Posts

የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች መንግስት በዞኑ የምፈጸመውን የሰብኣዊ መብት ረገጣ፡ እስር እና እንግልት እንዲያቆም ጠየቁ፤ በመንግስት ላይ ህዝብን በማነሳሳት በምል የታሰሩ ግለሰቦች ያለ ምንም ቅድሜ ሁኔታ እንዲፈቱ ኣሳሰቡ።

የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ሪፖርተሮች ተዘዋውረው ያኗገራቸው የዞኑ ነዋሪዎች እንደተናገሩት፤ መንግስት በሰበብ ኣስባቡ የተለየ ኣመለካከት እና ኣስተሳሰብ የምያራምድ ግለሰቦችን በኣስፈለገው ጊዜ እና ወቅት የተለያዩ ስሞችን በመስጠት በማስር ላይ ነው። በሃዋሳ ከተማ ሌዊ ሆቴል ሲዝናኑ ያገኘናቸው ካላ ጌታሁን ሳርምሶ የተባሉ በከተማዋ የኣዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ነዋሪ እንደተናገሩት፤ መንግስት በተለያዩ ጊዚያት በተለይ ከክልሉ ባለስልጣናት ፖለቲካዊ ኣመለካት የተለየ ያለ ኣመለካከት ያላቸውን ግለሰቦች ማሰሩ የተለመደ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው በኣሁኑ ጊዜ በተለይ ከሲዳማ የፊቼ በዓል ማግስት ጀምሮ በርካታ ሰዎች ህዝብን በመንግስት ላይ በማነሳሳት ተከሰው ታስረዋል። ግለሰቦች የመሰላቸውን ፖለቲካዊ ሆነ ማህባራዊ ኣመለካከትን ያለ ምንም ገደብ እንዲያራምዱ በምፈቅድ ህገ መንግስት ባለባት ኣገር ግለሰቦች የተለየ ኣመለካከት ስላላቸው ብቻ ስብኣዊ መብታቸው መጣሱ ኣግባብነት የለውም ብለዋል። ወጣት ንቆዲሞስ ኣየለ የተባለ በሃዋሳ ከተማ የባጃጂ ታክሲ ሽፌር በበኩሉ፤ የሲዳማ ክልል ይገባኛል ጥያቄ በተመለከተ ህዝባዊ ንቅናቄ  ከተጀመረ ወዲህ በተለይ ወጣቶች  በመንግስት የጸጥታ ሰዎች ማስፈራሪያ እንደምደርሳቸው ገልጿ፤ ለህዝቡ ጥያቄ ኣግባብነት ያለውን ምላሽ መስጠት እንጂ ሰዎችን ማስር እና ማንገላት መፍትሄ ኣይደለም ብለዋል። ካላ ዘርሁን ናራሞ የተባሉ በተለምዶ ስሙ ሊዝ ሰፈር በምባለው ኣከባቢ መንገድ ላይ ሲጓዙ ያገኘናቸው የሃዋሳ ከተማ ነዋሪ፤ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሃዋሳ ከተማ ብሎም በሲዳማ ዞን ወረዳዎች ውስጥ ግለሰቦች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ከመኖሪያ ቦታቸው እና ከስራ ገበታቸው እየተያዙ እንደምታሰሩ ጠቅሰው፤ ግለሰቦች በተጠረጠሩት ጉዳይ ላይ

