰጡት መካከል በሲዳማ ዞን ስር የሚገኙ የንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ፣ መንገዶችና ትራንስፖርት መምሪያ፣ የዳሌ ወረዳ አስተዳደር በሃዋሳ ከተማ የዳካ ቀበሌ ታዳጊ ተማሪዎች ህብረት፣ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ እንዲሁም የሀዲያ ዞን ንግድና ኢንዲስትሪ ልማት መምሪያ ይገኙበታል፡፡

ባለራዕይና የዘመናችን ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ ሁሉአቀፍ እውቀትና የመምራት ብቃት ያላቸው በሳል መሪ ነበሩ ብለዋል፡፡ በተመሳሳይም በይርጋዓለም ከተማ የሠላም አንድነት አረጋዊያን ማህበር የተስፋ ራዕይ አውራጅና ጫኝ ማህበር፣ ራይስ ኢንጀነሪንግ ኒያላ ሞተርስ፣ ሲዳማ ቡና አቅራቢዎች ማህበር፣ ፖራዳይስ ሆቴል፣ ይርጋዓለም ኮንስትራክሽንና  ኦሲስ ሆቴል ውስጥ የሚገኙ ሠራተኞች፣ ሃላፊዎቹና ባለቤቶቹ የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል፡፡ መሪያችን የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ አሌኝታ  የሆኑ ታላቅ ሰው ነበሩ ያሉት መግለጫ  ሰጪዎቹ በእሳቸው የተጀመሩትን እቅዶች ተግባራዊ በማድረግ ስራቸውን ከመቃብር በላይ ሲታወሱ እንዲኖሩ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ በተለይም ይህን የሰነቁትን ዓላማ ወጣቱ ትውልድ በደንብ ተገንዝቦት በጋራ የመረባረቡን ሃላፊነት እንዲወጣ አደራቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና ቤተሰቦቻቸውን መፅናናትን እንመኛለን ብለዋል፡፡