Posts

ኣስቂኝ ዜና ስለ ኣቶ መለስ እና የፕሬስ ነጻነት

Image
በተለይ በላፉት ኣምስት ኣመታት የሚዲያ ነጻነት ኣፊነው ጋዜጤኞችን በየጊዜው በሰበብ ኣስባቡ ከከርቼሌ ዘብጥያ ስወረውሩ የቆዩትን መሪ ለሚዲያ ነጻነት ታግለዋል ብሎ የሚያወድስ ዜና መስማት ኣያስቂም? ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት እንዲከበር ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል  -የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ ብሮድ ካስት ባለስልጣን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት እንዲከበር ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ መሪ እንደነበሩ ገለጸ። ባለሥልጣኑ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ የባለስልጣኑ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት ጥልቅ ኀዘን እንደተሰማቸው ገልጿል።  ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤተሰቦችና ለኢትዮጵያ ህዝብም መጽናናትን ተመኝቷል።  ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ህገ መንግሥታዊ ዋስትና አግኝተው ተግባራዊ እንዲሆኑ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ባለሥልጣኑ ገልጿል። በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት እንዲከበር ማድረግ የአመለካከት እና ሀሳብን በነፃ የመያዝና የመግለጽ መብት እውን እንዲሆን ሰርተዋል ብሏል። አገሪቱ ከኋላ ቀርነት እና ከድህነት ተላቅቃ በአፍሪካም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስሟ በመልካም እንዲጠራ የሰሩ እሩቅ አሳቢና ባለዕራይ ነበሩ። ያለው የባለሥልጣኑ መግለጫ፣ እሳቸው የጀመሩትን የሰላም የልማትና የዴሞክራሲ መስመር በመከተል ለማሳካት ጠንክሮ እንደሚሰራ አረጋግጧል። http://www.ethpress.gov.et/ethpress/main/news.php?newsLocation=home&newsInstruction=headline&newsId=9252

Food Production and Food Losses

People in all over the world produce their foods in their own peculiar way and system of production. The way an American farmer grows food compared with their Ethiopian counterparts are beyond comparison. The number of people who are engaged in agriculture in America is said to be only three percent of the total population while 87pct of the Ethiopian population are agriculturalists. However, the American farmers are net food exporters contrary to the large majority Ethiopians who are subsistence farmers and food insecure. This is not God’s curse against the Ethiopians; rather it is the huge difference in their level of development and production systems.  As in their food production, there is also marked difference between America and Ethiopia in the amount of their food losses. The amount of food losses in America is so large that it is incomparable with the food Ethiopia loses which is very minimal. The same is true with America and other developing countries. The same reality is a

Hawassa University Expresses its grief on the death of our late Prime Minister His Excellency Mr. Meles Zenawi. The University wishes strength for his family and the Ethiopian People.

Image
продвижение сайтов Hawassa University Expresses its grief on the death of our late Prime Minister His Excellency Mr. Meles Zenawi. The University wishes strength for his family and the Ethiopian People.

በኢትዮጵያ ህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን የደቡብ ኢትዮጵያ ህብረት ጽህፈት ቤት ፣ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሀዋሪያት ቤተክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት፣ የሀዋሣ ጐተራ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ጽህፈት ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለፁ፡፡

  በኢትዮጵያ ህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን የደቡብ ኢትዮጵያ ህብረት ጽህፈት ቤት ፣ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሀዋሪያት ቤተክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት፣ የሀዋሣ ጐተራ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ጽህፈት ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለፁ፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒሰትሩ የሀገራችን የልማት ሀዋሪያ፣ የምን ጊዜም ጀግና ፣ የፍሪካ ኩራት ናቸው፡፡ በሞት ቢለዩንም ህያው ሥራዎቻቸው በኢትዮጵያውያን ልብ ሲታወሱ ይኖራሉ ብለዋል፡፡   ለሀይማኖት መስፋፋት፣ ነፃነትና እኩልነት የተጉ መሪ እንደነበሩ ያመለከቱት መግለጫ ሰጪዎች በክልሉ የሚገኙ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች እጅ ለእጅ ተያይዘን የተጀመሩ የልማት ተግባራትን ከዳር ለማድረስ ቆርጠን እንሠራለን ብለዋል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/21NehTextN604.html  

የሲዳማ ዞን ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች መመሪያ፣ የእዥ ወረደ አስተዳደር በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን ገልፀዋል፡፡

ክቡር ጠቀላይ ሚኒስትር የሴቶችንና የወጣቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን እንዲሁም የህፃናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ ምቹ የሆኑ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን በመንደፍና ተግባራዊ በማድረግ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ በርሳቸው አመራር ኃላ ቀርነትን ታሪክ ለማድረግና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያስችል መሠረት ተጥሏል፡፡ ይሁን እንጂ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ሞት የከፋ ሀዘን ተሰምቶናል ብለዋል፡፡   በተመሳሳይ የሀዋሳ እርሻ ልማት ድርጅትና የኢትዮጵያ መፅሐፍ ቅዱስ ማህበር ሀዋሣ ቅርንጫፍ ሀገራችንን በበሳል አመራር ላለፉት 21 አመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በመምራትና ትክክለኛ የእድገት መንገድ በመቀየስ መሪ ሚና የተጫወቱት ክቡር ጠቅላይ ሚኒሰትር በመለየታቸው ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው አመልክተዋል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/21NehTextN204.html