የቡና ዋጋ ቅናሽ ማሳየት እያነጋገረ ነው

Image
ቃልዲ በኢትዮጵያ ምድር የገዘፈ ታሪክ ባለቤት ነው፡፡ በዘጠነኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ ይሆናል። ከከፋ መንደር ፍየሎች ጥዑም ፍሬን አገኙ። የመንጋው እረኛ ብላቴናው ቃልዲ ከዛን ዘመን ጀምሮ ስሙ በታሪክ ማኅደር ሰፈረ። ምክንያት የሚያግዳቸው ፍየሎች ለሀገሬውና ለዓለም ሕዝብ ቡናን በማሳወቃቸው ነው። ምስጋና ለእነርሱ ይሁንና ይኸው ዛሬም ድረስ ኢትዮጵያ ከጥዑም ቡናዋ እረኛው ቃልዲም ከታላቅ ስሙ ጋር ተቆራኝተው ለዘመናት መዝለቅ ችለዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ካሉ ሰባት ታዋቂ ቡና አምራች ሀገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉርም በዘርፉ የአንበሳውን ድርሻ ትወስዳለች። በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ውስጥ ሰፊ ድርሻ ያለው ቡና ለሀገሪቱ ምጣኔ ሀብታዊ ፋይዳ የጀርባ አጥንት ነው። ከሌሎች የግብርና ምርቶች ቡና ከአገር ውስጥ ተጠቃሚዎች አልፎ ለበርካታ ሀገራት በመቅረብም የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ረገድ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ያለተቀናቃኝ በአውራነት ሊዘልቅ ችሏል። ኢትዮጵያ ቡናን ለመጀመሪያ ጊዜ ለባህር ማዶ ገበያ ያቀረበችው በፈረንጆቹ የዘመን አቆጣጠር 1838 በምጽዋ ወደብ በኩል እንደነበር ታሪክ ይነግረናል። በ19ኛው ክፍለ ዘመን ሁለት የቡና ዓይነቶችን ( ሐረር እና አቢሲኒያ) ለንደንን ጨምሮ ወደ ኒውዮርክ እና ማርሴል ከተሞች በመላክ የኤክስፖርት ንግዱን ተያያዘችው። ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ዕድሜ ያስቆጠረው የኤክስፖርት ግብይት በአሁኑ ወቅትም በጥራት እና ብዛት ዕድገት እያሳየ ዘልቋል። ሆኖም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በግብይት ሥርዓቱ ውስጥ የሚፈጠሩ የተለያዩ መሰናክሎች ሳቢያ አርሶ አደሮች የጥረታቸውን ያህል ተጠቃሚ ነበሩ ለማለት ያዳግታል። ከፍተኛ የቡና ምርት መገኛ እንደሆኑ በሚነገርላቸው የተለያዩ አካባቢዎች የኅብረት ሥራ ማኅበራት መመሥረትን ተከት

የኢትዮጵያን የውክልና ሕግ ቢያውቁ ይጠቀማሉ

በኤልያስ ዶጊሶ  ከደቡብ ክልል ፍትህ ቢሮ  እጅግ እየዘመነ በመጣው የዓለማችን የኑሮ ሁኔታ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሕልውና ጥያቄ ሆኗል። በተለይ ሕዝቦች ከከፋ ድህነት ተላቅቀው የተሻለ ሕይወት መምራት እንዲችሉ በኢኮኖሚው መስክ ንቁ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ይጠበቃል፡፡ እንደ ንግድ ያሉ የኢኮኖሚ ዘርፎች ደግሞ አንዳንዴ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት የተለያየ ስፍራ መገኘትን ይጠይቃል። የሰው ልጅ ደግሞ በተፈጥሮው በጊዜና በቦታ ውሱን ከመሆኑ አንፃር በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ጥቅሙን በሚመለከቱ ስፍራዎች ሁሉ ተገኝቶ ተግባሩን መከወን አይችልም፡፡ እነዚህ መሰል ጉዳዮችን አስመልክቶ የሰው ልጅ የሚኖረው ብቸኛ አማራጭ እንደራሱ ሆኖ በእርሱ እግር ተተክቶ ጉዳዮቹን ወይም ሥራዎቹን የሚከውንለትን ሰው መወከል ግድ ይሆንበታል፡፡ ሥራዎችን በውክልና ማሰራት አስፈላጊ የሆነው በኢኮኖሚው ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በማህበራዊ የሕይወት መስክም ካለው ጠቀሜታ አኳያ ነው፡፡ በየትኛውም ዘርፍ የሚደረጉ የውክልና ውሎች ማዕቀፋቸው በፍትሐብሔር ሕግ ከአንቀጽ 2179 እስከ 2285 ባሉ ድንጋጌዎች ነው፡፡ በዚሁ ሕግ መሠረት የውክልና ሕግ የእንደራሴነት ሕግ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ሁለቱንም ቃላት መጠቀም በፍቺ ረገድ ልዩነት የላቸውም፡፡ በአማርኛ መዝገበ ቃላት «ወኪል» የሚለውን ቃል እንደዋና ሆኖ የሚሰራ፣ ተጠሪ፣ ኃላፊ፣ ዋናውን ተክቶ እንዲሰራ የተመረጠው ሰው፣ አካል የሚል ሲሆን «ውክልና» ማለትን ደግሞ ለአንድ ሰው ወይም ድርጅት ወኪል፣ ተጠሪ መሆን የሚል ፍቺ ተሰጥቶታል፡፡ በፍ/ሕ/ቁ 2199 መሠረት ደግሞ «ውክልና» ማለትን በሚከተለው መልኩ ይተረጉመዋል፡፡ «ተወካይ የተባለ አንድ ሰው ወካይ ለተባለው ሰው እንደራሴ ሆኖ አንድ ወይም ብዙ ሕጋዊ ሰራዎችን በወካዩ ስም ለማከናወን ግዴታ የሚገባበት ውል ነው።

ኣስቂኝ ዜና ስለ ኣቶ መለስ እና የፕሬስ ነጻነት

Image
በተለይ በላፉት ኣምስት ኣመታት የሚዲያ ነጻነት ኣፊነው ጋዜጤኞችን በየጊዜው በሰበብ ኣስባቡ ከከርቼሌ ዘብጥያ ስወረውሩ የቆዩትን መሪ ለሚዲያ ነጻነት ታግለዋል ብሎ የሚያወድስ ዜና መስማት ኣያስቂም? ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት እንዲከበር ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል  -የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ ብሮድ ካስት ባለስልጣን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት እንዲከበር ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ መሪ እንደነበሩ ገለጸ። ባለሥልጣኑ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ የባለስልጣኑ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት ጥልቅ ኀዘን እንደተሰማቸው ገልጿል።  ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤተሰቦችና ለኢትዮጵያ ህዝብም መጽናናትን ተመኝቷል።  ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ህገ መንግሥታዊ ዋስትና አግኝተው ተግባራዊ እንዲሆኑ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ባለሥልጣኑ ገልጿል። በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት እንዲከበር ማድረግ የአመለካከት እና ሀሳብን በነፃ የመያዝና የመግለጽ መብት እውን እንዲሆን ሰርተዋል ብሏል። አገሪቱ ከኋላ ቀርነት እና ከድህነት ተላቅቃ በአፍሪካም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስሟ በመልካም እንዲጠራ የሰሩ እሩቅ አሳቢና ባለዕራይ ነበሩ። ያለው የባለሥልጣኑ መግለጫ፣ እሳቸው የጀመሩትን የሰላም የልማትና የዴሞክራሲ መስመር በመከተል ለማሳካት ጠንክሮ እንደሚሰራ አረጋግጧል። http://www.ethpress.gov.et/ethpress/main/news.php?newsLocation=home&newsInstruction=headline&newsId=9252

Food Production and Food Losses

People in all over the world produce their foods in their own peculiar way and system of production. The way an American farmer grows food compared with their Ethiopian counterparts are beyond comparison. The number of people who are engaged in agriculture in America is said to be only three percent of the total population while 87pct of the Ethiopian population are agriculturalists. However, the American farmers are net food exporters contrary to the large majority Ethiopians who are subsistence farmers and food insecure. This is not God’s curse against the Ethiopians; rather it is the huge difference in their level of development and production systems.  As in their food production, there is also marked difference between America and Ethiopia in the amount of their food losses. The amount of food losses in America is so large that it is incomparable with the food Ethiopia loses which is very minimal. The same is true with America and other developing countries. The same reality is a